-
መጽሐፍ ቅዱስከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
-
-
ቋንቋ ሐሳብ ጋር የሚቀራረቡ መሆናቸው የታወቀ ነው። በቀላል አተረጓጐም የተዘጋጁ ዘመናዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች የመጀመሪያውን ትርጉም እስከ መለወጥ የደረሱበት ጊዜ አለ። ጥቂት ተርጓሚዎች ደግሞ የግል እምነታቸውን በትርጉማቸው ላይ እንዲንጸባረቅ አድርገዋል። ይሁን እንጂ እነዚህን ስህተቶች ከተለያዩ ትርጉሞች ጋር በማስተያየት ማረም ይቻላል።
አንድ ሰው እንዲህ ቢልስ:-
‘በመጽሐፍ ቅዱስ አላምንም’
እንዲህ በማለት ልትመልስ ትችላለህ:- ‘አምላክ እንዳለ ያምናሉ፣ አይደለም? . . . እንግዲያው አንድ ጥያቄ እንድጠይቅዎ የሚፈቅዱልኝ ከሆነ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመቀበል ያስቸገረዎት ነገር ምንድን ነው?’
ወይም እንዲህ ማለት ትችላለህ:- ‘ከመጀመሪያው ጀምሮ የሚሰማዎት እንዲህ ነበር? . . . አንዳንድ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን በጥልቀት ሳያጠኑ በመጽሐፍ ቅዱስ አላምንም ብለው ሲናገሩ እሰማለሁ። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ ከአምላክ የተላከ መልእክት እንደሆነ ብናምንበትና እርሱን ብንከተል የዘላለም ሕይወት እንደምናገኝ በግልጽ ስለሚናገር መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው እውነት መሆኑንና አለመሆኑን መርምረን ማወቅ ጠቃሚ የሚሆን አይመስልዎትም? (ከገጽ 58–62 ባለው ሐሳብ ተጠቀም።)’
‘መጽሐፍ ቅዱስ እርስ በርሱ ይጋጫል’
እንዲህ በማለት ልትመልስ ትችላለህ:- ‘ሌሎች ሰዎችም እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ። ይሁን እንጂ አንዳቸውም ቢሆኑ እርስ በርስ የሚቃረኑትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳቦች ሊያሳዩኝ አልቻሉም። እኔ በግሌ መጽሐፍ ቅዱስ በማነብበት ጊዜ አንድም የሚጋጭ ሐሳብ አላገኘሁም። እርስዎ አንድ ምሳሌ ሊሰጡኝ ይችላሉ?’ ከዚያም ምናልባት እንዲህ በማለት ልትቀጥል ትችላለህ:- ‘እርግጥ ብዙ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ በአእምሯቸው ለፈጠረባቸው ጥያቄ መልስ ለማግኘት እንዳልቻሉ ተረድቻለሁ። ለምሳሌ ያህል ቃየን ሚስት ከየት አገኘ? እንደሚለው ያሉት ሊሆኑ ይችላሉ። (በገጽ 301 ላይ ባለው ሐሳብ ተጠቀም።)’
‘መጽሐፍ ቅዱስን የጻፉት ሰዎች ናቸው’
እንዲህ በማለት ልትመልስ ትችላለህ:- ‘እውነት ነው። 40 የሚያክሉ ሰዎች በዚህ ሥራ ተካፍለዋል። ይሁን እንጂ መጽሐፉ የተጻፈው በአምላክ መንፈስ አነሣሽነት ነው።’ ከዚያም ምናልባት እንዲህ በማለት ልትቀጥል ትችላለህ:- (1) ‘እንደዚህ ሲባል ምን ማለት ነው? አንድ ሥራ አስኪያጅ ጸሐፊው ደብዳቤ እንድትጽፍለት እንደሚያደርግ ሁሉ አምላክም መጽሐፍ ቅዱስን ለማስጻፍ በሰዎች ተጠቅሟል ማለት ነው።’ (2) ‘በሰማያት ከሚኖር አንድ ሕያው አካል መልእክት እንዴት ሊመጣ ይችላል ብለን ልንገረም አይገባም። ሰዎች እንኳ ጨረቃ ላይ ሆነው መልእክቶችና ፎቶግራፎች ወደ መሬት ልከዋል። ይህን እንዴት ሊያደርጉ ቻሉ? ከብዙ ዘመን በፊት አምላክ በፈጠራቸው ሕጎች በመጠቀም ነው።’ (3) ‘ይሁን እንጂ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለው ሐሳብ ከአምላክ የተገኘ ለመሆኑ እንዴት እርግጠኞች ልንሆን እንችላለን? ከሰው ሊገኝ የማይችል ሐሳብ ስለያዘ ነው። እንዴት ያሉ ሐሳቦችን ይዟል? ወደፊት የሚፈጸሙ ሁኔታዎችን በዝርዝር ይገልጻል። እነዚህም ሙሉ በሙሉ በትክክል መፈጸማቸው በየጊዜው ተረጋግጧል። (ለምሳሌ ገጽ 58–60፤ እንዲሁም ከገጽ 234–238 “የመጨረሻ ቀኖች” በሚለው ርዕስ ሥር ያለውን ተመልከት።)’
‘እያንዳንዱ ሰው መጽሐፍ ቅዱስን እንዳሻው ይተረጉመዋል’
እንዲህ በማለት ልትመልስ ትችላለህ:- ‘ቢሆንም ሁሉም አተረጓጐም ትክክለኛ ሊሆን እንደማይችል የታወቀ ነው።’ ከዚያም ምናልባት እንዲህ በማለት ልትቀጥል ትችላለህ:- (1) ‘አንድ ሰው ቅዱሳን ጽሑፎች የሚናገሩትን ከራሱ ሐሳብ ጋር ለማስማማት ሲል ማጣመሙ ዘላለማዊ ጉዳት ሊያስከትልበት ይችላል። (2 ጴጥ. 3:15, 16)’ (2) ‘መጽሐፍ ቅዱስን በትክክል ለመረዳት ሁለት ነገሮች ሊረዱን ይችላሉ። በመጀመሪያ ከጥቅሱ ፊት ኋላ (በዙሪያው) ያለውን ሐሳብ መመርመር። ቀጥሎ ጥቅሱን ከርዕሰ ጉዳዩ ጋር ዝምድና ካላቸው ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ጋር ማወዳደር። ይህን ካደረግን የአምላክ ቃል አስተሳሰባችንን እንዲመራ ፈቀድንለታል ማለት ነው፤ ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች የምንሰጠው ትርጉሙም የእኛ ሳይሆን የአምላክ ይሆናል። የመጠበቂያ ግንብ ጽሑፎች የሚከተሉት ይህንን ዘዴ ነው።’ (ገጽ 205, 206 “የይሖዋ ምሥክሮች” በሚለው ርዕስ ሥር ያለውን ተመልከት።)
‘ለዘመናችን አያገለግልም’
እንዲህ በማለት ልትመልስ ትችላለህ:- ‘ሁላችንም በዛሬው ጊዜ ሊሠሩ የሚችሉ ነገሮችን እንወዳለን፤ አይደለም እንዴ?’ ከዚያም ምናልባት እንዲህ በማለት ልትቀጥል ትችላለህ:- (1) ‘ጦርነትን ማጥፋት ጠቃሚ ነገር ነው ቢባል አይስማሙም? . . . ሰዎች ከሌሎች ብሔራት ሕዝቦች ጋር በሰላም አብረው መኖር ቢማሩ መልካም ጅምር የሚሆን አይመስልዎትም? . . . መጽሐፍ ቅዱስ ወደፊት እንዲህ ይሆናል ሲል አስቀድሞ ተናግሯል። (ኢሳ. 2:2, 3) ዛሬ እየተካሄደ ባለው መጽሐፍ ቅዱስን የማስተማር ዘመቻ ምክንያት ይህ ሁኔታ በይሖዋ ምሥክሮች ላይ እየተፈጸመ ነው።’ (2) ‘ከዚህም የበለጠ ነገር ያስፈልጋል:- ለጦርነት መንስኤ የሆኑት ሰዎችና ብሔራት በሙሉ መወገድ አለባቸው። ታዲያ ይህ ሊሆን የሚችል ነገር ነው? አዎን ነው፤ ይህ እንዴት ሊሆን እንደሚችል መጽሐፍ ቅዱስ ይገልጽልናል። (ዳን. 2:44፤ መዝ. 37:10, 11)’
ወይም እንዲህ ማለት ትችላለህ:- ‘ይህ ነገር ለምን እንዳሳሰበዎት ይገባኛል። ለመመሪያነት የተዘጋጀ መጽሐፍ መመሪያዎቹ ምንም የማይሠሩ ከሆነ በዚህ መጽሐፍ መጠቀም ሞኝነት ይሆናል፤ አይደለም እንዴ?’ ከዚያም ምናልባት እንዲህ በማለት ልትቀጥል ትችላለህ:- ‘ደስተኛ የቤተሰብ ኑሮ እንዲኖረን የሚያስችል ጥሩ ምክር የሚሰጥ መጽሐፍ ለጊዜያችን ይሠራል ቢባል አይስማሙም? . . . ደስተኛ የቤተሰብ ኑሮ ያስገኛሉ የሚባሉት ሐሳቦችና ልማዶች በየጊዜው ይለዋወጣሉ። ጥሩ ውጤት አለማስገኘታቸውንም ዛሬ ከምናየው ሁኔታ ለመረዳት እንችላለን። መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን ምክር የሚያውቁና በሥራ ላይ ለማዋል የሚጥሩ ሰዎች ግን ጽኑና ደስተኛ ቤተሰብ አላቸው። (ቆላ. 3:12–14, 18–21)’
‘መጽሐፍ ቅዱስ ጥሩ መጽሐፍ ነው፤ ግን ሙሉ በሙሉ እውነት ነው የሚባል ነገር ሊኖር አይችልም’
እንዲህ በማለት ልትመልስ ትችላለህ:- ‘እያንዳንዱ ሰው የተለያየ ሐሳብ ሊኖረው የሚችል መሆኑ እውነት ነው። አንድ ሰው አንድን ነገር እንዳወቀ ቢሰማውም ብዙውን ጊዜ ገና ያልመረመረው ቢያንስ አንድ ሌላ ጉዳይ ያገኛል። ነገር ግን እንደዚህ ያለ የእውቀት ውስንነት የሌለበት አንድ አካል አለ። ማን ይሆን? . . . አዎ፣ የጽንፈ ዓለሙ ፈጣሪ ነው።’ ከዚያም ምናልባት እንዲህ በማለት ልትቀጥል ትችላለህ:- (1) ‘ኢየሱስ ክርስቶስ “ቃልህ እውነት ነው” ያለው ለዚህ ነው። (ዮሐ. 17:17) ይህ እውነት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይገኛል። (2 ጢሞ. 3:16, 17)’ (2) ‘አምላክ በድንቁርና እንድንደናበር አይፈልግም፤ እርሱ ለእኛ ያለው ፈቃድ የእውነትን ትክክለኛ እውቀት እንድናገኝ መሆኑን ተናግሯል። (1 ጢሞ. 2:3, 4) መጽሐፍ ቅዱስ አጥጋቢ በሆነ መንገድ እንዲህ ለመሰሉት ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል:- . . .’ (አንዳንድ ሰዎችን ለመርዳት ሲባል በመጀመሪያ አምላክ እንዳለ ለማመን በሚያስችሉት መረጃዎች ላይ መወያየት ያስፈልግህ ይሆናል። ከገጽ 146–152 “አምላክ” በሚለው ርዕስ ሥር ተመልከት።)
‘መጽሐፍ ቅዱስ የነጮች መጽሐፍ ነው’
እንዲህ በማለት ልትመልስ ትችላለህ:- ‘ነጮች ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎችን ማሳተማቸው እውነት ነው። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ አንዱ ዘር ከሌላው ዘር የተሻለ ነው አይልም።’ ከዚያም ምናልባት እንዲህ በማለት ልትቀጥል ትችላለህ:- (1) ‘መጽሐፍ ቅዱስ ከአምላክ የመጣ ነው፣ አምላክ ደግሞ ለማንም አያዳላም። (ሥራ 10:34, 35)’ (2) ‘የአምላክ ቃል የሁሉም አገር ሕዝቦችና ነገዶች በዚህች ምድር ላይ በአምላክ መንግሥት ሥር ለዘላለም የመኖር አጋጣሚ እንዳላቸው ይናገራል። (ራእይ 7:9, 10, 17)’
ወይም እንዲህ ማለት ትችላለህ:- ‘በፍጹም አይደለም! ስድሳ ስድስቱን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በመንፈስ አነሣሽነት የጻፉትን ሰዎች የመረጠው የሰው ልጆች ፈጣሪ ነው። ነጭ የቆዳ ቀለም ባላቸው ሰዎች ለመጠቀም ከመረጠ ይህ የእርሱ ኃላፊነት ነው። ነገር ግን የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት ለነጮች ብቻ የተወሰነ አይደለም።’ ከዚያም ምናልባት እንዲህ በማለት ልትቀጥል ትችላለህ:- (1) ‘ኢየሱስ የተናገረውን ልብ ይበሉ . . . (ዮሐ. 3:16) “ሁሉ” የሚለው አባባል የትኛውንም ዓይነት የቆዳ ቀለም ያላቸውን ሰዎች ይጨምራል። ከዚህም ሌላ ኢየሱስ ወደ ሰማይ ከማረጉ በፊት ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ የሚል የመሰነባበቻ ንግግር አድርጎላቸው ነበር:- . . . (ማቴ. 28:19)’ (2) ‘እንዲያውም የሐዋርያት ሥራ 13:1 ኔጌር ስለተባለ አንድ ሰው ይናገራል። የዚህ ሰው ስም ትርጉም “ጥቁር” ማለት ነው። እሱም በሦሪያ ግዛት የአንጾኪያ ጉባኤ ውስጥ ነቢያትና አስተማሪዎች ከነበሩት አንዱ ነበር።’
‘እኔ የማምነው የኪንግ ጄምስን የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ብቻ ነው’
እንዲህ በማለት ልትመልስ ትችላለህ:- ‘የራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ በቅርብ ካለ ከእርሱ ውስጥ ያገኘሁትን አንድ በጣም የሚያበረታታ ነገር ብነግርዎት ደስ ይለኛል።’
ወይም እንዲህ ማለት ትችላለህ:- ‘ብዙ ሰዎች በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ይጠቀማሉ። እኔም በግሌ ይህ ትርጉም አለኝ።’ ከዚያም ምናልባት እንዲህ በማለት ልትቀጥል ትችላለህ:- (1) ‘መጽሐፍ ቅዱስ በመጀመሪያ የተጻፈው በዕብራይስጥ፣ በአረማይክና በግሪክኛ ቋንቋዎች እንደነበረ ያውቁ ነበር? . . . በእነዚህ ቋንቋዎች የተጻፉትን ማንበብ ይችላሉ? . . . ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ወደ አማርኛ ቋንቋ በመተርጎሙ አመስጋኞች ነን።’ (2) ‘ይህ ሰንጠረዥ (በአዓት ላይ ያለው “የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት የተዘረዘሩበት ሰንጠረዥ”) የመጀመሪያው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የዘፍጥረት መጽሐፍ ተጽፎ ያለቀው በ1513 ከዘአበ እንደነበረ ያሳያል። የዘፍጥረት መጽሐፍ ከተጻፈ በኋላ ሙሉው መጽሐፍ ቅዱስ ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ እስከሚተረጐም 2, 900 ዓመታት እንዳለፉ ያውቁ ነበር? የኪንግ ጄምስ ትርጉም የተጠናቀቀው ተጨማሪ 200 ዓመታት ካለፉ በኋላ ነው። (በ1611 እዘአ)’ (3) ‘ከ17ኛው መቶ ዘመን ወዲህ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ብዙ ለውጦችን አድርጓል። በዘመናችንም እንኳ ይህን ለማየት ችለናል። አይደለም እንዴ? . . . ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጹትን እውነቶች ዛሬ በምንናገረው ቋንቋ የሚያቀርቡልንን ዘመናዊ ትርጉሞች በደስታ እንቀበላቸዋለን።’
‘እናንተ የራሳችሁ መጽሐፍ ቅዱስ አላችሁ’
“የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም” የሚለውን ዋና ርዕስ ተመልከት።
-
-
የልደት ቀንከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
-
-
የልደት ቀን
ፍቺ:- አንድ ሰው የተወለደበት ቀን ወይም ልደቱ የሚከበርበት ቀን የልደት ቀን ይባላል። በአንዳንድ ሥፍራዎች የልደት ቀን በተለይም ሕፃናት የተወለዱበት ቀን በድግስና ስጦታ በመስጠት ይከበራል። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ልማድ አይደለም።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ ልደት ቀን መከበር የሚናገሩት ጥቅሶች ነገሩ ጥሩ ልማድ መሆኑን ያመለክታሉን? መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ልደት ቀን መከበር የሚገልጸው ሁለት ጊዜ ብቻ ነው:-
ዘፍ. 40:20–22:- “በሦስተኛውም ቀን ፈርዖን የተወለደበት ቀን ነበረ፣ . . . ግብር አደረገ . . . የጠጅ አሳላፊዎቹንም አለቃ ወደ ስፍራው መለሰው፣ . . . የእንጀራ አበዛዎቹንም አለቃ ሰቀለው።”
ማቴ. 14:6–10:- “ሄሮድስ የተወለደበት ቀን በሆነ ጊዜ፣ የሄሮድያዳ ልጅ በመካከላቸው ዘፈነች ሄሮድስንም ደስ አሰኘችው፤ ስለዚህም የምትለምነውን ሁሉ እንዲሰጣት በመሐላ ተስፋ አደረገላት። እርስዋም በእናትዋ ተመክራ:- የመጥምቁ የዮሐንስን ራስ በወጭት ስጠኝ አለችው። . . . ልኮም የዮሐንስን ራስ በወህኒ አስቆረጠው።”
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጽፎ የሚገኝ ማናቸውም ነገር ያለ ምክንያት አይጻፍም። (2 ጢሞ. 3:16, 17) የይሖዋ ምሥክሮች የአምላክ ቃል የልደት ቀን ማክበርን እንደ ጥሩ ልማድ አድርጎ እንደማያቀርበው ስለሚገነዘቡ ከዚህ አድራጎት ይርቃሉ።
የጥንት ክርስቲያኖችና በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን ይኖሩ የነበሩ አይሁዶች የልደት ቀን አከባበርን እንዴት ይመለከቱት ነበር?
“የልደት ቀንን የማክበር ሐሳብ በጥንት ክርስቲያኖች ዘንድ አይታወቅም
-