የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የናሙና አቀራረቦችን እንዴት ልንጠቀምባቸው ይገባል?
    የመንግሥት አገልግሎት—2005 | ጥር
    • 5. በመንግሥት አገልግሎታችን ላይ ከሚወጣው የተለየ አቀራረብ መዘጋጀት የሚያስፈልገን ለምንድን ነው? እንዴትስ መዘጋጀት እንችላለን?

      5 አማራጭ አቀራረቦች:- በአገልግሎታችን ላይ መጠቀም የሚኖርብን ለናሙና የቀረቡትን መግቢያዎች ብቻ ነው? አይደለም። በይበልጥ የሚቀላችሁ ሌላ አቀራረብ ወይም ጥቅስ ካለ በእርሱ ተጠቀሙ። በተለይ መጽሔቶችን ስናበረክት በሽፋኑ ላይ ካለው ርዕስ ውጪ ለክልላችን ተስማሚ የሆኑ ሌሎች በመጽሔቱ ውስጥ የወጡ ርዕሶችን ለመጠቀም ንቁ መሆን ይኖርብናል። በአገልግሎት ስብሰባ ላይ በመስክ አገልግሎት የምንጠቀምባቸው አቀራረቦች በሠርቶ ማሳያ በሚቀርቡበት ወቅት ለጉባኤው የአገልግሎት ክልል ተስማሚ የሆነ ማንኛውንም አቀራረብ መጠቀም ይቻላል። ይህም ሁላችንም ምሥራቹን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመናገር እንድንችል ይረዳናል።

  • መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
    የመንግሥት አገልግሎት—2005 | ጥር
    • መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?

      መጠበቂያ ግንብ ኅዳር 1

      “ብዙ ሰዎች ሰብዓዊ መሪዎች በጊዜያችን ላሉት ችግሮች መፍትሔ ማስገኘት ይችላሉ የሚል እምነት የላቸውም። በእነዚህ ጥቅሶች ላይ የተነገሩትን ትንቢቶች ለመፈጸም የሚችል መሪ ይኖራል ብለው ያስባሉ? [መዝሙር 72:7, 12, 16ን አንብብ። ከዚያም መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ መጽሔት በትንቢቱ ላይ የተጠቀሰውን መሪ ማንነትና ምን ነገሮችን እንደሚያከናውን ያብራራል።”

      ንቁ! ኅዳር 2004

      “በዓለም አቀፍ ደረጃ ከአራት ሰዎች መካከል አንዱ በሕይወት ዘመኑ ውስጥ በሆነ ወቅት ላይ በአእምሮ ሕመም እንደሚጠቃ ይገመታል። አብዛኞቻችን በበሽታው የሚሰቃይ የምናውቀው ሰው ይኖራል። [ርዕሱን ገልጠህ አሳየው።] ይህ ርዕስ የቤተሰባችን አባል ወይም በቅርብ የምናውቀው ሰው በእንዲህ ዓይነት ሕመም ቢጠቃ ምን ማድረግ እንደሚኖርብን የሚገልጹ ጠቃሚ ሐሳቦች ይዟል።”

      መጠበቂያ ግንብ ኅዳር 15

      “ብዙ ሰዎች ጥሩ ጤና አግኝተው ረጅም ዕድሜ መኖር ይፈልጋሉ። የሚቻል ቢሆን እርስዎስ ለዘላለም መኖር ይፈልጋሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት። ከዚያም ዮሐንስ 17:3ን አንብብ።] ይህ መጽሔት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘውን የዘላለም ሕይወት ተስፋ የሚያብራራ ሲሆን ይህ ተስፋ እውን ሲሆን ሕይወት ምን እንደሚመስልም ይጠቁማል።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ