-
የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብየይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ
-
-
እጅግ ሰፊ እንደሆነ መገንዘቡ በአድናቆት እንዲዋጥና ራሱን ዝቅ አድርጎ እንዲመለከት አድርጎታል። ኢሳይያስ ባየው ነገር በጥልቅ በመነካቱ ከሰማይ የይሖዋን ፍርድ የማወጁን ልዩ ሥራ አስመልክቶ ጥሪ በቀረበ ጊዜ “እነሆኝ! እኔን ላከኝ!” የሚል ምላሽ ሰጥቷል።—ኢሳ. 6:1-5, 8
13 የይሖዋ ሕዝቦችም ድርጅቱን እያወቁና እያደነቁ ሲሄዱ ተመሳሳይ ምላሽ ለመስጠት ይገፋፋሉ። ድርጅቱ ወደፊት እየገሰገሰ በሄደ መጠን እኛም እኩል ለመጓዝ ጥረት እናደርጋለን። በዛሬው ጊዜ እኛም በይሖዋ ድርጅት እንደምንተማመን በተግባር ከማሳየት ወደኋላ አንልም።
የይሖዋ ድርጅት እየገሰገሰ ነው
14 በሕዝቅኤል ትንቢት የመጀመሪያ ምዕራፍ ላይ ይሖዋ በሰማይ አንድ ትልቅ ሠረገላ እየነዳ እንዳለ ተደርጎ ተገልጿል። ይህ ክብር የተላበሰ ሠረገላ በዓይን የማይታየውን የይሖዋን ድርጅት ክፍል ይወክላል። ይሖዋ ይህን ሠረገላ የሚነዳ መሆኑ ድርጅቱን ከዓላማው ጋር በሚስማማ መንገድ እንደሚመራውና እንደሚጠቀምበት ያሳያል።—መዝ. 103:20
15 የዚህ ሠረገላ እያንዳንዱ መንኮራኩር፣ ተመሳሳይ ስፋት ያለው ሌላ መንኮራኩር በውስጡ ይዟል፤ ሁለተኛው መንኮራኩር መሃል ለመሃል ስለሚሰካ መንኮራኩሮቹ መስቀለኛ ቅርጽ ይሠራሉ። መንኮራኩሮቹ “በአራቱም ጎን በፈለጉበት አቅጣጫ መሄድ ይችላሉ” ሊባል የሚችለው ይህ ከሆነ ብቻ ነው። (ሕዝ. 1:17) መንኮራኩሮቹ አቅጣጫቸውን በቅጽበት መቀየር ይችላሉ። ይሁን እንጂ ይህ ሲባል ሠረገላውን የሚቆጣጠረው ወይም የሚመራው አካል የለም ማለት አይደለም። ይሖዋ ድርጅቱ ባሻው መንገድ እንዲሄድ አይፈቅድም። ሕዝቅኤል 1:20 “መንፈሱ ወደመራቸው አቅጣጫ . . . ይሄዳሉ” ይላል። በመሆኑም በመንፈሱ አማካኝነት ድርጅቱን ወደሚፈልግበት አቅጣጫ እንዲጓዝ የሚያደርገው ይሖዋ ነው። ስለዚህ ‘ከድርጅቱ እኩል እየተጓዝኩ ነው?’ ብለን ራሳችንን መጠየቅ ይኖርብናል።
16 ከይሖዋ ድርጅት እኩል መጓዝ ሲባል በስብሰባዎች ላይ መገኘትና በመስክ አገልግሎት መሳተፍ ማለት ብቻ አይደለም። ይህ አባባል በዋነኝነት የሚያመለክተው ወደፊት መግፋትንና መንፈሳዊ እድገት ማድረግን ነው። “ይበልጥ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች” ለይቶ ማወቅና በየጊዜው የሚቀርበውን መንፈሳዊ ምግብ በወቅቱ መመገብ ይጠይቃል። (ፊልጵ. 1:10፤ 4:8, 9፤ ዮሐ. 17:3) በተጨማሪም መደራጀት ካለ ጥሩ ቅንጅትና የትብብር መንፈስ እንደሚኖር የታወቀ ነው። በመሆኑም ይሖዋ፣ ሥራውን በተሳካ ሁኔታ ማከናወን እንድንችል ሲል በአደራ የሰጠንን መንፈሳዊና ቁሳዊ ሀብት ከሁሉ በተሻለ መንገድ የመጠቀምን አስፈላጊነት ቸል ማለት አይኖርብንም። በሰማይ ካለው የይሖዋ ሠረገላ እኩል ለመጓዝ ጥረት ስናደርግ አኗኗራችን ከምናውጀው መልእክት ጋር የሚስማማ ይሆናል።
17 ሁላችንም በይሖዋ ድርጅት እርዳታ የአምላክን ፈቃድ በማድረግ ረገድ ወደፊት እየገሰገስን ነው። በሰማይ ያለውን ይህን ሠረገላ የሚነዳው ይሖዋ መሆኑን መዘንጋት አይኖርብንም። ስለዚህ ከሠረገላው እኩል ለመጓዝ የምናደርገው ጥረት ለይሖዋ አክብሮት እንዳለንና ዓለታችን በሆነው አምላክ እንደምንታመን ያሳያል። (መዝ. 18:31) መጽሐፍ ቅዱስ “ይሖዋ ለሕዝቡ ብርታት ይሰጣል። ይሖዋ ሰላም በመስጠት ሕዝቡን ይባርካል” የሚል ተስፋ ይዟል። (መዝ. 29:11) በዛሬው ጊዜ የይሖዋ ድርጅት ክፍል በመሆናችን እሱ ከሚሰጠው ብርታት ተጠቃሚ መሆን ችለናል፤ እንዲሁም ለተደራጀው ሕዝቡ የሰጠውን ሰላም አግኝተናል። በእርግጥም ዛሬም ሆነ ለዘላለም የይሖዋን ፈቃድ ማድረጋችንን በቀጠልን መጠን የተትረፈረፈ በረከት ማግኘታችን የማይታበል ሐቅ ነው።
-
-
ክርስቶስ በአምላክ ዝግጅት ውስጥ ያለውን ሚና መቀበልየይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ
-
-
ምዕራፍ 2
ክርስቶስ በአምላክ ዝግጅት ውስጥ ያለውን ሚና መቀበል
“በመጀመሪያ አምላክ ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ”፤ የፈጠረውም ነገር ሁሉ “እጅግ መልካም” ነበር። (ዘፍ. 1:1, 31) ይሖዋ ሰውን ሲፈጥር ከፊቱ አስደሳች ተስፋ ዘርግቶለት ነበር። ይሁን እንጂ በኤደን የተከሰተው ዓመፅ ለሰው ልጆች የተዘረጋው አስደሳች ሕይወት ለጊዜውም ቢሆን እንዲስተጓጎል አድርጓል። ሆኖም ይሖዋ ለምድርም ሆነ ለሰው ልጆች ያለው ዓላማ አልተለወጠም። አምላክ ታዛዥ የሆኑ የአዳም ዘሮች መዳን የሚያገኙበት ዝግጅት እንደሚኖር ጠቁሟል። እውነተኛው አምልኮ ዳግመኛ የሚቋቋምበት ጊዜ እንደሚመጣና አምላክ ዲያብሎስን ከክፋት ድርጊቶቹ ጋር ጠራርጎ እንደሚያጠፋው አመልክቷል። (ዘፍ. 3:15) በዚያን ጊዜ ሁሉም ነገር እንደቀድሞው “እጅግ መልካም” ይሆናል። ይሖዋ ይህን የሚያከናውነው በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ነው። (1 ዮሐ. 3:8) በመሆኑም ክርስቶስ በአምላክ ዝግጅት ውስጥ የሚጫወተውን ሚና መቀበላችን ወሳኝ ነው።—ሥራ 4:12፤ ፊልጵ. 2:9, 11
የክርስቶስ ሚና ምንድን ነው?
2 ክርስቶስ በአምላክ ዝግጅት ውስጥ የሚጫወተው ሚና ብዙ ገጽታዎች እንዳሉት መገንዘብ ይኖርብናል። ኢየሱስ ሊቀ ካህናትና የክርስቲያን ጉባኤ ራስ ሆኖ የሚያገለግል ከመሆኑም ሌላ የሰው ልጆችን የሚቤዠው እሱ ነው፤ በአሁኑ ጊዜ ደግሞ የአምላክ መንግሥት ንጉሥ ሆኗል። ክርስቶስ በሚጫወተው የተለያየ ሚና ላይ ስናሰላስል ለአምላክ ዝግጅት ያለን አድናቆት ያድጋል፤ እንዲሁም ለክርስቶስ ኢየሱስ ያለን ፍቅር ይጨምራል። መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ የሚጫወተውን የተለያየ ሚና ይገልጻል።
ይሖዋ ለሰው ዘር ባለው ዓላማ አፈጻጸም ረገድ ኢየሱስ ቁልፍ ሚና ይጫወታል
3 ክርስቶስ ምድራዊ አገልግሎቱን ባከናወነበት ወቅት፣ ታዛዥ የሰው ልጆችን ከአምላክ ጋር የሚያስታርቀው እሱ እንደሆነ በግልጽ ታውቆ ነበር። (ዮሐ. 14:6) ኢየሱስ የሰው ልጆችን የሚቤዥ እንደመሆኑ መጠን ራሱን ለብዙዎች ቤዛ አድርጎ ሰጥቷል። (ማቴ. 20:28) ስለዚህ ኢየሱስ በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ያለውን አኗኗር መምራት የሚቻለው እንዴት እንደሆነ ከማሳየት ያለፈ ነገር አድርጓል። ይሖዋ ለሰው ዘር ባለው ዓላማ አፈጻጸም ረገድ ኢየሱስ ቁልፍ ሚና ይጫወታል። የአምላክን ሞገስ መልሰን ማግኘት የምንችለው በእሱ በኩል ብቻ ነው። (ሥራ 5:31፤ 2 ቆሮ. 5:18, 19) የኢየሱስ መሥዋዕታዊ ሞትና ትንሣኤው ታዛዥ የሆኑ የሰው ልጆች በሰማይ ባለው የአምላክ መንግሥት አገዛዝ አማካኝነት ዘላለማዊ በረከቶች ማግኘት የሚችሉበትን በር ከፍቷል።
4 ኢየሱስ ሊቀ ካህናት ስለሆነ ‘በድካማችን ሊራራልን’ ይችላል፤ እንዲሁም በምድር ላይ ያሉ ራሳቸውን ለአምላክ የወሰኑ ተከታዮቹ የሚሠሩትን ኃጢአት ያስተሰርይላቸዋል። ሐዋርያው ጳውሎስ “ያለን ሊቀ ካህናት በድካማችን ሊራራልን የማይችል አይደለምና፤ ከዚህ ይልቅ እንደ እኛው በሁሉም ረገድ የተፈተነ ሊቀ ካህናት አለን፤ ይሁንና እሱ ኃጢአት የለበትም” ሲል ገልጿል። ጳውሎስ በመቀጠል በኢየሱስ ክርስቶስ የሚያምኑ ሁሉ ከአምላክ ጋር እንዲታረቁ የሚያስችላቸውን ይህን ዝግጅት ሙሉ በሙሉ እንዲጠቀሙበት ለማበረታታት እንዲህ ብሏል፦ “እንግዲህ እርዳታ በሚያስፈልገን ጊዜ ምሕረትና ጸጋ እናገኝ ዘንድ ያለ ምንም ፍርሃት ወደ ጸጋው ዙፋን እንቅረብ።”—ዕብ. 4:14-16፤ 1 ዮሐ. 2:2
5 በተጨማሪም ኢየሱስ የክርስቲያን ጉባኤ ራስ ነው። በመጀመሪያው መቶ ዘመን እንደነበሩት እውነተኛ ተከታዮቹ ሁሉ እኛም ሰብዓዊ መሪ አያስፈልገንም። ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስና ብቃት ባላቸው የበታች እረኞች አማካኝነት አመራር ይሰጣል፤ እነዚህ እረኞች የአምላክን መንጋ ስለሚይዙበት መንገድ በእሱም ሆነ በሰማይ ባለው አባቱ ዘንድ ተጠያቂ ናቸው። (ዕብ. 13:17፤ 1 ጴጥ. 5:2, 3) ይሖዋ ኢየሱስን በተመለከተ “እነሆ፣ ለብሔራት ምሥክር፣ መሪና አዛዥ አድርጌዋለሁ” የሚል ትንቢት
-