የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ይሁዳ ባድማ ሆና ቆይታለች?
    መጠበቂያ ግንብ—2006 | ኅዳር 15
    • ይሁዳ ባድማ ሆና ቆይታለች?

      መጽሐፍ ቅዱስ፣ ይሁዳ በባቢሎናውያን እንደምትጠፋና አይሁዳውያን ከምርኮ እስኪመለሱ ድረስ ባድማ ሆና እንደምትቆይ ተናግሮ ነበር። (ኤርምያስ 25:8-11) ይህ ትንቢት ለመፈጸሙ ጠንካራ ማስረጃ የሚሆነው ወደ ትውልድ አገራቸው ከተመለሱት ምርኮኞች መካከል የመጀመሪያው ቡድን ይሁዳ ከደረሰ ከ75 ዓመታት በኋላ በመንፈስ አነሳሽነት የተጻፈው ታሪካዊ ዘገባ ነው። ዘገባው የባቢሎን ንጉሥ “ከሰይፍ የተረፉትን ቅሬታዎች በምርኮ ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው፤ እስከ ፋርስ መንግሥት መነሣትም ድረስ የእርሱና የልጆቹ አገልጋዮች ሆኑ” ይላል። ምድሪቱን በተመለከተ ደግሞ “የሰንበት ዕረፍት አገኘች፤ . . . ባድማ በነበረችበት ዘመን ሁሉ ዐረፈች” ተብሏል። (2 ዜና መዋዕል 36:20, 21) ይህንን የሚደግፍ አርኪኦሎጂያዊ ማስረጃ ይኖር ይሆን?

      በሂብሪው ዩኒቨርሲቲ የጳለስጢና ምድር የአርኪኦሎጂ ፕሮፌሰር የሆኑት ኤፍሬም ስተርን ቢብሊካል አርኪኦሎጂ ሪቪው በተባለው መጽሔት ላይ እንዲህ ብለዋል:- “አሦራውያንም ሆኑ ባቢሎናውያን የጥንቷን እስራኤል አብዛኛውን ክፍል አውድመዋል፤ ሆኖም አሦራውያን ድል ካደረጓት በኋላና ከባቢሎናውያኑ ድል በኋላ የነበረው ሁኔታ ፈጽሞ የተለያየ እንደነበረ አርኪኦሎጂያዊ መረጃዎች በግልጽ ያሳያሉ።” አክለውም እንዲህ ሲሉ ገልጸዋል:- “አሦራውያን የጳለስጢናን ምድር ከያዙ በኋላ ስለነበረው ሁኔታ የሚያሳይ ግልጽ ማስረጃ አለ፤ የሚያስገርመው ግን ባቢሎናውያን ምድሪቱን ካጠፉ በኋላ በዚያ የነበረውን ሁኔታ የሚጠቁም መረጃ አለመኖሩ ነው። . . . እስከ ፋርሳውያን ዘመን ድረስ በዚያ የሰፈሩ ሰዎች መኖራቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ አላገኘንም። . . . በምድሪቱ የሚኖሩ ሰዎች እንደነበሩ የሚያመለክት ምንም ነገር የለም። በእነዚህ ጊዜያት ሁሉ ባቢሎናውያን ያጠፉት አንድም ከተማ እንደገና ሕዝብ አልሰፈረበትም።”

      የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ሎውረንስ ስቴጀር በዚህ ሐሳብ ይስማማሉ። የባቢሎናውያን ነገሥታት “የያዙትን ምድር ሙሉ በሙሉ የማውደም ፖሊሲ ስለነበራቸው፣ በመላው ፍልስጥኤም በኋላም በመላው ይሁዳ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምዕራብ ያለው ምድር ባድማ ሊሆን ችሏል” ሲሉ ተናግረዋል። አክለውም “በርካታ አይሁዳውያን ግዞተኞች ወደ ትውልድ አገራቸው ተመልሰው እንደገና በሰፈሩባቸው በኢየሩሳሌምና በይሁዳ . . . የተገኙት አርኪኦሎጂያዊ ማስረጃዎች ባቢሎናውያንን ድል ያደረገው የፋርሱ ንጉሥ ታላቁ ቂሮስ መግዛት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ያለውን ሁኔታ ብቻ የሚጠቁሙ ናቸው” ብለዋል።

      ይሁዳ ባድማ እንደምትሆን ይሖዋ የተናገረው ቃል በእርግጠኝነት ተፈጽሟል። ይሖዋ አምላክ የሚናገረው ማንኛውም ትንቢት ምንጊዜም ተፈጻሚነቱን ያገኛል። (ኢሳይያስ 55:10, 11) በመሆኑም በይሖዋና በቃሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተመዝግበው በሚገኙት ተስፋዎች ላይ ሙሉ እምነት ማሳደር እንችላለን።—2 ጢሞቴዎስ 3:16

  • መጥተን እንድናነጋግርዎ ይፈልጋሉ?
    መጠበቂያ ግንብ—2006 | ኅዳር 15
    • መጥተን እንድናነጋግርዎ ይፈልጋሉ?

      በዚህ በመከራ በተሞላ ዓለምም እንኳ ስለ አምላክ፣ ስለ መንግሥቱና ለሰው ልጆች ስላለው አስደናቂ ዓላማ ትክክለኛ የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት በማግኘት ደስተኛ መሆን ይችላሉ። ተጨማሪ መረጃ ብንሰጥዎ ደስ የሚልዎት ከሆነ ወይም አንድ የይሖዋ ምሥክር መጥቶ እንዲያነጋግርዎትና መጽሐፍ ቅዱስን ያለ ክፍያ እንዲያስተምርዎ የሚፈልጉ ከሆነ የይሖዋ ምሥክሮች፣ የፖ. ሣ. ቁ. 5522፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ብለው ወይም በገጽ 2 ላይ ካሉት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው ይጻፉ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ