-
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችን እድገት እንዲያደርጉ መርዳትየመንግሥት አገልግሎት—2005 | መጋቢት
-
-
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችን እድገት እንዲያደርጉ መርዳት
ክፍል 7፦ በጥናቱ ወቅት መጸለይ
1. (ሀ) ጥናቱን በጸሎት መክፈትና መደምደም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? (ለ) በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችን ወቅት ስለ ጸሎት እንዴት ልንነግራቸው እንችላለን?
1 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችን በመንፈሳዊ እድገት እንዲያደርጉ የይሖዋ እርዳታ የግድ አስፈላጊ ነው። (1 ቆሮ. 3:6) ስለዚህ ጥናቱን ከመክፈታችንና ከመደምደማችን በፊት መጸለያችን ተገቢ ነው። የምናስጠናው ሰው ስለ ጸሎት የሚያውቅ ከሆነ አብዛኛውን ጊዜ ከመጀመሪያው ቀን አንስቶ ጥናቱን በጸሎት መክፈትና መደምደም እንችላለን። ለሌሎች ጥናቶቻችን ግን ስለ ጸሎት መቼ ብናወያያቸው የተሻለ እንደሚሆን ማስተዋል ያስፈልገን ይሆናል። ጸሎት የምናቀርብበትን ምክንያት ለማስረዳት መዝሙር 25:4, 5 እና 1 ዮሐንስ 5:14ን እንዲሁም ወደ ይሖዋ ስንጸልይ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል መቅረባችን አስፈላጊ መሆኑን ለመግለጽ ዮሐንስ 15:16ን መጠቀም እንችላለን።
2. አንዲት እህት ከአንድ የተጠመቀ ወንድም ወይም ካልተጠመቀ የመንግሥቱ አስፋፊ ጋር ጥናት በምታስጠናበት ወቅት ጸሎት ማቅረብ ያለበት ማነው?
2 በጥናቱ ወቅት ጸሎት ማቅረብ ያለበት ማነው? አንዲት እህት ጥናት በምትመራበት ወቅት አንድ የተጠመቀ ወንድም የሚገኝ ከሆነ ጸሎቱን የሚያቀርበው እሱ ሲሆን እህት ራሷን ሸፍና ጥናቱን መምራት ትችላለች። (1 ቆሮ. 11:5, 10) በሌላ በኩል ደግሞ አንድ ያልተጠመቀ የመንግሥቱ አስፋፊ አብሯት ጥናቱ ላይ ከተገኘ እሷ መጸለይዋ ተገቢ ነው። በዚህ ወቅት እህት ጥናቱን ስትመራም ሆነ ስትጸልይ ራሷን መሸፈን አለባት።
3. በጥናታችን ወቅት በምናቀርበው ጸሎት ውስጥ የትኞቹን ነገሮች ማካተት ተገቢ ነው?
3 በጸሎቱ ውስጥ መካተት ያለባቸው ነገሮች:- በጥናቱ ወቅት የሚቀርበው ጸሎት አስፈላጊ የሆኑትን ነጥቦች ለይቶ ሊጠቅስ ይገባል እንጂ ከልክ በላይ ሊረዝም አይገባም። በጥናቱ ወቅት የአምላክን እርዳታ ከመጠየቅና ለሰጠን እውነት ከማመስገን በተጨማሪ ይሖዋ የትምህርቱ ምንጭ እንደመሆኑ መጠን ሊወደስ ይገባዋል። (ኢሳ. 54:13) ከዚህም በላይ ለተማሪው ያለንን ልባዊ አሳቢነት እንዲሁም ይሖዋ እየተጠቀመበት ላለው ድርጅት አመስጋኝነታችንን በጸሎት መግለጽ እንችላለን። (1 ተሰ. 1:2, 3፤ 2: 7, 8) ጥናታችን እየተማረ ያለውን ነገር በሥራ ላይ ለማዋል የሚያደርገውን ጥረት ይሖዋ እንዲባርከው መጸለያችን ተማሪው ‘ቃሉ የሚናገረውን የማድረግን’ አስፈላጊነት እንዲገነዘብ ያደርገዋል።—ያዕ. 1:22
4. የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችንን በጸሎት መክፈትና መዝጋታችን ምን ጥቅሞችን ያስገኛል?
4 በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ወቅት የሚደረገው ጸሎት ብዙ ጥቅሞች አሉት። የአምላክን በረከት ያስገኛል። (ሉቃስ 11:13) የአምላክን ቃል ማጥናት ምን ያህል ክብደት ሊሰጠው የሚገባ መሆኑን ያጎላል። በምንጸልይበት ጊዜ ተማሪያችን እንዴት ብሎ መጸለይ እንዳለበትም ይማራል። (ሉቃስ 6:40) ከዚህም በላይ ለአምላክ ባለን ፍቅርና ወደር ለሌላቸው ባሕርያቱ ባለን አድናቆት ተገፋፍተን ከልብ በመነጨ ስሜት የምናቀርበው ጸሎት ጥናታችን ከይሖዋ ጋር የቅርብ ዝምድና እንዲመሠርት ይረዳዋል።
-
-
የታኅሣሥ የአገልግሎት ሪፖርትየመንግሥት አገልግሎት—2005 | መጋቢት
-
-
የታኅሣሥ የአገልግሎት ሪፖርት
አማ. አማ. አማ. አማ.
ብዛት:- ሰዓት መጽሔ. ተ.መ. መ/ቅ.ጥ.
ልዩ አቅኚ 216 130.5 25.5 86.4 6.7
አቅኚ 862 70.2 8.5 29.8 2.0
ረዳት አቅኚ 360 53.2 7.1 19.0 1.1
አስፋፊ 5,929 12.7 2.0 5.4 0.4
ጠቅላላ 7,367 አዲስ ከፍተኛ ቁጥር!
-
-
መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?የመንግሥት አገልግሎት—2005 | መጋቢት
-
-
መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ጥር 1
“አብዛኞቹ ሃይማኖቶች ሰዎች ጎረቤቶቻቸውን ሊወድዱ እንደሚገባ ያስተምራሉ። [ማቴዎስ 22:39ን አንብብ።] ይህ ከሆነ ታዲያ በዓለም ላይ የሚካሄዱት አብዛኞቹ ጦርነቶችና ግጭቶች የሃይማኖት እጅ ያለባቸው ለምን ይመስልዎታል? [የሚሰጠውን መልስ አዳምጥ።] ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም ‘ሃይማኖት ለሰው ዘር አንድነት ሊያስገኝ ይችላል?’ ለሚለው ጥያቄ መልስ ይዟል።”
ንቁ! ጥር 2005
“በዛሬው ጊዜ ከፍተኛ የቴክኖሎጂ እድገት ቢኖርም ይህ ሁኔታ የሰው ልጆች ጓደኛ ለማግኘት ያላቸውን መሠረታዊ ፍላጎት አላስቀረውም። ሆኖም በማኅብረሰቡ ውስጥ የሚታዩት ለውጦች የጠበቀ ወዳጅነት መመሥረት አስቸጋሪ እንዲሆን ማድረጋቸውን ልብ ብለዋል? [የሚሰጠውን መልስ ካዳመጥህ በኋላ ምሳሌ 18:24ን አንብብ።] ይህ መጽሔት እውነተኛ ወዳጆች ማፍራትና ወዳጅነታችን ዘላቂ እንዲሆን ማድረግ የምንችለው እንዴት እንደሆነ ይገልጻል።”
መጠበቂያ ግንብ ጥር 15
“ሁላችንም ለራሳችንም ሆነ ለልጆቻችን የተሻለ ሕይወት እንመኛለን። ሆኖም ብዙዎች ይህንን ለማግኘት አቅም እንደሌላቸው ይሰማቸዋል። የወደፊት ዕጣችንን መወሰን የምንችል ይመስልዎታል? [የሚሰጠውን መልስ አዳምጥ።] ይህ መጽሔት ሕይወታችንን መቆጣጠር እንደምንችልና የወደፊት ሕይወታችን አሁን በምናደርጋቸው ምርጫዎች ላይ የተመካ እንደሆነ ከመጽሐፍ ቅዱስ እየጠቀሰ ያብራራል።” ዘዳግም 30:19ን አንብብ።
-