-
በትላልቅ ስብሰባዎች ላይ የምንገኘው ለምንድን ነው?በዛሬው ጊዜ የይሖዋን ፈቃድ የሚያደርጉት እነማን ናቸው?
-
-
ትምህርት 11
በትላልቅ ስብሰባዎች ላይ የምንገኘው ለምንድን ነው?
ሜክሲኮ
ጀርመን
ቦትስዋና
ኒካራጉዋ
ጣሊያን
በእነዚህ ሰዎች ፊት ላይ የደስታ ስሜት የሚነበበው ለምንድን ነው? የይሖዋ ምሥክሮች በሚያደርጉት አንድ ትልቅ ስብሰባ ላይ ስለተገኙ ነው። በዓመት ውስጥ ሦስት ጊዜ እንዲሰበሰቡ ታዘው እንደነበሩት እንደ ጥንቶቹ የአምላክ ሕዝቦች ሁሉ እኛም ብዙ ሆነን የምንሰበሰብ ሲሆን ልክ እንደ እነሱ እኛም ይህን ጊዜ በጉጉት እንጠብቃለን። (ዘዳግም 16:16) በየዓመቱ ሦስት ትላልቅ ስብሰባዎች የምናደርግ ሲሆን ሁለት ጊዜ የአንድ ቀን የወረዳ ስብሰባ እንዲሁም አንድ ጊዜ የሦስት ቀን የክልል ስብሰባ እናደርጋለን። ከእነዚህ ስብሰባዎች ምን ጥቅም እናገኛለን?
ክርስቲያናዊ ወንድማማችነታችንን ያጠናክሩልናል። እስራኤላውያን ይሖዋን “በታላቅ ጉባኤ መካከል” ማወደስ ያስደስታቸው እንደነበረ ሁሉ እኛም በእነዚህ ልዩ ወቅቶች አንድ ላይ ሆነን እሱን ማምለክ ያስደስተናል። (መዝሙር 26:12፤ 111:1) እነዚህ ስብሰባዎች ከሌሎች ጉባኤዎች አልፎ ተርፎም ከሌሎች አገራት ከመጡ የይሖዋ ምሥክሮች ጋር ለመገናኘትና አብረን ጊዜ ለማሳለፍ አጋጣሚ ይፈጥሩልናል። እኩለ ቀን ሲሆን ከስብሰባው ቦታ ሳንወጣ ምሳችንን መመገባችን እነዚህ መንፈሳዊ ዝግጅቶች አስደሳች እንዲሆኑ አስተዋጽኦ ያበረክታል። (የሐዋርያት ሥራ 2:42) ከዚህም ሌላ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የይሖዋ ሕዝቦችን ያቀፈውን “የወንድማማች ማኅበር” አንድ የሚያደርገውን ፍቅር ለመቅመስ የሚያስችል አጋጣሚ እናገኛለን።—1 ጴጥሮስ 2:17
መንፈሳዊ እድገት ለማድረግ ያስችሉናል። እስራኤላውያን በስብሰባዎች ላይ ቅዱሳን መጻሕፍት ይብራሩላቸው ስለነበር ‘ቃሉን መረዳት’ ችለዋል። (ነህምያ 8:8, 12) እኛም ብንሆን በትላልቅ ስብሰባዎች ላይ ከመጽሐፍ ቅዱስ የምናገኛቸውን ማሳሰቢያዎች ከፍ አድርገን እንመለከታቸዋለን። እያንዳንዱ ፕሮግራም ከቅዱሳን መጻሕፍት በተወሰደ ጭብጥ ላይ የተመሠረተ ነው። በስብሰባው ላይ የሚቀርቡት ግሩም ንግግሮች፣ ሲምፖዚየሞችና ሠርቶ ማሳያዎች የአምላክን ፈቃድ በሕይወታችን ውስጥ እንዴት መፈጸም እንደምንችል ያስተምሩናል። ባለንበት አስቸጋሪ ጊዜ፣ ክርስቲያኖች በመሆናቸው የሚያጋጥሟቸውን ተፈታታኝ ሁኔታዎች በጽናት የተወጡ የእምነት ባልንጀሮቻችንን ተሞክሮ ስንሰማ እንበረታታለን። በክልል ስብሰባዎች ላይ የሚኖሩት ድራማዎች የመጽሐፍ ቅዱስን ታሪኮች ሕያው አድርገው በማቅረብ ከዘገባው ትምህርት እንድናገኝ ይረዱናል። ራሳቸውን ለአምላክ መወሰናቸውን ለሕዝብ ለማሳየት ለሚፈልጉ በሙሉ በሁሉም ትላልቅ ስብሰባዎች ላይ የጥምቀት ሥነ ሥርዓት ይዘጋጃል።
ትላልቅ ስብሰባዎች አስደሳች ወቅት የሆኑት ለምንድን ነው?
በትላልቅ ስብሰባዎች ላይ በመገኘት ምን ጥቅም ማግኘት ትችላለህ?
-
-
የመንግሥቱን ምሥራች የምንሰብከው እንዴት ነው?በዛሬው ጊዜ የይሖዋን ፈቃድ የሚያደርጉት እነማን ናቸው?
-
-
ትምህርት 12
የመንግሥቱን ምሥራች የምንሰብከው እንዴት ነው?
ስፔን
ቤላሩስ
ሆንግ ኮንግ
ፔሩ
ኢየሱስ ከመሞቱ ጥቂት ቀደም ብሎ “ይህ የመንግሥቱ ምሥራች ለብሔራት ሁሉ ምሥክር እንዲሆን በመላው ምድር ይሰበካል፤ ከዚያም መጨረሻው ይመጣል” በማለት ተናግሮ ነበር። (ማቴዎስ 24:14) ይሁን እንጂ ይህ ዓለም አቀፍ የስብከት ሥራ የሚከናወነው እንዴት ነው? ኢየሱስ ምድር ሳለ የተወውን ምሳሌ በመከተል ነው።—ሉቃስ 8:1
ሰዎችን ቤታቸው ሄደን ለማነጋገር ጥረት እናደርጋለን። ኢየሱስ ምሥራቹን ከቤት ወደ ቤት እየሄዱ እንዲሰብኩ ደቀ መዛሙርቱን አሠልጥኗቸው ነበር። (ማቴዎስ 10:11-13፤ የሐዋርያት ሥራ 5:42፤ 20:20) በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩት እነዚህ ወንጌላውያን የሚሰብኩበት ክልል ተመድቦላቸው ነበር። (ማቴዎስ 10:5, 6፤ 2 ቆሮንቶስ 10:13) ዛሬም በተመሳሳይ የስብከት ሥራችን በሚገባ የተደራጀ ሲሆን እያንዳንዱ ጉባኤም ሊሸፍነው የሚገባ የራሱ ክልል ተመድቦለታል። ይህም “ለሰዎች እንድንሰብክና በተሟላ ሁኔታ እንድንመሠክር” የሚያዝዘውን የኢየሱስን መመሪያ ለመፈጸም ያስችለናል።—የሐዋርያት ሥራ 10:42
ሰዎች በሚገኙበት ቦታ ሁሉ ለመስበክ ጥረት እናደርጋለን። ኢየሱስ ብዙ ሕዝብ በሚገኝባቸው ቦታዎችም ለምሳሌ በባሕር ዳርቻዎችና በውኃ ጉድጓዶች አቅራቢያ በመስበክ አርዓያ ትቶልናል። (ማርቆስ 4:1፤ ዮሐንስ 4:5-15) እኛም ሰዎችን ማግኘት በምንችልበት ቦታ ሁሉ ይኸውም በመንገድ ላይ፣ በንግድ አካባቢዎችና በመናፈሻ ቦታዎች አሊያም ደግሞ በስልክ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ እናወያያቸዋለን። በተጨማሪም አመቺ አጋጣሚ በምናገኝበት ጊዜ ለጎረቤቶቻችን፣ ለሥራ ባልደረቦቻችን፣ አብረውን ለሚማሩ ልጆችና ለዘመዶቻችን ሁሉ እንመሠክራለን። ምሥራቹን ለመስበክ የምናደርገው ይህ ሁሉ ጥረት በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች “የማዳኑን ምሥራች” እንዲሰሙ አስችሏል።—መዝሙር 96:2
ስለ አምላክ መንግሥትና ወደፊት ስለሚያመጣቸው ነገሮች የሚገልጸውን ምሥራች ልትነግረው የምትፈልገው ሰው አለ? ይህን አስደሳች ተስፋ ሚስጥር አድርገህ አትያዘው። ዛሬ ነገ ሳትል ይህን ምሥራች ለሌሎች ተናገር!
መሰበክ ያለበት “ምሥራች” የትኛው ነው?
የይሖዋ ምሥክሮች፣ ኢየሱስ ምሥራቹን የሰበከበትን መንገድ የሚኮርጁት እንዴት ነው?
-
-
አቅኚነት ምንድን ነው?በዛሬው ጊዜ የይሖዋን ፈቃድ የሚያደርጉት እነማን ናቸው?
-
-
ትምህርት 13
አቅኚነት ምንድን ነው?
ካናዳ
ከቤት ወደ ቤት
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
የግል ጥናት
“አቅኚ” የሚለው ቃል ብዙውን ጊዜ የሚሠራበት ወደ አዲስ አካባቢ የሚሄዱ እንዲሁም ፈር ቀዳጅ በመሆን ለሌሎች መንገድ የሚጠርጉ ሰዎችን ለማመልከት ነው። ኢየሱስ፣ ሕይወት የሚያስገኝ አገልግሎት ለማከናወንና ወደ መዳን የሚመራውን በር ለመክፈት ወደ ምድር በመምጣቱ አቅኚ ሊባል ይችላል። (ማቴዎስ 20:28) በዛሬው ጊዜም ተከታዮቹ፣ ሰዎችን ‘ደቀ መዛሙርት በማድረጉ’ ሥራ የሚችሉትን ያህል ጊዜ በማሳለፍ የእሱን ምሳሌ እየተከተሉ ነው። (ማቴዎስ 28:19, 20) አንዳንድ የኢየሱስ ተከታዮች ደግሞ የአቅኚነት አገልግሎት ብለን በምንጠራው መስክ ይካፈላሉ።
አቅኚዎች የሙሉ ጊዜ ወንጌላውያን ናቸው። ሁሉም የይሖዋ ምሥክሮች የምሥራቹ አስፋፊዎች ወይም ሰባኪዎች ናቸው። አንዳንዶች ግን ፕሮግራማቸውን አስተካክለው በየወሩ 70 ሰዓት በስብከቱ ሥራ በማሳለፍ የዘወትር አቅኚዎች ሆነው ያገለግላሉ። ብዙዎች ይህን ለማድረግ ሲሉ በሰብዓዊ ሥራቸው ላይ የሚያሳልፉትን ጊዜ ይቀንሳሉ። ሌሎች ደግሞ የመንግሥቱ ሰባኪዎች ይበልጥ በሚያስፈልጉባቸው አካባቢዎች ልዩ አቅኚዎች ሆነው እንዲያገለግሉ የሚመደቡ ሲሆን እነዚህ ክርስቲያኖች በስብከቱ ሥራ በየወሩ 130 ሰዓት ወይም ከዚያ በላይ ያሳልፋሉ። አቅኚዎች ይሖዋ የሚያስፈልጓቸውን መሠረታዊ ነገሮች እንደሚያሟላላቸው ቅንጣት ታክል ስለማይጠራጠሩ ባላቸው በመርካት ቀለል ያለ ሕይወት ይመራሉ። (ማቴዎስ 6:31-33፤ 1 ጢሞቴዎስ 6:6-8) ልዩ ወይም የዘወትር አቅኚ መሆን የማይችሉ ክርስቲያኖች ደግሞ በሚመቻቸው ወር ረዳት አቅኚዎች ሆነው የሚያገለግሉ ሲሆን በዚያ ወቅት በስብከቱ ሥራ በወር ውስጥ 30 ወይም 50 ሰዓት ያሳልፋሉ።
አቅኚዎች በዚህ መስክ እንዲሰማሩ የሚያነሳሳቸው ለይሖዋና ለሰዎች ያላቸው ፍቅር ነው። ኢየሱስ በዘመኑ የነበሩት ሰዎች ያሉበትን መንፈሳዊ ሁኔታ ሲመለከት አዝኖላቸው ነበር፤ እኛም በዛሬው ጊዜ ብዙ ሰዎች ያሉበት መንፈሳዊ ሁኔታ አሳዛኝ እንደሆነ እናስተውላለን። (ማርቆስ 6:34) በሌላ በኩል ደግሞ ሰዎች ለወደፊቱ ጊዜ አስተማማኝ ተስፋ እንዲኖራቸው የሚያደርግ እውቀት እንዳለን እንገነዘባለን፤ ይህ እውቀት በአሁኑ ጊዜም እንኳ ሊጠቅማቸው ይችላል። አቅኚዎች ለሰዎች ያላቸው ፍቅር ሌሎችን በመንፈሳዊ ለመርዳት ጊዜያቸውንና ጉልበታቸውን ሳይቆጥቡ በስብከቱ ሥራ እንዲያሳልፉ ያነሳሳቸዋል። (ማቴዎስ 22:39፤ 1 ተሰሎንቄ 2:8) እንዲህ በማድረጋቸው እምነታቸው የሚጠናከርና ወደ አምላክ ይበልጥ የሚቀርቡ ከመሆኑም ሌላ ይህ ነው የማይባል ደስታ ያገኛሉ።—የሐዋርያት ሥራ 20:35
አቅኚነት ምንድን ነው?
አንዳንዶች በአቅኚነት እንዲካፈሉ የሚያነሳሳቸው ምንድን ነው?
-