የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መከር ከመድረሱ በፊት “በእርሻው” ውስጥ መሥራት
    መጠበቂያ ግንብ—2000 | ጥቅምት 15
    • አይቀበልም ነበር። በሥላሴ አያምንም ነበር። ሆኖም ሊሞት እስከተቃረበበት ጊዜ ድረስ መንፈስ ቅዱስ አካል ይሁን አይሁን እርግጠኛ አልነበረም። ጆርጅ ስቶርዝ ክርስቶስ የሚመለሰው በማይታይ ሁኔታ ቢሆንም መጨረሻ ላይ በሚታይ ሁኔታ ይገለጣል ብሎ ያስብ ነበር። የሆነ ሆኖ ሁለቱም ሰዎች ልበ ቅኖች ነበሩ ለማለት ይቻላል። ከሌሎች በተሻለ ወደ እውነት ተጠግተዋል።

      ኢየሱስ ስለ ስንዴውና ስለ እንክርዳዱ በተናገረው ምሳሌ ላይ የጠቀሰው “እርሻው” ገና ለአጨዳ አልደረሰም ነበር። (ማቴዎስ 13:​38) ግሪው፣ ስቶርዝና ሌሎች ሰዎች ለመከሩ ሥራ አንዳንድ ሁኔታዎችን በማመቻቸት በ“እርሻው” ላይ ሲሠሩ ቆይተዋል።

      ይህን መጽሔት በ1879 ማሳተም የጀመረው ቻርልስ ቴዝ ራስል ቀደም ሲል ስላሳለፋቸው ዓመታት የሚከተለውን ጽፎ ነበር:- “ጌታ ቃሉን ስናጠና በእጅጉ ረድቶናል፤ እጅግ ተወዳጅ የሆነው አረጋዊው ወንድማችን ጆርጅ ስቶርዝ በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱት አንዱ ሲሆን በቃልም ሆነ በጽሑፍ ብዙ ረድቶናል። ሆኖም ‘እንደተወደዱ ልጆች የአምላክ ተከታዮች’ ለመሆን እንጂ የሰው ደቀ መዛሙርት ለመሆን አስበን አናውቅም።” አዎን፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ግሪውንና ስቶርዝን የመሰሉ ሰዎች ካደረጉት ጥረት ጥቅም ሊያገኙ ይችላሉ። አሁንም ቢሆን እውነት የሚፈልቅበት ትክክለኛው ምንጭ መጽሐፍ ቅዱስ በመሆኑ የአምላክን ቃል መመርመሩ እጅግ አስፈላጊ ነው።​—⁠ዮሐንስ 17:​17

  • የአንባብያን ጥያቄዎች
    መጠበቂያ ግንብ—2000 | ጥቅምት 15
    • የአንባብያን ጥያቄዎች

      መጽሐፍ ቅዱስ ደም ምን መደረግ እንዳለበት ከሚሰጠው መመሪያ አንጻር የይሖዋ ምሥክሮች የራስን ደም በመጠቀም ለሚከናወኑ የሕክምና አሠራሮች ያላቸው አመለካከት ምንድን ነው?

      በግል ምርጫ ወይም በአንዳንድ የሕክምና መመሪያዎች ላይ ብቻ ተመሥርቶ ከመወሰን ይልቅ እያንዳንዱ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ነገር በጥሞና መመርመር አለበት። ይህ በግለሰቡና በይሖዋ መካከል ያለ ጉዳይ ነው።

      የሕይወታችን ባለቤት የሆነው ይሖዋ ደም መበላት እንደሌለበት ደንግጓል። (ዘፍጥረት 9:​3, 4) ደም ሕይወትን ስለሚወክል አምላክ ለጥንቱ የእስራኤል ሕዝብ በሰጠው ሕግ በደም አጠቃቀም ላይ ገደብ አውጥቷል። “የሥጋ ሕይወት በደሙ ውስጥ ነውና፤ . . . በመሠዊያው ላይ ለነፍሳችሁ ማስተስረያ ይሆን ዘንድ እኔ ለእናንተ ሰጠሁት” ሲል ደንግጓል። አንድ ሰው ለምግብነት ብሎ እንስሳ ቢያርድስ? አምላክ “ደሙን ያፈስሳል በአፈርም ይከድነዋል” ብሏል።a (ዘሌዋውያን 17:​11, 13) ይሖዋ ይህን ትእዛዝ በተደጋጋሚ ተናግሯል። (ዘዳግም 12:​16, 24፤ 15:​23) ሶንሲኖ ሹማሽ የተባለው የአይሁዳውያን መጽሐፍ እንዲህ ይላል:- “ደሙ መቀመጥ የለበትም። ከዚህ ይልቅ ለመብልነት እንዳይውል ምድር ላይ መፍሰስ አለበት።” ማንኛውም እስራኤላዊ ሕይወቱ የአምላክ ንብረት የሆነውን የሌላ ፍጡር ደም መውሰድ፣ ማስቀመጥ ወይም መጠቀም አይችልም ነበር።

      መሲሑ ሲሞት የሙሴን ሕግ የመጠበቁ ግዴታ አከተመ። ሆኖም አምላክ ለደም ቅድስና ያለው አመለካከት አልተለወጠም። ሐዋርያት በአምላክ ቅዱስ መንፈስ ተመርተው ክርስቲያኖች ‘ከደም እንዲርቁ’ አዝዘዋል። ይህ ትእዛዝ እንደ ቀላል ነገር የሚታይ አልነበረም። ትእዛዙ ከሥነ ምግባር አንጻር ሲታይ ከጾታ ብልግና ወይም ከጣዖት አምልኮ የመራቅን ያህል አስፈላጊ ነበር። (ሥራ 15:​28, 29፤ 21:​25) ደም መስጠትም ሆነ መውሰድ በ20ኛው መቶ ዘመን የተለመደ እየሆነ ሲመጣ የይሖዋ ምሥክሮች ይህ ተግባር ከአምላክ ቃል ጋር እንደሚቃረን ተገነዘቡ።b

      አልፎ አልፎ አንድ ዶክተር አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ የራሱን የታካሚውን ደም መልሶ መስጠት ይችል ዘንድ ቀዶ ሕክምና ከመከናወኑ ከሳምንታት በፊት ታካሚው የራሱን ደም እንዲሰጥ (ከቀዶ ሕክምና በፊት የራስን ደም መለገስ ወይም ፒ ኤ ዲ) ያሳስበዋል። ይሁን እንጂ እንዲህ ዓይነቱ ደምን የመውሰድ፣ የማስቀመጥና የመስጠት ልማድ ዘሌዋውያንና ዘዳግም ላይ የሠፈረውን ሕግ በቀጥታ ይቃረናል። ደም መቀመጥ የለበትም፤ ከዚህ ይልቅ ምድር ላይ መፍሰስ አለበት። ይህም በምሳሌያዊ አነጋገር ወደ አምላክ የተመለሰ ያህል ነው። በአሁኑ ጊዜ የሙሴ ሕግ የተሻረ መሆኑ እውነት ነው። ሆኖም የይሖዋ

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ