ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ማቴዎስ 6-7
ከሁሉ አስቀድማችሁ የአምላክን መንግሥት ፈልጉ
ኢየሱስ በጸሎት ናሙናው ላይ እንደጠቆመው ከሁሉ በላይ ሊያሳስበን የሚገባው ከይሖዋ ዓላማና ከመንግሥቱ ጋር የተያያዘ ጉዳይ ነው።
የአምላክ ስም
የአምላክ መንግሥት
የአምላክ ፈቃድ
የዕለት ምግባችን
የኃጢአት ይቅርታ
ከፈተና መዳን
በጸሎቴ ውስጥ ላካትታቸው የምችላቸው ከመንግሥቱ ጋር የተያያዙ አንዳንድ ጉዳዮች፦
የስብከቱ ሥራ እንዲስፋፋ
አምላክ በቅዱስ መንፈሱ አማካኝነት በስደት ላይ ያሉ ወንድሞችን እንዲያበረታ
አምላክ ቲኦክራሲያዊ የግንባታ ፕሮጀክቶችን ወይም የስብከት ዘመቻዎችን እንዲባርክ
አምላክ አመራር ለሚሰጡ ወንድሞች ጥበብና ብርታት እንዲሰጥ
ሌሎች ጉዳዮች