የአምላክ ቃል ያለው ኃይል በሕይወትህ ውስጥ እንዲሠራ እያደረግክ ነው?
መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ ማንበባችን ‘በእምነት እንድንጸናና ሥር እንድንሰድ’ ይረዳናል። (ቆላ. 2:6, 7) ሆኖም የይሖዋ ቃል ያለው ኃይል በሕይወታችን ውስጥ እንዲሠራ በቃሉ ላይ ማሰላሰልና በውስጡ ያሉትን መሠረታዊ ሥርዓቶች ተግባራዊ ማድረግ ይኖርብናል። (ዕብ. 4:12፤ ያዕ. 1:22-25) ኢያሱ 1:8 መጽሐፍ ቅዱስን በምናነብበት ወቅት ልንከተላቸው የሚገቡ ሦስት ውጤታማ ዘዴዎችን ይዟል፦ (1) የአምላክን ቃል “ቀንም ሆነ ሌሊት” ማንበብ። (2) “በለሆሳስ” ማለትም ለማሰላሰል እንዲሁም መቼቱንና በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ በዓይነ ሕሊናችን ለመሳል በሚያስችል ፍጥነት ማንበብ። (3) “በውስጡ የተጻፈውን” ነገር በቁም ነገር መፈጸም። እነዚህን ነጥቦች ተግባራዊ ማድረጋችን ‘መንገዳችን እንዲቃና’ እንዲሁም ‘ማንኛውንም ነገር በጥበብ እንድናከናውን’ ያስችለናል።