መዝሙር 21
መሐሪዎች ደስተኞች ናቸው
በወረቀት የሚታተመው
(ማቴዎስ 5:7)
1. መሐሪዎች ደስተኞች፣
ናቸው በአምላክ ፊት ውቦች።
ያምላክን ምሕረት ከቃሉ፣
ለቅኖች ይናገራሉ።
ያምላክ መሐሪነት ታይቷል፤
ቤዛው ምሥክር ይሆናል።
የኛን አፈር መሆን ያውቃል፤
ይህን አይቶ ይምረናል።
2. የሚምሩ ተባርከዋል፤
ኃጢያታቸው ይሰረዛል።
በ’የሱስ አማላጅነት፣
አግኝተዋልና ምሕረት።
ቃሉን የትም ይሰብካሉ፤
ምሕረቱን ያሳውቃሉ።
“መንግሥቱ ቀርቧል” እያሉ፣
ሰውን ሁሉ ያጽናናሉ።
3. ይሖዋ ሲፈርድላቸው፣
ያያሉ ’ንደሚወዳቸው።
ስለሚምሩ የእውነት፣
ያገኛሉ የሱን ምሕረት።
ለሰዎች ምሕረት እናሳይ፤
እናዳብረው ይህን ጠባይ።
ይሖዋንና ’የሱስን፣
’ንምሰል መሐሪ በመሆን።