የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የርዕስ ማወጫ
    መጠበቂያ ግንብ—2012 | መስከረም 1
    • © 2012 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania. የባለቤቱ መብት በሕግ የተጠበቀ ነው።

  • አምላክ በእርግጥ ለሴቶች ያስብላቸዋል?
    መጠበቂያ ግንብ—2012 | መስከረም 1
    • አምላክ በእርግጥ ለሴቶች ያስብላቸዋል?

      “ጥንቱንም ኃጢአት ከሴት ተገኘች፤ ስለሷም ሁላችን እንሞታለን።”—መጽሐፈ ሲራክ፣ ሁለተኛው መቶ ዘመን ዓ.ዓ.

      “የዲያብሎስ መግቢያ በር አንቺ ነሽ፤ የተከለከለውን ፍሬ የቀጠፍሽ አንቺ ነሽ፤ መለኮታዊውን ሕግ መጀመሪያ የጣስሽ አንቺ ነሽ። . . . በአምላክ አምሳል የተፈጠረውን ወንድ በቀላሉ ያጠፋሽ አንቺ ነሽ።”—ተርቱሊያን፣ ኦን ዚ አፓረል ኦቭ ዊሜን፣ ሁለተኛው መቶ ዘመን ዓ.ም.

      እነዚህ ጥንታዊ ጥቅሶች የተወሰዱት ከመጽሐፍ ቅዱስ አይደለም። ይሁንና በሴቶች ላይ የሚፈጸመውን በደል ትክክል ለማስመሰል ለብዙ መቶ ዘመናት ሲሠራባቸው ቆይቷል። በዛሬው ጊዜም እንኳ ሳይቀር አንዳንድ ጽንፈኞች፣ በሴቶች ላይ የሚደርሰው ጭቆና ተገቢ እንደሆነ አድርገው ለማቅረብ ሲሉ ሃይማኖታዊ ጽሑፎችን ይጠቅሳሉ፤ እነዚህ ሰዎች ለሰው ዘር ችግሮች ተጠያቂዎቹ ሴቶች እንደሆኑ ይናገራሉ። ይሁን እንጂ አምላክ፣ ሴቶችን የፈጠረው በወንዶች እንዲናቁና እንዲበደሉ ነበር? ስለዚህ ጉዳይ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል እስቲ እንመልከት።

      አምላክ ሴቶችን ረግሟቸዋል?

      አልረገማቸውም። አምላክ የረገመው ‘ዲያብሎስ ተብሎ የሚጠራውን የመጀመሪያውን እባብ’ እንጂ ሴቶችን አይደለም። (ራእይ 12:9፤ ዘፍጥረት 3:14) አምላክ፣ አዳም በሚስቱ ላይ “የበላይ” እንደሚሆን ሲናገር ወንዶች ሴቶችን እንዲጨቁኑ መፍቀዱ አልነበረም። (ዘፍጥረት 3:16) ከዚህ ይልቅ የመጀመሪያዎቹ ባልና ሚስት ኃጢአት መሥራታቸው የሚያስከትለውን አሳዛኝ መዘዝ መተንበዩ ነበር።

      በመሆኑም በሴቶች ላይ የሚደርሰው በደል የሰው ልጆች ኃጢአተኛ መሆናቸው ያስከተለው ውጤት እንጂ የአምላክ ፈቃድ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ፣ ለመጀመሪያው ኃጢአት ስርየት እንዲገኝ ሲባል ሴቶች በወንዶች መጨቆን እንዳለባቸው አይገልጽም።—ሮም 5:12

      አምላክ ሴትን የፈጠራት የወንድ የበታች አድርጎ ነው?

      አይደለም። ዘፍጥረት 1:27 “እግዚአብሔር ሰውን በራሱ መልክ ፈጠረው፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው” በማለት ይናገራል። በመሆኑም ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ሲፈጠሩ የአምላክን ባሕርያት የማንጸባረቅ ችሎታ ተሰጥቷቸዋል። አዳምና ሔዋን በስሜትም ሆነ በአካላዊ ሁኔታ የተለያዩ ቢሆኑም ሁለቱም አንድ ዓይነት መመሪያ የተሰጣቸው ከመሆኑም ሌላ በፈጣሪያቸው ፊት እኩል መብት ነበራቸው።—ዘፍጥረት 1:28-31

      ሔዋን ቅርጫት ስትሠራ፣ አዳም ደግሞ ፍሬ ሲለቅም

      ሔዋን የተፈጠረችው ለአዳም ረዳትና ማሟያ እንድትሆን ነበር

      ሔዋን ከመፈጠሯ በፊት አምላክ ለአዳም “የሚስማማውን ረዳት አበጅለታለሁ” ብሎ ነበር። (ዘፍጥረት 2:18) “ረዳት” ወይም “ማሟያ” የሚለው ቃል ሴቲቱ ከወንዱ ታንስ እንደነበር የሚያመለክት ነው? አይደለም፤ ምክንያቱም ይህ የዕብራይስጥ ቃል “አቻ” ወይም ለወንዱ “ተመጣጣኝ የሆነ ረዳት” ተብሎም ሊተረጎም ይችላል። የቀዶ ጥገና ሐኪምና ማደንዘዣ የሚሰጥ ባለሙያ በቀዶ ጥገና ወቅት አንዱ የሌላው ረዳት በመሆን ስለሚያከናውኑት የሥራ ድርሻ አስብ። አንዱ የሌላውን ወገን እገዛ ሳያገኝ ብቻውን

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ