በሳምንቱ መሃል በሚደረጉ ስብሰባዎች ላይ የተደረጉ ማስተካከያዎች
መስከረም 3 ከሚጀምረው ሳምንት አንስቶ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚወስደው ጊዜ ከ25 ወደ 30 ደቂቃ ይራዘማል። ጥናቱን የሚመራው ወንድም፣ በመግቢያው ላይ በአንድ ደቂቃ ውስጥ ያለፈውን ሳምንት ትምህርት መከለስ ይኖርበታል። በሌላ በኩል ደግሞ የአገልግሎት ስብሰባ ከ35 ወደ 30 ደቂቃ ያጥራል። ከእንግዲህ ወዲህ ለማስታወቂያዎች የተለየ ክፍል አይኖርም። ከዚህ ይልቅ ማንኛውም ማስታወቂያ መቅረብ ያለበት በመጀመሪያው የአገልግሎት ስብሰባ ክፍል መግቢያ ላይ ይሆናል። አብዛኛውን ጊዜ የተወሰኑ ማስታወቂያዎችን (ላይኖርም ይችላል) መናገሩ በቂ ሊሆን ይችላል፤ በአገልግሎት ስብሰባ ላይ የሚቀርቡትን ክፍሎች አስቀድሞ ማስተዋወቅ አያስፈልግም። በተጨማሪም የመስክ አገልግሎት ዝግጅቶችን፣ ጽዳትንና ሰላምታዎችን አስመልክቶ ማስታወቂያ መነገር የለበትም። (km 10/08 ገጽ 1 አን. 4) ረጅም ማስታወቂያ የሚኖር ከሆነ በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ክፍል ያላቸው ወንድሞች ክፍላቸውን ማሳጠር እንዲችሉ ቀደም ብሎ ቢነገራቸው ጥሩ ነው።