የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “የፍቅራዊ ደግነት ሕግ” አንደበታችሁን እንዲቆጣጠረው ፍቀዱ
    መጠበቂያ ግንብ—2010 | ነሐሴ 15
    • 18, 19. ከእምነት ባልንጀሮቻችን ጋር ባለን ግንኙነት ረገድ የፍቅራዊ ደግነት ሕግ ከአንደበታችን ሊጠፋ የማይገባው ለምንድን ነው?

      18 ጽኑ ፍቅር ከይሖዋ አገልጋዮች ጋር ባለን ግንኙነት ሁሉ በግልጽ መታየት ይኖርበታል። በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ በምንሆንበት ጊዜም እንኳ የፍቅራዊ ደግነት ሕግ ከአንደበታችን ሊጠፋ አይገባም። ይሖዋ፣ የእስራኤል ልጆች ፍቅራዊ ደግነት “እንደ ማለዳ ጉም” በንኖ በጠፋበት ጊዜ አዝኖ ነበር። (ሆሴዕ 6:4, 6) እሱ የሚደሰተው ፍቅራዊ ደግነትን አዘውትረው በሚያሳዩ ሰዎች ነው። ይሖዋ ፍቅራዊ ደግነትን የሚከታተሉ ሰዎችን እንዴት እንደሚባርክ እንመልከት።

  • ሰዓት አክባሪ መሆን ያለብን ለምንድን ነው?
    መጠበቂያ ግንብ—2010 | ነሐሴ 15
    • ሰዓት አክባሪ መሆን ያለብን ለምንድን ነው?

      ቀጠሮ ማክበር ወይም በሰዓቱ መገኘት ሁልጊዜ ቀላል አይደለም። ልንወጣቸው ከሚገቡን እንቅፋቶች መካከል የምንሄድበት ቦታ ርቀት፣ የትራፊክ መጨናነቅና የተጣበበ ፕሮግራም ይገኙበታል። ያም ቢሆን በሰዓቱ መገኘት አስፈላጊ ነው። ለምሳሌ ያህል፣ በሥራ ቦታ ሰዓት የሚያከብር ሰው አብዛኛውን ጊዜ ታማኝና ትጉህ ሠራተኛ ተደርጎ ይቆጠራል። በሌላ በኩል ግን የሚያረፍድ ሰው ሌሎች የሚያከናውኑትን ሥራ እንዲሁም የሥራውን ጥራትና የሚሰጠውን አገልግሎት ሊያስተጓጉል ይችላል። አንድ ተማሪ አርፋጅ መሆኑ አንዳንድ ትምህርቶች እንዲያመልጡትና በትምህርቱ ተገቢውን እድገት እንዳያደርግ እንቅፋት እንዲሆንበት ያደርጋል። አንድ ሰው ለጥርስ ወይም ለሌላ ሕክምና ቀጠሮ ኖሮት በሰዓቱ ባይደርስ ተገቢውን ሕክምና እንዳያገኝ ሊያደርገው ይችላል።

      ያም ሆኖ በአንዳንድ ቦታዎች ቀጠሮ ማክበር ያን ያህል አስፈላጊ ሆኖ አይታይም። እንዲህ ባሉ አካባቢዎች የምንኖር ከሆነ ማርፈድ በቀላሉ ልማድ ሊሆንብን ይችላል። እንዲህ ዓይነቱ ልማድ ካለብን ቀጠሮ የማክበር ፍላጎት ማዳበራችን አስፈላጊ ነው። በሰዓቱ መገኘት ያለውን ጥቅም መረዳታችን ቀጠሮ አክባሪ እንድንሆን እንደሚረዳን ምንም ጥርጥር የለውም። ቀጠሮ የምናከብርባቸው አንዳንድ ምክንያቶች ምንድን ናቸው? ቀጠሮ እንዳናከብር የሚያደርጉንን አንዳንድ ተፈታታኝ ሁኔታዎች መወጣት የምንችለው እንዴት ነው? ሰዓት አክባሪዎች መሆናችን ምን ጥቅሞች ሊያስገኝልን ይችላል?

      ይሖዋ የቀጠረውን ጊዜ የሚያከብር አምላክ ነው

      ቀጠሮ እንድናከብር የሚያደርገን ከሁሉ የላቀው ምክንያት የምናመልከውን አምላክ መምሰል ስለምንፈልግ

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ