የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘የእምነትን ቃል መመገብ’
    የመንግሥት አገልግሎት—2005 | ጥር
    • ‘የእምነትን ቃል መመገብ’

      1 ለአምላክ ያደሩ ሆኖ መኖር ብርቱ ጥረት ይጠይቃል። (1 ጢሞ. 4:7-10) በመሆኑም በራሳችን ኃይል ይህን የሕይወት ጎዳና ለመከተል ጥረት የምናደርግ ከሆነ ዝለን ልንወድቅ እንችላለን። (ኢሳ. 40:29-31) ከይሖዋ ዘንድ ኃይል የምናገኝበት አንዱ መንገድ ‘የእምነትን ቃል በመመገብ’ ነው።—1 ጢሞ. 4:6 የ1954 ትርጉም

      2 የተትረፈረፈ መንፈሳዊ ምግብ:- ይሖዋ በቃሉ እንዲሁም ‘በታማኝና ልባም ባሪያ’ በኩል የተትረፈረፈ መንፈሳዊ ምግብ ያቀርብልናል። (ማቴ. 24:45 የ1954 ትርጉም) ከዚህ ዝግጅት ለመጠቀም የበኩላችንን እያደረግን ነው? መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ እናነባለን? የግል ጥናት ለማድረግና ለማሰላሰል የሚያስችል ጊዜስ መድበናል? (መዝ. 1:2, 3) እንደዚህ ያለው ጤናማ መንፈሳዊ ምግብ ብርታት የሚሰጠን ከመሆኑም በላይ የሰይጣን ዓለም በሚያደርስብን ተጽዕኖ እንዳንዳከም ይረዳናል። (1 ዮሐ. 5:19) አእምሯችንን ጤናማ የሆነ ትምህርት የምንመግብና የተማርነውን በሕይወታችን ውስጥ ተግባራዊ የምናደርግ ከሆነ ይሖዋ ከእኛ ጋር ይሆናል።—ፊልጵ. 4:8, 9

      3 ይሖዋ በጉባኤ ስብሰባዎችም ያበረታታናል። (ዕብ. 10:24, 25) በእነዚህ ስብሰባዎች ላይ የምናገኘው መንፈሳዊ ትምህርትና ከወንድሞቻችን ጋር የምንመሠርተው ጥሩ ወዳጅነት በፈተና ጊዜ ጸንተን እንድንቆም ያደርገናል። (1 ጴጥ. 5:9, 10) አንዲት ወጣት ክርስቲያን “ሙሉ ቀን ትምህርት ቤት ውዬ ስመጣ እዝላለሁ። ስብሰባዎች ግን ልክ በበረሃ መካከል እንዳለ ገነት ለሚቀጥለው ቀን የትምህርት ቤት ውሎዬ መንፈሴን ያድሱልኛል” በማለት ተናግራለች። በስብሰባዎች ላይ ለመገኘት በምናደርገው ጥረት በእጅጉ ተባርከናል!

      4 እውነትን ማወጅ:- ለሌሎች መስበክ ለኢየሱስ ልክ እንደ ምግብ የብርታት ምንጭ ሆኖለት ነበር። (ዮሐ. 4:32-34) እኛም በተመሳሳይ ለሰዎች ስለ አስደናቂው የአምላክ ተስፋ በምንናገርበት ጊዜ ኃይላችን ይታደሳል። በተጨማሪም በአገልግሎት የምንጠመድ ከሆነ ልባችንም ሆነ አእምሯችን በመንግሥቱና በቅርቡ በሚመጡት በረከቶች ላይ ያተኮረ ይሆናል። በእውነትም የስብከቱ ሥራ እንድንታደስ ያደርገናል።—ማቴ. 11:28-30

      5 በዛሬው ጊዜ ይሖዋ ለሕዝቦቹ ከሚያቀርበው የተትረፈረፈ መንፈሳዊ ምግብ መቋደስ በመቻላችን በእርግጥም ተባርከናል! እንግዲያው ይሖዋን በደስታ ማወደሳችንን እንቀጥል።—ኢሳ. 65:13, 14

  • ክፍል 5—የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችን እድገት እንዲያደርጉ መርዳት
    የመንግሥት አገልግሎት—2005 | ጥር
    • ክፍል 5​—የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችን እድገት እንዲያደርጉ መርዳት

      ምን ያህል ትምህርት እንደምንሸፍን መወሰን

      1 ኢየሱስ በሚያስተምርበት ወቅት የደቀ መዛሙርቱን አቅም ግምት ውስጥ በማስገባት “መረዳት በሚችሉበት መጠን” ይነግራቸው ነበር። (ማር. 4:33፤ ዮሐ. 16:12) በተመሳሳይም በዛሬው ጊዜ ያሉት የአምላክ ቃል አስተማሪዎች መጽሐፍ ቅዱስን ሲያስጠኑ አንድን ትምህርት በምን ያህል ጊዜ መሸፈን እንደሚችሉ መገመት አለባቸው። እርግጥ የሚሸፈነው ትምህርት መጠን በአስጠኚውም ሆነ በጥናቱ ችሎታና ሁኔታ ላይ የተመካ ነው።

      2 ጠንካራ እምነት ገንቡ፦ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች በአንድ የጥናት ክፍለ ጊዜ በቀላሉ ሊረዱ የሚችሉትን ትምህርት ለሌሎች ጥናቶች በሁለት ወይም በሦስት ክፍለ ጊዜ ማስጠናት ሊኖርብን ይችላል። አሳሳቢው ነገር ተማሪው ትምህርቱን በግልጽ መረዳቱ እንጂ በፍጥነት መጨረሱ አይደለም። እያንዳንዱ ተማሪ ከአምላክ ቃል ያገኘው አዲስ እምነት በጠንካራ መሠረት ላይ የተመሠረተ ሊሆን ይገባል።—ምሳሌ 4:7፤ ሮሜ 12:2

      3 በየሳምንቱ ጥናት በምንመራበት ጊዜ ተማሪው ከአምላክ ቃል የተማረው እንዲገባውና እንዲቀበለው ለማድረግ የሚያስፈልገውን ያህል ጊዜ መመደብ ይኖርብናል። ስለሆነም ትምህርቱን በሩጫ በመሸፈን ተማሪው ከሚማራቸው እውነቶች ሙሉ በሙሉ ተጠቃሚ እንዳይሆን ማድረግ የለብንም። በዋና ዋና ነጥቦቹ ላይ ለማተኮርና ለትምህርቱ መሠረት በሆኑት ቁልፍ ጥቅሶች ላይ ለመወያየት በቂ ጊዜ መድብ።—2 ጢሞ.3:16,17

      4 ትኩረታችሁን ሊከፋፍሉ የሚችሉ ነገሮችን አስወግዱ፦ ጥናቱን በጥድፊያ መምራት እንደሌለብን ሁሉ ትኩረታችንን የሚከፋፍሉ ነገሮች እንዲፈጠሩም አንፈልግም። ተማሪው ስለ ግል ጉዳዮቹ ሊነግረን የሚፈልገው ብዙ ነገር ካለ ጥናቱን ስናበቃ ለመወያየት ዝግጅት ማድረግ ይኖርብናል።—መክ. 3:1

      5 በሌላ በኩል ደግሞ ለእውነት ያለን አድናቆት በጥናቱ ወቅት ብዙ እንድንናገር ሊፈትነን ይችላል። (መዝ. 145:6, 7) እርግጥ አንዳንድ ጊዜ በጥናቱ መሃል ተጨማሪ ሐሳብ ወይም ተሞክሮ መናገራችን ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን እንደነዚህ ያሉት ሐሳቦች ረጅም ወይም የተንዛዙ ሆነው ተማሪው መሠረታዊ ስለሆኑት የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች ትክክለኛ እውቀት ሳይቀስም እንዲቀር አንፈልግም።

      6 በእያንዳንዱ የጥናት ክፍለ ጊዜ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎቻችንን እንደ አቅማቸው በማስጠናት ‘በእግዚአብሔር ብርሃን እንዲመላለሱ’ ልንረዳቸው እንችላለን።—ኢሳ. 2:5

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ