የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • እውነትን ማስተማር
    የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ—2016 | ነሐሴ
    • ክርስቲያናዊ ሕይወት

      እውነትን አስተምሩ

      ከመስከረም ጀምሮ የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ “እውነትን አስተምሩ” የሚል አዲስ የአቀራረብ ናሙና ይዞ ይወጣል። ይህን አዲስ አቀራረብ ስንጠቀም ዓላማችን አንድ ጥያቄና ጥቅስ በመጠቀም የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ትምህርቶች ለሰዎች ማስተማር ነው።

      ግለሰቡ ፍላጎት እንዳለው ካስተዋልን ጽሑፎችን በመስጠት ወይም በjw.org ላይ የወጣን አንድ ቪዲዮ በማሳየት ቀጥሎ የምንመጣበትን ጊዜ በጉጉት እንዲጠብቅ ማድረግ እንችላለን። በጀመርነው ርዕሰ ጉዳይ ላይ ውይይቱን ለመቀጠል በጥቂት ቀናት ውስጥ ተመልሰን መሄድ ይኖርብናል። ይህ አዲስ የአቀራረብ ናሙና እና የተማሪ ክፍሎቹ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል? (በአማርኛ አይገኝም) በተባለው መጽሐፍ ላይ በሚገኙ ርዕሶች ላይ የተመሠረቱ ናቸው፤ ይህ መጽሐፍ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? በሚባለው መጽሐፍ ላይ ተመሥርቶ ቀለል ባለ መንገድ የተዘጋጀ ነው። መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ በመጠቀም ተመላልሶ መጠየቅ ለማድረግ ወይም ጥናት ለመምራት የሚረዱ ተጨማሪ ሐሳቦችንና ጥቅሶችን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በተባለው መጽሐፍ ላይ ማግኘት እንችላለን።

      ወደ ሕይወት የሚወስደው መንገድ አንድ ብቻ ነው። (ማቴ 7:13, 14) የተለያየ ሃይማኖትና አስተዳደግ ያላቸውን ሰዎች ስናነጋግር የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት በግለሰብ ደረጃ እንዲማርካቸው አድርገን ማቅረብ ይኖርብናል። (1ጢሞ 2:4) በተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ርዕሶች ላይ ይበልጥ ውይይት ስናደርግ “የእውነትን ቃል በአግባቡ በመጠቀም” ረገድ ያለን ችሎታ ይበልጥ ይሻሻላል፤ ይህ ደግም ደስታችን እንዲጨምርና እውነትን በማስተማር ረገድ ስኬታማ እንድንሆን ይረዳናል።—2ጢሞ 2:15

  • በመስከረም ወር የመጠበቂያ ግንብ መጽሔት ለማበርከት የሚደረግ ልዩ ዘመቻ
    የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ—2016 | ነሐሴ
    • ክርስቲያናዊ ሕይወት

      በመስከረም ወር የመጠበቂያ ግንብ መጽሔት ለማበርከት የሚደረግ ልዩ ዘመቻ

      መጠበቂያ ግንብ ቁጥር 5 2016 | ማጽናኛ ማግኘት የምትችለው ከየት ነው?

      በዛሬው ጊዜ፣ እያንዳንዱ ሰው ማጽናኛ ማግኘት ያስፈልገዋል። (መክ 4:1) በመሆኑም በመስከረም ወር ስለ ማጽናኛ የሚናገረውን የመጠበቂያ ግንብ እትም ለማበርከት ልዩ ጥረት እናደርጋለን። ይህን መጽሔት በስፋት ለማሰራጨት የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን። ሆኖም ሰዎችን ለማጽናናት እነሱን በአካል ማነጋገር ስላለብን ቤት ላልተገኙ ሰዎች መጽሔቱን በራቸው ላይ ትተን አንሄድም።

      ምን ማለት እንችላለን?

      “ማናችንም ብንሆን በሆነ ወቅት ላይ ማጽናኛ ማግኘት ያስፈልገናል። ግን ማጽናኛ ማግኘት የምንችለው ከየት ነው? [2 ቆሮንቶስ 1:3, 4⁠ን አንብብ።] ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም አምላክ ማጽናኛ የሚሰጠን እንዴት እንደሆነ ያብራራል።”

      ግለሰቡ ፍላጎት ካለውና መጽሔቱን ከወሰደ ደግሞ . . .

      መጽሐፍ ቅዱስን መማር የሚኖርብን ለምንድን ነው? የሚለውን ቪዲዮ አሳየው።

      መጽሐፍ ቅዱስ እንዲያጠና ግብዣ አቅርብለት።

      ለተመላልሶ መጠይቅ መሠረት ጣል

      ተመልሰህ ስትመጣ ልትመልስለት የምትችል አንድ ጥያቄ አንሳ፤ ለምሳሌ “አምላክ መከራ እንዲኖር የፈቀደው ለምንድን ነው?” ብለህ ልትጠይቀው ትችላለህ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ