የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 4/08 ገጽ 1
  • ‘የምታመሰግኑ ሁኑ’

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ‘የምታመሰግኑ ሁኑ’
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “የምታመሰግኑ ሁኑ”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
  • ‘የምታመሰግኑ ሁኑ’
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
  • አመስጋኝ ነህን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
  • አድናቆታችንን መግለጽ ያለብን ለምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2019
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
km 4/08 ገጽ 1

‘የምታመሰግኑ ሁኑ’

1 ኢየሱስ ለምጽ የያዛቸውን አሥር ሰዎች በፈወሰበት ወቅት ምስጋናውን ለመግለጽ የተመለሰው አንዱ ብቻ ነበር። በመሆኑም ኢየሱስ “የነጹት ዐሥር ሰዎች አልነበሩምን? ታዲያ፣ ዘጠኙ የት ደረሱ?” በማለት ጠይቋል። (ሉቃስ 17:11-19) ለጋስና አፍቃሪ ከሆነው ከሰማዩ አባታችን ከይሖዋ ለምናገኘው በጎ ስጦታና ፍጹም በረከት ሁሉ አድናቂና አመስጋኝ መሆናችን ምንኛ አስፈላጊ ነው!—ቈላ. 3:15፤ ያዕ. 1:17

2 አመስጋኝ ልንሆንባቸው ከሚገቡን ነገሮች መካከል አንዳንዶቹ ምንድን ናቸው? አንደኛው፣ አምላክ ለሰው ልጆች ከሰጠው ስጦታ ሁሉ የላቀ የሆነው የቤዛው ዝግጅት ነው። (ዮሐ. 3:16) በተጨማሪም ይሖዋ ወደ እሱ ስለሳበን እናመሰግነዋለን። (ዮሐ. 6:44) አመስጋኝ እንድንሆን የሚያነሳሳን ሌላው ምክንያት ደግሞ ክርስቲያናዊ አንድነታችን ነው። (መዝ. 133:1-3) ከይሖዋ ያገኘናቸውን ሌሎች በርካታ ስጦታዎችንም መጥቀስ እንደምትችሉ ምንም ጥርጥር የለውም። ይሖዋ ያደረገላቸውን እንደረሱት ምስጋና ቢስ እስራኤላውያን መሆን በፍጹም አንፈልግም!—መዝ. 106:12, 13

3 አመስጋኝ መሆናችሁን አሳዩ:- ምንም እንኳ ለምጽ የያዛቸው አሥሩም ሰዎች ኢየሱስ ላደረገላቸው ነገር አድናቆት ሊኖራቸው ቢችልም አመስጋኝ መሆኑን ያሳየው ግን አንዱ ብቻ ነበር። (ሉቃስ 17:15) እኛም በተመሳሳይ በአገልግሎቱ በቅንዓት በመካፈል አመስጋኝ መሆናችንን እናሳይ። አፍቃሪው የሰማዩ አባታችን ላደረገልን ነገር ሁሉ አመስጋኞች ከሆንን ስለ እሱ በመናገር ፍቅሩንና ለጋስነቱን ለመኮረጅ ልባችን መገፋፋቱ አይቀርም። (ሉቃስ 6:45) ይሖዋ ‘ያደረገውን ድንቅ ነገርና ለእኛ ያለውን ሐሳብ’ ለሌሎች ስንናገር ለእሱ ያለን ፍቅርና አድናቆት እየጨመረ ይሄዳል።—መዝ. 40:5

4 ሌሎች አድናቆት እንዲያድርባቸው አድርጉ:- ልጆቻችንና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችን አድናቆት እንዲያድርባቸው ለመርዳት የሚያስችሉ አጋጣሚዎችን በመፈለግ ረገድ ንቁ ልንሆን ይገባል። ወላጆች ይህን ማድረግ የሚችሉባቸው በርካታ አጋጣሚዎች አሏቸው፤ ለምሳሌ ያህል፣ ስለ ይሖዋ የፍጥረት ሥራዎች ከልጆቻቸው ጋር በሚጨዋወቱበት ጊዜ አጋጣሚውን ሊጠቀሙበት ይችላሉ። (ሮሜ 1:20) የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ስንመራ የምናስጠናውን ግለሰብ፣ “ይህ ሐሳብ ስለ ይሖዋ ማንነት ምን የሚነግረን ነገር አለ?” በማለት ልንጠይቀው እንችላለን። መጽሐፍ ቅዱስ የምናስጠናው ሰው አድናቆቱ እየጨመረ በሄደ ቁጥር ለአምላክ ያለው ፍቅር የዚያኑ ያህል ያድጋል፤ እንዲሁም እሱን ለማስደሰት ያደረገው ቁርጥ ውሳኔ ይጠናከራል።

5 በዚህ በመጨረሻ ዘመን ብዙ ሰዎች አድናቆት የጎደላቸውና የማያመሰግኑ ሆነዋል። (2 ጢሞ. 3:1, 2) ይሖዋ፣ ለእሱ ያደሩ አገልጋዮቹ በአገልግሎቱ በቅንዓት በመካፈል አመስጋኝነታቸውን ሲያሳዩ ምንኛ ይደሰታል!—ያዕ. 1:22-25

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ