-
የወረዳ የበላይ ተመልካቾች የሚጠቅሙን እንዴት ነው?በዛሬው ጊዜ የይሖዋን ፈቃድ የሚያደርጉት እነማን ናቸው?
-
-
ትምህርት 17
የወረዳ የበላይ ተመልካቾች የሚጠቅሙን እንዴት ነው?
ማላዊ
የስምሪት ስብሰባ
የመስክ አገልግሎት
የሽማግሌዎች ስብሰባ
የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ስለ በርናባስና ስለ ሐዋርያው ጳውሎስ በተደጋጋሚ ይጠቅሳሉ። እነዚህ ወንድሞች ተጓዥ የበላይ ተመልካቾች በመሆን የጥንቶቹን ጉባኤዎች ይጎበኙ ነበር። ይህን ያደርጉ የነበረው ለምንድን ነው? ስለ መንፈሳዊ ወንድሞቻቸው ደህንነት ከልባቸው ያስቡ ስለነበር ነው። ጳውሎስ “ወንድሞች በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ” ሲል ‘ተመልሶ ሊጠይቃቸው’ እንደሚፈልግ ተናግሯል። እነሱን ሄዶ ለማበረታታት በመቶዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮች ለመጓዝ ፈቃደኛ ነበር። (የሐዋርያት ሥራ 15:36) ዛሬም ያሉት ተጓዥ የበላይ ተመልካቾች ተመሳሳይ ስሜት አላቸው።
ማበረታቻ ይሰጡናል። እያንዳንዱ የወረዳ የበላይ ተመልካች ወደ 20 ገደማ የሚሆኑ ጉባኤዎችን በዓመት ሁለት ጊዜ የሚጎበኝ ሲሆን በእያንዳንዱ ጉብኝት ወቅት ከጉባኤው ጋር ለአንድ ሳምንት ይቆያል። ከእነዚህ ወንድሞችና ያገቡ ከሆኑ ደግሞ ከሚስቶቻቸው ተሞክሮም ብዙ ጥቅም ልናገኝ እንችላለን። የወረዳ የበላይ ተመልካቾችም ሆኑ ሚስቶቻቸው፣ ወጣት ሽማግሌ ሳይሉ ከሁላችንም ጋር ለመተዋወቅ ጥረት ያደርጋሉ፤ በተጨማሪም አብረውን በመስክ አገልግሎት ለመሰማራትና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችንን ለማስጠናት ይፈልጋሉ። እነዚህ የበላይ ተመልካቾች ከሽማግሌዎች ጋር ሆነው እረኝነት ያደርጋሉ፤ እንዲሁም በጉባኤና በትላልቅ ስብሰባዎች ላይ የሚያበረታቱና እምነትን የሚያጠናክሩ ንግግሮች ያቀርባሉ።—የሐዋርያት ሥራ 15:35
ለሁሉም አሳቢነት ያሳያሉ። የወረዳ የበላይ ተመልካቾች የጉባኤዎች መንፈሳዊ ሁኔታ ከልብ ያሳስባቸዋል። ስለ ጉባኤው እንቅስቃሴ ለመወያየት ከሽማግሌዎችና ከጉባኤ አገልጋዮች ጋር ስብሰባ የሚያደርጉ ሲሆን ለእነዚህ ወንድሞች ኃላፊነቶቻቸውን ከሚወጡበት መንገድ ጋር በተያያዘ ጠቃሚ ምክር ይለግሷቸዋል። አቅኚዎች በአገልግሎታቸው ውጤታማ መሆን እንዲችሉ ይረዷቸዋል፤ እንዲሁም ከአዳዲሶች ጋር መጨዋወትና ስላደረጉት መንፈሳዊ እድገት መስማት በጣም ያስደስታቸዋል። ራሳቸውን በፈቃደኝነት የሚያቀርቡት እነዚህ ወንድሞች በሙሉ ‘ለእኛ ጥቅም አብረውን የሚሠሩ ባልደረቦቻችን’ ናቸው። (2 ቆሮንቶስ 8:23) በመሆኑም እምነታቸውንና ለአምላክ ያደሩ በመሆን ረገድ የሚተዉትን ምሳሌ መከተል አለብን።—ዕብራውያን 13:7
የወረዳ የበላይ ተመልካቾች ጉባኤዎችን የሚጎበኙበት ዓላማ ምንድን ነው?
ከጉብኝታቸው ጥቅም ልታገኝ የምትችለው እንዴት ነው?
-
-
አስቸጋሪ ሁኔታ ያጋጠማቸውን ወንድሞቻችንን የምንረዳው እንዴት ነው?በዛሬው ጊዜ የይሖዋን ፈቃድ የሚያደርጉት እነማን ናቸው?
-
-
ትምህርት 18
አስቸጋሪ ሁኔታ ያጋጠማቸውን ወንድሞቻችንን የምንረዳው እንዴት ነው?
ዶሚኒካን ሪፑብሊክ
ጃፓን
ሄይቲ
ድንገተኛ አደጋ በሚደርስበት ጊዜ የይሖዋ ምሥክሮች በአደጋው የተጎዱ ወንድሞቻቸውን ለመርዳት ወዲያውኑ ዝግጅት ያደርጋሉ። እንዲህ ያለው ጥረት በመካከላቸው ያለው ፍቅር ከልብ የመነጨ መሆኑን ያሳያል። (ዮሐንስ 13:34, 35፤ 1 ዮሐንስ 3:17, 18) ታዲያ ወንድሞቻችንን በየትኞቹ መንገዶች መርዳት እንችላለን?
ገንዘብ እናዋጣለን። በይሁዳ ታላቅ ረሃብ በተከሰተ ጊዜ በአንጾኪያ የነበሩ የጥንት ክርስቲያኖች ለመንፈሳዊ ወንድሞቻቸው የገንዘብ እርዳታ ልከው ነበር። (የሐዋርያት ሥራ 11:27-30) በተመሳሳይም በአንድ የዓለም ክፍል የሚኖሩ ወንድሞቻችን ከባድ ችግር እንዳጋጠማቸው ስናውቅ የሚያስፈልጓቸውን ቁሳዊ ነገሮች ለማሟላት እንዲቻል በጉባኤያችን በኩል የገንዘብ መዋጮ እንልካለን።—2 ቆሮንቶስ 8:13-15
በተግባር የተደገፈ እርዳታ እንሰጣለን። ድንገተኛ አደጋ በደረሰባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ሽማግሌዎች እያንዳንዱ የጉባኤ አባል የት እንዳለና ደህንነቱን ያጣራሉ። የአደጋ ጊዜ እርዳታ ኮሚቴ ተጎጂዎቹ ምግብ፣ ንጹሕ ውኃ፣ ልብስ፣ መጠለያና የሕክምና አገልገሎት ማግኘት የሚችሉበትን ዝግጅት ያስተባብራል። በዚህ ጊዜ ተፈላጊ የሆኑ ሙያዎች ያሏቸው በርካታ የይሖዋ ምሥክሮች ወጪያቸውን ችለው በእርዳታ አቅርቦት ሥራ ለመካፈል ወይም የተጎዱ ቤቶችንና የስብሰባ አዳራሾችን ለመጠገን ራሳቸውን በፈቃደኝነት ያቀርባሉ። አንድነት ስላለንና አብረን በመሥራት ረገድ ልምድ ስላካበትን እንደዚህ ባሉት ጊዜያት የሚያስፈልጉትን የእርዳታ ቁሳቁሶችና ሠራተኞች በፍጥነት ማሰባሰብ እንችላለን። በዋነኝነት የእርዳታ እጃችንን የምንዘረጋው “በእምነት ለሚዛመዱን ሰዎች” ቢሆንም በሚቻለን ጊዜ ሁሉ እገሌ ከገሌ ሳንል የማንኛውም ሃይማኖት አባላት የሆኑ ሰዎችንም እንረዳለን።—ገላትያ 6:10
መንፈሳዊና ስሜታዊ ድጋፍ እንሰጣለን። አደጋ የደረሰባቸው ሰዎች ከሌሎች ይበልጥ ማጽናኛ ያስፈልጋቸዋል። እንደነዚህ ባሉት ጊዜያት ብርታት የምናገኘው “የመጽናናት ሁሉ አምላክ” ከሆነው ከይሖዋ ነው። (2 ቆሮንቶስ 1:3, 4) በጭንቀት ላይ ለሚገኙ ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን ተስፋዎች በደስታ በመናገር በቅርቡ የአምላክ መንግሥት የመከራና የሥቃይ ምክንያት የሚሆኑ ነገሮችን በሙሉ እንደሚያስወግድ እናረጋግጥላቸዋለን።—ራእይ 21:4
የይሖዋ ምሥክሮች አደጋ በሚደርስበት ጊዜ አፋጣኝ እርዳታ ለመስጠት ዝግጁ የሆኑት ለምንድን ነው?
ከአደጋ ለተረፉ ሰዎች ምን ዓይነት መንፈሳዊ ማጽናኛ መስጠት እንችላለን?
-
-
ታማኝና ልባም ባሪያ ማን ነው?በዛሬው ጊዜ የይሖዋን ፈቃድ የሚያደርጉት እነማን ናቸው?
-
-
ትምህርት 19
ታማኝና ልባም ባሪያ ማን ነው?
ሁላችንም ከሚቀርብልን መንፈሳዊ ምግብ ጥቅም እናገኛለን
ኢየሱስ ከመሞቱ ጥቂት ቀደም ብሎ አራት ደቀ መዛሙርቱ ይኸውም ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ፣ ዮሐንስና እንድርያስ ወደ እሱ ለብቻቸው መጥተው አነጋግረውት ነበር። ኢየሱስ በመጨረሻው ዘመን የእሱን መገኘት የሚያሳውቀውን ምልክት በሚናገርበት ወቅት እንደሚከተለው በማለት አንድ ወሳኝ ጥያቄ አነሳ፦ “በተገቢው ጊዜ ምግባቸውን እንዲሰጣቸው ጌታው በቤተሰቦቹ ላይ የሾመው ታማኝና ልባም ባሪያ በእርግጥ ማን ነው?” (ማቴዎስ 24:3, 45፤ ማርቆስ 13:3, 4) ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ይህን ጥያቄ ሲያቀርብ ‘ጌታቸው’ እንደመሆኑ መጠን በመጨረሻው ዘመን ለተከታዮቹ ሳያሰልሱ መንፈሳዊ ምግብ የሚያቀርቡ ሰዎችን እንደሚሾም ማረጋገጡ ነበር። ታዲያ እነዚህ ሰዎች እነማን ናቸው?
ጥቂት ቁጥር ያላቸው በመንፈስ የተቀቡ የኢየሱስ ተከታዮችን ያቀፈ ቡድን ነው። ‘ባሪያው’ የይሖዋ ምሥክሮችን የበላይ አካል ያመለክታል። አብረውት ይሖዋን ለሚያመልኩት የእምነት ባልንጀሮቹ ወቅታዊ የሆነ መንፈሳዊ ምግብ ያቀርባል። የሚያስፈልገንን “ምግብ በተገቢው ጊዜ” የምናገኘው ከታማኙ ባሪያ ነው።—ሉቃስ 12:42
የአምላክን ቤተሰብ ያስተዳድራል። (1 ጢሞቴዎስ 3:15) ኢየሱስ፣ የይሖዋ ድርጅት ምድራዊ ክፍል የሚያከናውነውን ሥራ የማስተዳደሩን ከባድ ኃላፊነት የሰጠው ለባሪያው ነው፤ ይህም ቁሳዊ ንብረቶቹን መቆጣጠርን፣ የስብከቱን ሥራ መምራትን እንዲሁም በጉባኤዎች በኩል እኛን ማስተማርን ይጨምራል። “ታማኝና ልባም ባሪያ” በአገልግሎታችን ላይ በምንጠቀምባቸው ጽሑፎች እንዲሁም በጉባኤና በትላልቅ ስብሰባዎቻችን ላይ በሚቀርቡት ትምህርቶች አማካኝነት የሚያስፈልገንን መንፈሳዊ ምግብ በተገቢው ጊዜ እያቀረበልን ነው።
ባሪያው ለመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችና ምሥራቹን እንዲሰብክ ለተሰጠው ኃላፊነት ታማኝ ሲሆን በምድር ላይ የሚገኘውን የክርስቶስ ንብረት በጥበብ በማስተዳደርም ልባም መሆኑን አሳይቷል። (የሐዋርያት ሥራ 10:42) ይሖዋ የሕዝቦቹ ቁጥር እንዲያድግ በማድረግ እንዲሁም ባሪያው የተትረፈረፈ መንፈሳዊ ዝግጅት እንዲያቀርብ በመርዳት ይህ ባሪያ የሚያከናውነውን ሥራ እየባረከው ነው።—ኢሳይያስ 60:22፤ 65:13
ኢየሱስ፣ ደቀ መዛሙርቱን በመንፈሳዊ እንዲመግብ የሾመው ማንን ነው?
ባሪያው፣ ታማኝና ልባም የሆነው በምን መንገዶች ነው?
-