የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • bh ገጽ 3-7
  • የአምላክ ዓላማ ይህ ነበር?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአምላክ ዓላማ ይህ ነበር?
  • ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
  • ንዑስ ርዕሶች
  • መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ የሚከተሉትን ለውጦች በምድር ላይ እንደሚያመጣ ይናገራል።
  • መጽሐፍ ቅዱስ ከሚያስተምረው ትምህርት ተጠቀም
ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
bh ገጽ 3-7

የአምላክ ዓላማ ይህ ነበር?

የትኛውንም ጋዜጣ ብታነብ፣ ቴሌቪዥን ብትመለከት ወይም ሬዲዮ ብትሰማ የምታነበውም ሆነ የምታየው አሊያም የምትሰማው አብዛኛው ዘገባ ከወንጀል፣ ከጦርነትና ከሽብርተኝነት ጋር የተያያዘ ነው! አንተ ራስህ ያሉብህንም ችግሮች እስቲ አስብ። ምናልባት በሕመም እየተሠቃየህ ይሆናል፤ ወይም ደግሞ በጣም የምትወደውን ሰው በሞት በማጣትህ ከባድ ሐዘን ላይ ወድቀህ ሊሆን ይችላል። በመሆኑም ‘በመከራ ተዘፍቄአለሁ’ እንዳለው እንደ ጻድቁ ሰው እንደ ኢዮብ ዓይነት ስሜት ይሰማህ ይሆናል።—ኢዮብ 10:15

እስቲ እንዲህ እያልክ ራስህን ጠይቅ:-

  • አምላክ ለእኔም ሆነ ለቀረው የሰው ዘር ያለው ዓላማ ይህ ነው?

  • ችግሮቼን ለመቋቋም የሚያስችል እርዳታ ላገኝ የምችለው ከየት ነው?

  • በምድር ላይ ሰላም የሚሰፍንበት ጊዜ ይመጣ ይሆን?

መጽሐፍ ቅዱስ ለእነዚህ ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ ይሰጣል።

መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ የሚከተሉትን ለውጦች በምድር ላይ እንደሚያመጣ ይናገራል።

“እንባን ሁሉ ከዐይናቸው ያብሳል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሞት ወይም ሐዘን ወይም ልቅሶ ወይም ሥቃይ አይኖርም።”—ራእይ 21:4

“አንካሳ እንደ ሚዳቋ ይዘላል።”—ኢሳይያስ 35:6

“የዕውር ዐይኖች ይገለጣሉ።”—ኢሳይያስ 35:5

“መቃብር ውስጥ ያሉ ሁሉ . . . ይወጣሉ።”—ዮሐንስ 5:28, 29

“‘ታምሜአለሁ’ የሚል አይኖርም።”—ኢሳይያስ 33:24

‘በምድሪቱ ላይ እህል ይትረፈረፋል።’—መዝሙር 72:16

ምድር አምላክ መጀመሪያ ወዳሰበው ሁኔታ ስትመለስ፦ ሽማግሌው ወጣት ሲሆን፣ የታመመ ሰው ሲድን፣ ማየት የተሳነው ሰው ዓይኑ ሲከፈት፣ የሞተ ሰው ሲነሳ፣ በምድር ላይ እህል ሲትረፈረፍ

መጽሐፍ ቅዱስ ከሚያስተምረው ትምህርት ተጠቀም

ቀደም ባሉት ገጾች ላይ የተገለጸው ሐሳብ እንዲሁ ምኞት ካልሆነ በስተቀር ሊፈጸም የማይችል ነገር ነው ብለህ ለመደምደም አትቸኩል። አምላክ እነዚህን ነገሮች እንደሚፈጽም ቃል የገባ ሲሆን መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ አምላክ እነዚህን ተስፋዎች እንዴት እንደሚፈጽም ይገልጽልናል።

ሁለት ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ ተጠቅመው መጽሐፍ ቅዱስን ሲያጠኑ

ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ ከዚህም ሌላ የሚያስገኘው ጥቅም አለ። በአሁኑ ጊዜም እንኳ አስደሳች የሆነ ሕይወት መኖር የምትችልበትን መንገድ ያስተምርሃል። እስቲ የሚያስጨንቁህንና የሚያሳስቡህን ነገሮች ለጥቂት ደቂቃዎች አስብ። እነዚህ ችግሮች ከገንዘብ፣ ከቤተሰብ፣ ከጤና ወይም በጣም የምትወደውን ሰው በሞት ከማጣት ጋር የተያያዙ ሊሆኑ ይችላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ በአሁኑ ጊዜ እነዚህን ችግሮች መወጣት እንድትችል የሚረዳህ ከመሆኑም በላይ እንደሚከተሉት ላሉት ጥያቄዎች መልስ በመስጠት እፎይታ ሊያስገኝልህ ይችላል:-

  • መከራና ሥቃይ የሚደርስብን ለምንድን ነው?

  • ኑሮ የሚያስከትልብንን ጭንቀት መቋቋም የምንችለው እንዴት ነው?

  • የቤተሰባችንን ሕይወት አስደሳች ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?

  • ስንሞት ምን እንሆናለን?

  • በሞት ያጣናቸውን ሰዎች ዳግመኛ እናገኛቸው ይሆን?

  • አምላክ የወደፊቱን ጊዜ አስመልክቶ ቃል የገባቸውን ነገሮች እንደሚፈጽም እንዴት እርግጠኞች ልንሆን እንችላለን?

ይህን መጽሐፍ እያነበብክ መሆኑ በራሱ፣ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረውን ትምህርት ማወቅ እንደምትፈልግ የሚያሳይ ነው። በዚህ ረገድ ይህ መጽሐፍ በእጅጉ ይረዳሃል። አንቀጾቹ በገጹ ግርጌ ላይ ጥያቄዎች እንዳሏቸው ልብ በል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን በዚህ መንገድ በጥያቄና መልስ ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር በማጥናታቸው በጣም ተጠቅመዋል። አንተም እንደምትጠቀም ተስፋ እናደርጋለን። ትክክለኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት መማር የምትችልበትን ይህን አስደሳች አጋጣሚ ለመጠቀም በምታደርገው ጥረት የአምላክ በረከት እንዳይለይህ እንመኛለን!

ከመጽሐፍ ቅዱስህ ጋር ተዋወቅ

መጽሐፍ ቅዱስ 66 መጻሕፍትንና መልእክቶችን ያቀፈ ነው። እነዚህ መጻሕፍትና መልእክቶች በቀላሉ ለማውጣት እንዲመች ሲባል በምዕራፎችና በቁጥሮች ተከፋፍለዋል። በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ጥቅሶች በሚጠቀሱበት ጊዜ ከመጽሐፉ ስም ቀጥሎ የሚገኘው የመጀመሪያው አኃዝ የመጽሐፉን ወይም የመልእክቱን ምዕራፍ የሚያመለክት ሲሆን ቀጥሎ ያለው አኃዝ ደግሞ ቁጥሩን የሚያመለክት ነው። ለምሳሌ ያህል “2 ጢሞቴዎስ 3:16” ከተጠቀሰ ሁለተኛ ጢሞቴዎስ ምዕራፍ 3 ቁጥር 16 ማለት ነው።

በዚህ ጽሑፍ ውስጥ የተጠቀሱትን ጥቅሶች እያወጣህ በማንበብ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ቶሎ መተዋወቅ ትችላለህ። ከዚህም በተጨማሪ በየዕለቱ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ የምትችልበት ፕሮግራም ለምን አታወጣም? በቀን ከሦስት እስከ አምስት የሚደርሱ ምዕራፎችን በማንበብ በአንድ ዓመት ውስጥ መላውን መጽሐፍ ቅዱስ አንብበህ መጨረስ ትችላለህ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ