የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb18 ነሐሴ ገጽ 7
  • ኢየሱስ ለወንድምህም ጭምር ሞቶለታል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ኢየሱስ ለወንድምህም ጭምር ሞቶለታል
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2018
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ለጉባኤው አንድነት የበኩልህን አስተዋጽኦ አበርክት
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • የክርስቶስ ዓይነት አስተሳሰብ ይኑራችሁ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • “እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ”
    እውነተኛው አንድ አምላክ ያስገኘው የአምልኮ አንድነት
  • “ከእነዚህ ከትናንሾቹ መካከል አንዱንም” አታሰናክሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2021
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2018
mwb18 ነሐሴ ገጽ 7
ኢየሱስ ተከታዮቹን ሲያነጋግር

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ኢየሱስ ለወንድምህም ጭምር ሞቶለታል

ኢየሱስ ፍጹም ላልሆኑ ሰዎች ሕይወቱን መሥዋዕት አድርጓል። (ሮም 5:8) ኢየሱስ ሕይወቱን በመስጠት ለእኛ በግለሰብ ደረጃ ፍቅር እንዳሳየን ማስታወስ አይከብደን ይሆናል። ሆኖም ክርስቶስ ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለወንድማችንም ጭምር እንደሞተለት መዘንጋት አይኖርብንም። ልክ እንደ እኛ ፍጹማን ላልሆኑ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የክርስቶስን ዓይነት ፍቅር ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? ሦስት መንገዶችን እንመልከት። አንደኛ፣ ከእኛ የተለየ አስተዳደግ ካላቸው ሰዎች ጋር ጭምር ለመቀራረብ ጥረት ማድረግ እንችላለን። (ሮም 15:7፤ 2ቆሮ 6:12, 13) ሁለተኛ፣ ሌሎችን ቅር ሊያሰኝ የሚችል ነገር ከመናገር ወይም ከማድረግ ለመቆጠብ ጥረት ማድረግ ያስፈልገናል። (ሮም 14:13-15) በመጨረሻም፣ የበደሉንን ሰዎች ይቅር ለማለት ፈጣኖች መሆን አለብን። (ሉቃስ 17:3, 4፤ 23:34) በእነዚህ መንገዶች ኢየሱስን ለመምሰል ብርቱ ጥረት የምናደርግ ከሆነ ይሖዋ ሰላምና አንድነት በመስጠት ጉባኤውን መባረኩን ይቀጥላል።

ይበልጥ ውብ መሆን! የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ሚኪ የአዲሱ ጉባኤዋ አባላት በደስታ ሲቀበሏት

    ሚኪ መጀመሪያ ላይ ስለ ጉባኤዋ ምን ተሰምቷት ነበር?

  • ሚኪ ጉባኤዋ ውስጥ ባሉት ሰዎች ተበሳጭታ

    ለጉባኤዋ አሉታዊ አመለካከት እንዲያድርባት ያደረገው ምንድን ነው?

  • ኢየሱስ ተከታዮቹ እንቅልፍ ወስዷቸው የነበረ ቢሆንም ደግነት አሳይቷቸዋል

    ኢየሱስ የተወው ምሳሌ አመለካከቷን እንድታስተካክል የረዳት እንዴት ነው? (ማር 14:38)

  • ሚኪ አንድ ትንሽ ልጅ ከእሷ ጋር ተጋጭቶ የምትጠጣውን ነገር ልብሷ ላይ ሲያስደፋት ስትስቅ

    ምሳሌ 19:11 ለእምነት ባልንጀሮቻችን አዎንታዊ አመለካከት እንድንይዝ የሚረዳን እንዴት ነው?

ለማሰላሰል የሚረዳ ጥያቄ፦

ችላ ብዬ ማለፍ ሲኖርብኝ በውስጤ አምቄ የያዝኳቸው በደሎች ይኖሩ ይሆን?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ