የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ለሰዎች ያለብን ዕዳ
    የመንግሥት አገልግሎት—2005 | ሐምሌ
    • ለሰዎች ያለብን ዕዳ

      1 ሐዋርያው ጳውሎስ ለሰዎች የመስበክ ግዴታ እንዳለበት ተሰምቶታል። ይሖዋ በልጁ ክቡር ደም አማካኝነት ሰዎች ሁሉ መዳን የሚችሉበትን ዝግጅት ማድረጉን ያውቅ ነበር። (1 ጢ⁠ሞ. 2:3-6) በዚህም ምክንያት “ግሪኮች ለሆኑትና ላልሆኑት፣ ለጥበበኞችና ለማያስተውሉ፣ ዕዳ አለብኝ” በማለት ተናግሯል። ጳውሎስ ለሌሎች ሰዎች ያለበትን ዕዳ ለመክፈል ሲል ምሥራቹን በጋለ ስሜትና ያለማሰለስ ሰብኳል።—⁠ሮሜ 1:14, 15

      2 በዛሬው ጊዜ የሚገኙ ክርስቲያኖችም ልክ እንደ ጳውሎስ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ለሰዎች ምሥራቹን መስበክ ይፈልጋሉ። ‘ታላቁ መከራ’ በፍጥነት እየተቃረበ በመሆኑ ቅን ልብ ያላቸውን ሰዎች መፈለጋችን አጣዳፊ ነው። ለሰዎች ያለን ልባዊ ፍቅር ሕይወት አድን በሆነው በዚህ ሥራ ላይ በትጋት እንድንካፈል ይረዳናል።​—⁠ማቴ. 24:21፤ ሕዝ. 33:8

      3 ዕዳችንን መክፈል:- ለሰዎች መስበክ የምንችልበት ዋነኛው መንገድ ከቤት ወደ ቤት ማገልገል ነው። ብዙ ሰዎች ቤታቸው በማይገኙባቸው የአገልግሎት ክልሎች ውስጥ ትክክለኛ መረጃ መያዝና በተለያየ ሰዓት መሄድ ተጨማሪ ሰዎችን እንድናገኝ ያስችለናል። (1 ቆ⁠ሮ. 10:33) በተጨማሪም በንግድ አካባቢ፣ በመንገድ ላይ፣ በመናፈሻ ቦታዎች፣ በመኪና ማቆሚያ አካባቢዎች እንዲሁም በስልክ በመመሥከር ምሥራቹን ለሰዎች ማድረስ እንችላለን። ‘የሕይወትን መልእክት ለሌሎች ለማካፈል በሁሉም ዓይነት የስብከት ዘዴዎች የቻልኩትን ያህል ለመጠቀም እየጣርኩ ነው?’ ብለን ራሳችንን መጠየቅ እንችላለን።​—⁠ማቴ. 10:11

      4 አንዲት አቅኚ እህት በአገልግሎት ክልሏ ለሚገኙት ሰዎች ሁሉ ምሥራቹን የማድረስ ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለባት ይሰማታል። ይሁን እንጂ ወደ አንድ ቤት ደጋግማ ብትሄድም ማንንም ሰው አግኝታ አታውቅም። አንድ ቀን በሌላ ጉዳይ በዚያ አካባቢ ስታልፍ በር ላይ መኪና ቆሞ አየች። አጋጣሚው እንዳያመልጣት ስትል የቤቱን መጥሪያ ደወለች። አንድ ሰው በሩን ከፍቶላት ውይይት ያደረጉ ሲሆን ይህም እህትና ባለቤቷ ለበርካታ ጊዜያት ተመላልሶ መጠየቅ እንዲያደርጉ መሠረት ጥሏል። ከጊዜ በኋላ ሰውየው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲጀምር የቀረበለትን ግብዣ ተቀበለ፤ አሁን የተጠመቀ ወንድም ሆኗል። ይህች እህት ለሌሎች የመስበክ ዕዳ እንዳለባት ተሰምቷት ኃላፊነቷን በመወጣቷ አመስጋኝ ነው።

      5 መጨረሻው ይበልጥ እየተቃረበ በመሆኑ በስብከቱ ሥራ በትጋት እየተካፈልን ለሌሎች ሰዎች ያለብንን ዕዳ የምንከፍልበት ጊዜ አሁን ነው።​—⁠2 ቆ⁠ሮ. 6:1, 2

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችን እድገት እንዲያደርጉ መርዳት
    የመንግሥት አገልግሎት—2005 | ሐምሌ
    • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችን እድገት እንዲያደርጉ መርዳት

      ክፍል 11፦ ጥናቶቻችን ተመላልሶ መጠየቅ እንዲያደርጉ መርዳት

      1 አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ በስብከቱ ሥራ ላይ መሳተፍ ሲጀምር ለምሥራቹ ፍላጎት የሚያሳዩ ሰዎችን ማግኘቱ አይቀርም። ታዲያ ይህ አዲስ አስፋፊ ውጤታማ ተመላልሶ መጠየቅ ማድረግና ያገኛቸውን ሰዎች ፍላጎት ማሳደግ እንዲችል እንዴት ልንረዳው እንችላለን?

      2 ተመላልሶ መጠየቅ ለማድረግ ዝግጅት መደረግ ያለበት በመጀመሪያው ውይይት ወቅት ነው። ጥናትህ ያነጋገራቸውን ሰዎች የመርዳት ልባዊ ፍላጎት እንዲያድርበት አበረታታው። (ፊልጵ. 2:4) ተማሪው የሚያነጋግራቸውን ሰዎች ሐሳባቸውን እንዲገልጹ መጋበዝ፣ የሚሰጡትን ሐሳብ በጥሞና ማዳመጥና የሚያሳስባቸውን ጉዳይ መረዳት የሚችለው እንዴት እንደሆነ ቀስ በቀስ አሠልጥነው። ፍላጎት ያሳየ ሰው ሲያጋጥምህ አዲሱ አስፋፊ በውይይቱ ውስጥ የተነሱትን ጠቃሚ ሐሳቦች በጽሑፍ እንዲያሰፍር አድርግ። ይህን መረጃ ለቀጣዩ ውይይት እቅድ ለማውጣት እንዲጠቀምበት እርዳው።

      3 ተመላልሶ መጠየቅ ለማድረግ መዘጋጀት:- የመጀመሪያውን ውይይት ከከለሳችሁ በኋላ መንግሥቱን በሚመለከት ሰውየውን ሊማርኩ የሚችሉ ሐሳቦችን መምረጥ የሚችልበትን መንገድ ለጥናትህ አሳየው። (1 ቆ⁠ሮ. 9:​19-​23) ከማስጠኛ ጽሑፍ ላይ በአንድ አንቀጽና በዚያ ውስጥ በሚገኝ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ላይ የተመሠረተ አጠር ያለ ውይይት እንዴት ማድረግ እንደሚችል አብራችሁ ተዘጋጁ። በተጨማሪም ለቀጣዩ ውይይት መሠረት መጣል እንድትችሉ በውይይቱ መደምደሚያ ላይ የምታነሷቸውን ጥያቄዎች አዘጋጁ። በምታደርጓቸው ቀጣይ ተመላልሶዎች ሰውየው ስለ አምላክ ቃል ያለውን እውቀት ደረጃ በደረጃ እንዲያሳድግ እንዴት መርዳት እንደሚችል ለአስፋፊው አሳየው።

      4 በተጨማሪም ጥናትህ በተመላልሶ መጠየቅ ጊዜ ሊጠቀምበት የሚችል ቀለል ያለ መግቢያ እንዲዘጋጅ መርዳት ጠቃሚ ነው። ከቤቱ ባለቤት ጋር ሰላምታ ከተለዋወጠ በኋላ እንደሚከተለው ለማለት ይችላል:- “ባለፈው ጊዜ ባደረግነው ውይይት በጣም ተደስቻለሁ፤ አሁን ተመልሼ የመጣሁት ስለ [ቀደም ሲል የተወያያችሁበትን ርዕሰ ጉዳይ ጥቀስ] ተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሐሳቦችን ላካፍልዎት ነው።” የቤቱን በር ሌላ ሰው ቢከፍት ምን ለማለት እንደሚችል ለአዲሱ አስፋፊ ማሳየት ይኖርብህ ይሆናል።

      5 ተመላልሶ መጠየቅ በማድረግ ረገድ ትጉዎች ሁኑ:- ጥናትህ ፍላጎት ላሳዩ ሰዎች ሁሉ ተመላልሶ መጠየቅ በማድረግ ረገድ ጥሩ ምሳሌ እንዲሆን አበረታታው። ሰዎችን ቤታቸው ማግኘት ሳይሰለቹ ተመልሶ መሄድ ይጠይቃል። በድጋሚ ለመገናኘት እንዴት ቀጠሮ መያዝ እንደሚችልና ቃል በገባው መሠረት ተመልሶ የመሄዱን አስፈላጊነት እንዲገነዘብ እርዳው። (ማቴ. 5:​37) በግ መሰል የሆኑ ሰዎችን ለመፈለግና ፍላጎታቸውን ለማሳደግ ርኅሩኅ፣ አሳቢና አክብሮት ያለው እንዲሆን አዲሱን አስፋፊ አሠልጥነው።​—⁠ቲቶ 3:2

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ