መዝሙር 75
ለደስታችን ምክንያት የሆኑ ነገሮች
በወረቀት የሚታተመው
1. ለደስታ አለን ብዙ ምክንያት፣
ዋጋው እንደሚጨምር ሀብት።
በብሔራት ውስጥ ያሉ ምርጦች፣
ወደኛ ጎርፈዋል ሕዝቦች።
ደስታችን መሠረት ያለው ነው፤
ከቃሉ የመነጨ ነው።
ለዚህ ነው ሁሌም ’ምናነበው፤
በሰማነው የምናምነው።
ደስታችን ምንጊዜም አይጠፋም፤
በልባችን እንዳለ ፍም።
ችግር፣ መከራ ያገኘናል፤
ይሖዋ ግን ያጸናናል።
(አዝማች)
አምላካችን ነው፣ ደስታችን፤
ሥራዎቹም እርካታችን።
ሐሳቦቹ ጥልቅ፣ ሥራዎቹም ድንቅ፣
ነው ጥሩና ኃይሉ ታላቅ!
2. ድንቅ ነው ማየት ሥራዎቹን፣
ሰማይ፣ ባሕርና ምድርን።
ስናይ የፍጥረት ሥራዎቹን፣
የ’ጁን ጥበብ ’ናደንቃለን።
በደስታ እንመሠክራለን፤
ያምላክ መንግሥት መቋቋሙን።
የሚያመጣውንም በረከት፣
ካጽናፍ አጽናፍ ’ናበስራለን።
ጨለማው በብርሃን ይተካል፤
የዘላለም ደስታ ቀርቧል።
አዲስ ምድርና ሰማያት፣
ያስገኛል ዘላለም ሐሴት።
(አዝማች)
አምላካችን ነው፣ ደስታችን፤
ሥራዎቹም እርካታችን።
ሐሳቦቹ ጥልቅ፣ ሥራዎቹም ድንቅ፣
ነው ጥሩና ኃይሉ ታላቅ!