-
ትንቢትከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
-
-
እንዲህ በማለት ልትመልስ ትችላለህ:- ‘የኢየሱስ ክርስቶስን ሚና መገንዘብና መቀበል በእርግጥም አስፈላጊ ነው። ይሁን እንጂ በመጀመሪያው መቶ ዘመን አይሁድ ኢየሱስን እንዳይቀበሉ ዕንቅፋት ከሆኑባቸው ነገሮች አንዱ ለትንቢቶች ተገቢ ትኩረት አለመስጠታቸው እንደሆነ ያውቃሉ?’ ከዚያም ምናልባት እንዲህ በማለት ልትቀጥል ትችላለህ:- (1) ‘በዕብራይስጥ በተጻፉት ቅዱሳን ጽሑፎች የሚገኙ ትንቢቶች መሲሑ (ክርስቶስ) መቼ እንደሚገለጥ ምን እንደሚያደርግ ተንብየው ነበር። ይሁን እንጂ አይሁዳውያን በአጠቃላይ እነዚህ ትንቢቶች ለሚናገሯቸው ነገሮች ትኩረት አልሰጡም። መሲሑ ምን እንደሚያደርግና ምን ማድረግ እንደሚገባው የራሳቸው አስተሳሰብ ስለነበራቸው የአምላክን ልጅ ሳይቀበሉ ቀሩ። (ገጽ 212, 213 ላይ “ኢየሱስ ክርስቶስ” በሚለው ርዕስ ሥር ተመልከት።)’ (2) ‘ዛሬ የምንኖረው ክርስቶስ ሰማያዊ ንጉሥ ሆኖ በሚገዛበትና አሕዛብን ሁሉ ለሕይወት አለዚያም ለጥፋት በየወገናቸው በሚለይበት ዘመን ላይ ነው። (ማቴ. 25:31–33, 46) አብዛኞቹ ሰዎች ግን የሚጠብቁት ከዚህ የተለየ ነገር ነው።’
ወይም እንዲህ ማለት ትችላለህ:- ‘ጥሩ ክርስቲያን መሆን አስፈላጊ እንደሆነ እኔም እስማማለሁ። ይሁን እንጂ ኢየሱስ ያስተማራቸውን አንዳንድ ነገሮች እየፈጸምኩ በሕይወታችን ቅድሚያ ልንሰጣቸው የሚገቡትን ነገሮች ችላ ብል ጥሩ ክርስቲያን እሆናለሁ? . . . እዚህ ማቴዎስ 6:33 ላይ የተመዘገበውን የኢየሱስ ቃል ልብ ይበሉ።’ ከዚያም ምናልባት እንዲህ በማለት ልትጨምር ትችላለህ:- ‘ኢየሱስ ስለዚህች መንግሥት እንድንጸልይ አስተምሮን የለም? እንዲያውም ኢየሱስ አዳኛችን መሆኑን በማመናችን ምክንያት ከምናገኘው የኃጢአት ሥርየት እንኳን አስቀድመን ስለዚህች መንግሥት እንድንጸልይ አስተምሮ የለም? (ማቴ. 6:9–12)’
-
-
መንጽሔከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
-
-
መንጽሔ
ፍቺ:- “መንጽሔ [የሮማ ካቶሊክ] ቤተ ክርስቲያን እንደምታስተምረው በጸጋ የሞቱ ግን ገና ካለፍጽምናቸው ሙሉ በሙሉ ያልነጹ ነፍሳት ይቅርታ ላላገኙባቸው ቀላል ኃጢአቶች ንስሐ የሚገቡበት ወይም ለሠሯቸው ቀላል ግን ሞት የሚገባቸው ኃጢአቶች ጊዜአዊ ቅጣት የሚቀበሉበትና ወደ ሰማይ ከመግባታቸው በፊት የሚነጹበት በወዲያኛው ዓለም ውስጥ የሚገኝ ሁኔታ ወይም ቦታ ነው።” (ኒው ካቶሊክ ኢንሳይክሎፔድያ፣ 1967፣ ጥራዝ 11፣ ገጽ 1034) የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት አይደለም።
የመንጽሔ ትምህርት የተመሠረተው በምን ላይ ነው?
ኒው ካቶሊክ ኢንሳይክሎፔድያ (1967፣ ጥራዝ 11፣ ገጽ 1034) ካቶሊካውያን ጸሐፊዎች እንደ 2 መቃብያን 12:39–45፣ ማቴዎስ 12:32ና 1 ቆሮንቶስ 3:10–15 ስላሉት ጥቅሶች የጻፏቸውን ከመረመረ በኋላ እንዲህ ብሏል:- “ይህንን ሁሉ ከመረመርን በኋላ የምንገነዘበው የካቶሊክ የመንጽሔ መሠረተ ትምህርት በቅዱሳን ጽሑፎች ላይ ሳይሆን በወግ ላይ የተመሠረተ መሆኑን ነው።”
-