መዝሙር 73
አጥብቃችሁ ከልብ ተዋደዱ
በወረቀት የሚታተመው
1. የፍቅር ምንጩ መነሻው፣
ከልብ ነው መጀመሪያው፤
ይህ ነው ቁልፉ ለመረዳት፣
የሌላውን ስሜት።
አሳቢነት ለማሳየት፣
አጋጣሚ ’ንፈልጋለን፤
እንዳምላክ ደጎች በመሆን፣
በማሳየት ፍቅርን።
ይታይ ፍቅር በሥራም፣
ለጋሶች በመሆን ምንጊዜም፣
ጥሩ ሰዎች በመሆን፣
አጋጣሚው ሳያልፈን።
ሁሌ እናክብር ሰዎችን፤
ደግና አሳቢ ’ንሁን።
አናንሳ ድክመታቸውን።
እንዳይጠፋ ’ንጠብቀው፣
ኅብረታችን ውድ ነው።
2. ፍቅራችን ከሆነ የ’ውነት፣
አንቸኩልም ለመከፋት።
ውድ ወንድሞችን ለማመን፣
በቂ ምክንያት አለን።
ይደግ ወዳጅነታችን፤
’ናድንቃቸው ከልባችን።
አብሮ መሰብሰብ ደስ ይላል፤
መንፈስን ያድሳል።
ሁሉም ሰው ይሳሳታል፤
ግድ የለሽ ቃል ሰውን ይጎዳል።
እናም እንራራላቸው፤
አምላክ ለሚወዳቸው።
’ናጠናክረው ፍቅራችንን፤
ጥሩ ወዳጅ እንድንሆን።
ፍቅር መለያችን ይሁን።
አምላክን ’ናስከብረው፤
በፍቅሩም እንምሰለው።
(በተጨማሪም 1 ጴጥ. 2:17፤ 3:8፤ 4:8ን እና 1 ዮሐ. 3:11ን ተመልከት።)