መዝሙር 128
የዚህ ዓለም ትእይንት እየተለዋወጠ ነው
በወረቀት የሚታተመው
1. ይሖዋ ተስፋ ሊሰጠን፣
ከኃጢያት፣ ከሞት ሊያድነን፣
አንድ ልጁን ለኛ ላከው።
ስጦታው ወደር የለው።
(አዝማች)
ያለም ትእይንት
ይለዋወጣል፤
ይሖዋ ግን ሰማይ፣ ምድርን
ሊባርክ ተዘጋጅቷል።
2. ዓለም በጭንቅ ውስጥ ይገኛል።
ይህ ክፉ ሥርዓትም ወድቋል።
መንግሥቱ ነው የኛ ተስፋ፤
ተቋቁሟል በይፋ።
(አዝማች)
ያለም ትእይንት
ይለዋወጣል፤
ይሖዋ ግን ሰማይ፣ ምድርን
ሊባርክ ተዘጋጅቷል።
(በተጨማሪም መዝ. 115:15, 16ን፣ ሮም 5:15-17፤ 7:25ን እና ራእይ 12:5ን ተመልከት።)