መዝሙር 82
“ብርሃናችሁ ይብራ”
በወረቀት የሚታተመው
1. “ያለም ብርሃን ናችሁ”
ብሎናል ጌታ፤
ብርሃናችን ይብራ
ቀንና ማታ።
የሰላም ምሥራች ይዟል
ያምላክ ቃል፤
ሰዎችን ስናስተምር
ደምቆ ያበራል።
2. ምሥራቹ ብርሃን
ይፈነጥቃል፤
መል’ክቱ መነገር
ይኖርበታል።
ቃሉ ይመራናል
ብርሃናችን ነው፤
ሰዎች ብርሃኑን ይዩ
እውነትን አውቀው።
3. መልካሙ ሥራችን
ብርሃን ያበራል፤
ለትምህርታችንም
ውበት ይሰጣል።
እንቀጥል ብርሃኑን
ማብራታችንን፤
ይህ ነው በይሖዋ ዘንድ
የሚያስወድደን።
(በተጨማሪም መዝ. 119:130ን፣ ማቴ. 5:14, 15, 45ን እና ቆላ. 4:6ን ተመልከት።)