-
የግንቦት የአገልግሎት ሪፖርትየመንግሥት አገልግሎት—2005 | ነሐሴ
-
-
የግንቦት የአገልግሎት ሪፖርት
አማ. አማ. አማ. አማ.
ብዛት:- ሰዓት መጽሔ. ተ.መ. መ/ቅ.ጥ.
ልዩ አቅኚ 261 131.4 25.0 82.6 5.9
አቅኚ 801 67.2 9.0 28.2 1.9
ረዳት አቅኚ 430 50.8 7.0 18.9 1.0
አስፋፊ 5,982 12.2 2.0 5.2 0.4
ጠቅላላ 7,474
-
-
ሰዎችን በራቸው ላይ እንደቆምን አሊያም በስልክ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመርየመንግሥት አገልግሎት—2005 | ነሐሴ
-
-
ሰዎችን በራቸው ላይ እንደቆምን አሊያም በስልክ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመር
1, 2. በሥራ የተጠመዱ ሰዎችን ለመርዳት መጽሐፍ ቅዱስ የምናስጠናበትን ፕሮግራም እንዴት ማስተካከል እንችላለን?
1 በዛሬው ጊዜ ሰዎች በሥራ የተጠመዱ ናቸው። እንደዚያም ሆኖ ግን ብዙዎች ለመንፈሳዊ ነገሮች ፍላጎት አላቸው። ታዲያ መንፈሳዊ ፍላጎታቸውን እንዴት ማርካት እንችላለን? (ማቴ. 5:3) በርካታ አስፋፊዎች ሰዎችን በራቸው ላይ ቆመው እያነጋገሯቸው ሳለ ወይም በስልክ አማካኝነት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመር ችለዋል። አንተስ በዚህ መልኩ አገልግሎትህን ማስፋት ትችል ይሆን?
2 አመቺ አጋጣሚ ስናገኝ ጥናቱ እንዴት እንደሚካሄድ ለሰዎች ለማሳየት ዝግጁ በመሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመር እንችላለን። ይህን ማድረግ የሚቻለው እንዴትና የት ነው?
3. በመጀመሪያው ውይይት ላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዴት እንደሚካሄድ ማሳየት ያስፈለገው ለምንድን ነው? ይህን ማድረግ የሚቻለውስ እንዴት ነው?
3 በራቸው ላይ እንደቆምን:- ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ለመወያየት የሚፈልግ ሰው ስታገኝ ቀደም ብለህ የተዘጋጀህበትን አንድ አንቀጽ አውጥተህ ጥናት አስጀምረው፤ ለምሳሌ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው በተባለው ብሮሹር ትምህርት 1 የመጀመሪያውን አንቀጽ መጠቀም ትችላለህ። አንቀጹን ካነበብክና ጥያቄዎቹን ከጠየቅክ በኋላ በአንቀጹ ላይ ከሚገኙት ጥቅሶች አንድ ወይም ሁለቱን አንብብና ተወያዩባቸው። ብዙውን ጊዜ እዚያው በራቸው ላይ እንደቆምክ ከአምስት እስከ አሥር ደቂቃ ባለው ጊዜ ውስጥ እንዲህ ዓይነት ውይይት ማድረግ ትችላለህ። ግለሰቡ በውይይቱ ከተደሰተ በሌላ ጊዜ ቀጣዮቹን አንድ ወይም ሁለት አንቀጾች ለመወያየት ዝግጅት አድርግ።—ቀጥተኛ አቀራረብ በመጠቀም ጥናት ለማስጀመር የሚያስችሉ ሐሳቦች ከጥር 2002 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 6 ላይ ማግኘት ይቻላል።
4. ተመላልሶ መጠየቅ ስናደርግ በሩ ላይ እንደቆምን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመር የምንችለው እንዴት ነው?
4 ተመላልሶ መጠየቅ ስናደርግም ተመሳሳይ አቀራረብ በመጠቀም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመር እንችላለን። ለምሳሌ፣ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር ካስተዋወቅክ በኋላ ትምህርት 2 አንቀጽ 1ና 2ን በመጠቀም ስለ ይሖዋ ስም ማብራራት ትችላለህ። በሚቀጥለው ጊዜ አንቀጽ 3ና 4ን በመጠቀም መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ይሖዋ ባሕርያት የሚናገረውን ልትወያዩበት ትችላላችሁ። ከዚያ በኋላ ደግሞ አንቀጽ 5ና 6ን እንዲሁም ገጽ 5 ላይ ያለውን ሥዕላዊ መግለጫ በመጠቀም ይሖዋን ለማወቅ መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት እንዴት እንደሚረዳን ልታብራራ ትችላለህ። ይህን ሁሉ በሩ ላይ እንደቆምን ማድረግ እንችላለን።
5, 6. (ሀ) አንዳንዶች መጽሐፍ ቅዱስን በስልክ ለማጥናት የሚመርጡት ለምንድን ነው? (ለ) በስልክ ጥናት ለማስጀመር የትኛውን መግቢያ ልንጠቀም እንችላለን?
5 በስልክ:- አንዳንድ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን በግንባር ቀርበው ከሚያጠኑ ይልቅ በስልክ ለማጥናት ይበልጥ ፈቃደኞች ሊሆኑ ይችላሉ። የሚቀጥለውን ተሞክሮ ተመልከት:- አንዲት እህት ከቤት ወደ ቤት በምታገለግልበት ጊዜ ሥራ የሚበዛባት አንዲት ወጣት እናት አገኘች። እህት ሴትየዋን ተመልሳ ቤት ለማግኘት ስላልቻለች ስልክ ለመደወል ወሰነች። ወጣቷ ሴት መጽሐፍ ቅዱስን ለመወያየት ምንም ጊዜ እንደሌላት ነገረቻት። እህት ቀጠል አደረገችና “በስልክ ለ10 ወይም ለ15 ደቂቃ በመወያየትም ቢሆን አዲስ ነገር መማር ትችያለሽ” አለቻት። ሴትየዋም “በስልክ ከሆነ እስማማለሁ!” ብላ መለሰችላት። ብዙም ሳይቆይ መጽሐፍ ቅዱስን አዘውትረው በስልክ ማጥናት ጀመሩ።
6 ምናልባት ተመላልሶ መጠየቅ ከምታደርግላቸው ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ በስልክ ለማጥናት ይፈልጉ ይሆን? ከላይ የተጠቀሰውን መግቢያ ልትጠቀም ትችላለህ፤ አሊያም እንዲህ ማለት ትችላለህ:- “የሚያመችዎት ከሆነ በስልክ መወያየት እንችላለን። እንደዚህ ብናደርግ ለእርስዎ አመቺ ይሆንልዎታል?” መጽሐፍ ቅዱስ የምናስጠናበትን ፕሮግራም ለሰዎች እንደሚመች አድርገን በማስተካከል ‘አምላክን ማወቅ’ እንዲችሉ ልንረዳቸው እንችላለን።—ምሳሌ 2:5፤ 1 ቆሮ. 9:23
-
-
መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?የመንግሥት አገልግሎት—2005 | ነሐሴ
-
-
መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ሰኔ 1
“አብዛኛው ሰው ስለ ሰላም ቢናገርም ዓለም አቀፍ አንድነት ግን ከሰው ልጆች ርቋል። ዓለም አቀፍ አንድነት ሕልም ብቻ ሆኖ የሚቀር ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት ዓለምን አንድ ማድረግ የሚችል መንግሥት እንዳለ ይገልጻል።” መዝሙር 72:7, 8ን አንብብና ይህ እንዴት ሊሆን እንደሚችል ለመወያየት ተመልሰህ ለመምጣት ቀጠሮ ያዝ።
ንቁ! ሰኔ 2005
“ልጆች አስቸጋሪ በሆነው አፍላ የጉርምስና ዕድሜ የሚከሰቱትን ችግሮች ለማስወገድ እንዲችሉ ወላጆች እንዴት ሊረዷቸው የሚችሉ ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው። ከዚያም ኢሳይያስ 48:17, 18ን አንብብለት።] ይህ መጽሔት ወላጆች የመጽሐፍ ቅዱስን ምክር በሥራ ላይ በማዋል ከልጆቻቸው ጋር ጥሩ የሐሳብ ግንኙነት ማድረግና አግባብነት ያላቸው ገደቦችን ማበጀት የሚችሉበትን መንገድ ያብራራል።”
መጠበቂያ ግንብ ሰኔ 15
“አብዛኞቻችን በሕይወታችን ውስጥ ሰፋ ያለውን ጊዜ የምናሳልፈው በሥራ ነው። አንዳንዶች ሥራን እንደ በረከት ሲያዩት ሌሎች ደግሞ እንደ እርግማን ይመለከቱታል። እርስዎስ ምን ይሰማዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው። ከዚያም መክብብ 2:24ን አንብብለት።] ይህ መጽሔት ለሥራ ሚዛናዊ የሆነ አመለካከት እንድናዳብር መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት እንደሚረዳን ያሳያል። ከሥራ ጋር በተያያዘ የሚፈጠር ውጥረትን እንዴት መወጣት እንደሚቻልም ያብራራል።”
-