-
የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 41—ማርቆስ“ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው፣ ጥራዝ 16
-
-
እንደሆነና ሥልጣን ተሰጥቶት እንደመጣ የሚያረጋግጡ ናቸው። ከይሖዋ ባገኘው ሥልጣን “እንደ ባለ ሥልጣን” አስተምሯል፤ እዚህ ምድር ላይ ሳለ ዋነኛ ሥራው “የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለች” እያለ ‘የእግዚአብሔርን ወንጌል መስበክ’ እንደሆነ ጎላ አድርጎ ገልጿል። የኢየሱስን ትምህርት በሥራ ላይ ያዋሉ ሁሉ ይህ ነው የማይባል ጥቅም አግኝተዋል።— ማር. 1:22, 14, 15
32 ኢየሱስ፣ ደቀ መዛሙርቱን “ለእናንተ የእግዚአብሔር መንግሥት ምስጢር ተሰጥቶአችኋል” ብሏቸዋል። ማርቆስ “የእግዚአብሔር መንግሥት” የሚለውን አገላለጽ 14 ጊዜ የተጠቀመበት ሲሆን በመንግሥቱ አማካኝነት ሕይወት ማግኘት ለሚፈልጉ ሰዎች መመሪያ የሚሆኑ በርካታ መሠረታዊ ሥርዓቶችን ገልጿል። ኢየሱስ “ስለ እኔና ስለ ወንጌል ነፍሱን የሚያጠፋት ሁሉ . . . ያድናታል” ብሏል። ሕይወት እንዳናገኝ እንቅፋት የሚሆን ማንኛውም ነገር መወገድ ይኖርበታል:- “ሁለት ዐይን ኖሮህ ወደ ገሃነም ከመጣል፣ አንድ ዐይን ኖሮህ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት ይሻልሃል።” ከዚህም በተጨማሪ ኢየሱስ “የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደ ሕፃን የማይቀበል ሁሉ ከቶ አይገባባትም” እንዲሁም “ለሀብታሞች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንዴት ከባድ ነገር ነው!” በማለት ተናግሯል። ሁለቱን ታላላቅ ትእዛዛት መጠበቅ ከሚቃጠል መሥዋዕት ሁሉና ከሌሎችም መሥዋዕቶች እንደሚበልጥ ያስተዋለውን ሰው “ከእግዚአብሔር መንግሥት የራቅህ አይደለህም” ብሎታል። በማርቆስ ወንጌል ውስጥ የሚገኙት እነዚህና ሌሎች ከአምላክ መንግሥት ጋር የተያያዙ ትምህርቶች በዕለታዊ ሕይወታችን በሥራ ላይ ልናውላቸው የምንችላቸው በጣም ጠቃሚ የሆኑ ምክሮች ይዘዋል።— 4:11፤ 8:35፤ 9:43-48፤ 10:13-15, 23-25፤ 12:28-34
33 ሙሉው “የማርቆስ ወንጌል” በአንድ ወይም በሁለት ሰዓት ውስጥ ሊነበብ ይችል ይሆናል፤ አንባቢው እንዲህ በማድረግ ስለ ኢየሱስ አገልግሎት አስደሳች፣ ፈጣንና ሕያው የሆነ ክለሳ ማድረግ ይችላል። በመንፈስ አነሳሽነት የተጻፈውን ይህን ወንጌል በዚህ መልኩ በአንድ ጊዜ መውጣት እንዲሁም በጥልቀት ማጥናትና በዘገባው ላይ ማሰላሰል ምንጊዜም ቢሆን ጠቃሚ ነው። እንደ መጀመሪያው መቶ ዘመን ሁሉ በዛሬው ጊዜም የማርቆስ ወንጌል በስደት ላይ ላሉ ክርስቲያኖች ጠቃሚ ነው፤ በአሁኑ ጊዜ ክርስቲያኖች ‘በሚያስጨንቅ ጊዜ’ ውስጥ ስለሚኖሩ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ እንደሚገኘው ዘገባ ያለ ምሳሌያችን የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን አስመልክቶ በመንፈስ አነሳሽነት የተጻፈ መመሪያ ያስፈልጋቸዋል። የማርቆስን ወንጌል በማንበብ በዚህ ትኩረት የሚስብ ዘገባ እንድትደሰት እንዲሁም የእምነታችን ጀማሪና ፍጹም አድራጊ የሆነው ኢየሱስ ያገኘው ዓይነት የማይጠፋ ደስታ አግኝተህ የእሱን ፈለግ እንድትከተል እናበረታታሃለን። (2 ጢሞ. 3:1፤ ዕብ. 12:2) አዎን፣ ኢየሱስ የተግባር ሰው መሆኑን አስተውል፤ የእሱ ዓይነት ቅንዓት ይኑርህ፤ እንዲሁም በፈተና እና በተቃውሞ ወቅት ያሳየውን የማያወላውል የአቋም ጽናትና ድፍረት ኮርጅ። በመንፈስ አነሳሽነት ከተጻፈው ከዚህ የቅዱሳን መጻሕፍት ክፍል መጽናናት አግኝ። የዘላለም ሕይወት ለማግኘት በምታደርገው ጥረት ይህን ወንጌል ተጠቀምበት!
-
-
የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 42—ሉቃስ“ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው፣ ጥራዝ 16
-
-
የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 42—ሉቃስ
ጸሐፊው:- ሉቃስ
የተጻፈበት ቦታ:- ቂሣርያ
ተጽፎ ያለቀው:- ከ56–58 ከክ.ል.በኋላ ገደማ
ታሪኩ የሚሸፍነው ጊዜ:- ከ3 ከክ.ል.በፊት እስከ 33 ከክ. ል. በኋላ
የሉቃስን ወንጌል የጻፈው፣ ንቁ አእምሮ ያለው ደግ ሰው ነው፤ እነዚህ ግሩም ባሕርያት የአምላክ መንፈስ ከሚሰጠው አመራር ጋር ተጣምረው ጸሐፊው ትክክለኛና ሕያው የሆነ ዘገባ እንዲያቀርብ አስችለውታል። በመግቢያው ላይ “እኔም በበኩሌ ሁሉን ከመሠረቱ በጥንቃቄ ከመረመርሁ በኋላ፣ ታሪኩን ቅደም ተከተሉን በጠበቀ ሁኔታ ልጽፍልህ መልካም ሆኖ ታየኝ” ሲል ተናግሯል። ጸሐፊው በዝርዝርና በጥንቃቄ ያሰፈረው ይህ ዘገባ አባባሉ እውነት መሆኑን በሚገባ ያረጋግጣል።—ሉቃስ 1:3
2 በዚህ ወንጌል ውስጥ የሉቃስ ስም አንድም ቦታ ላይ ባይጠቀስም ጸሐፊው እሱ መሆኑን የጥንት ጸሐፊዎች ይስማማሉ። በሙራቶሪያን ቁርጥራጭ (170 ከክርስቶስ ልደት በኋላ ገደማ) ላይ ወንጌሉን የጻፈው ሉቃስ እንደሆነ ከመጠቀሱም ሌላ እንደ ኢራንየስና የእስክንድርያው ክሌመንት ያሉ የሁለተኛው መቶ ዘመን ጸሐፊዎችም በዚህ ሐሳብ ይስማማሉ። በወንጌሉ ውስጥም ጸሐፊው ሉቃስ መሆኑን የሚጠቁሙ ጠንካራ ማስረጃዎች ይገኛሉ። ጳውሎስ፣ በቈላስይስ 4:14 ላይ “የተወደደው ሐኪሙ ሉቃስ” ብሎ የጠራው ሲሆን የወንጌሉ አጻጻፍም ቢሆን እንደ ዶክተር ያለ ምሑር እንዳዘጋጀው ያስታውቃል። ሉቃስ ወንጌሉን የጻፈበት ቋንቋ ላቅ ያለ ደረጃ ያለው ከመሆኑም በላይ ሦስቱ የወንጌል ጸሐፊዎች ያሰፈሯቸው ቃላት አንድ ላይ ቢደመሩ እንኳ የማይተካከሏቸው ብዛት ያላቸው የተለያዩ ቃላትን ተጠቅሟል፤ ይህም በጣም አስፈላጊ የሆነውን ርዕሰ ጉዳይ ጥንቃቄ በተሞላበትና ሰፋ ባለ መንገድ ለማስፈር አስችሎታል። አንዳንዶች፣ ሉቃስ ስለ አባካኙ ልጅ ያሰፈረው ዘገባ እስከ ዛሬ ድረስ ከተጻፉት አጫጭር ታሪኮች ሁሉ ተወዳዳሪ የማይገኝለት እንደሆነ ይናገራሉ።
3 ሉቃስ፣ ከ300 የሚበልጡ የሕክምና ስያሜዎችን ወይም ከሕክምና ጋር የተያያዘ ፍቺ የሰጣቸውን ቃላት ተጠቅሟል፤
-