የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb20 ነሐሴ ገጽ 3
  • መጨረሻው እየቀረበ ሲመጣ ጸንታችሁ ቁሙ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መጨረሻው እየቀረበ ሲመጣ ጸንታችሁ ቁሙ
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2020
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አምላክን የሚያስደስቱ ባሕርያትን አዳብሩ—ድፍረት
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2017
  • ደፋር መሆን ያን ያህል ከባድ አይደለም
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
  • “ደፋር . . . ሁን፤ ሥራህንም ጀምር”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017
  • ድፍረት ስጠኝ
    ለይሖዋ ‘በደስታ ዘምሩ’
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2020
mwb20 ነሐሴ ገጽ 3

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መጨረሻው እየቀረበ ሲመጣ ጸንታችሁ ቁሙ

አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? በቅርቡ የሚያጋጥሙን አስደናቂ ነገሮች ድፍረታችንንና በይሖዋ ላይ ያለንን እምነት ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ ይፈትኑታል። የሐሰት ሃይማኖት ሲጠፋ ታላቁ መከራ ይጀምራል። (ማቴ 24:21፤ ራእይ 17:16, 17) ውጥረት በሚነግሥበት በዚያ ጊዜ ኃይለኛ የፍርድ መልእክት ማወጅ ሊኖርብን ይችላል። (ራእይ 16:21) የማጎጉ ጎግ ጥቃት ይሰነዝርብናል። (ሕዝ 38:10-12, 14-16) ይሖዋም ሕዝቡን ለመጠበቅ ሲል “ሁሉን ቻይ በሆነው አምላክ ታላቅ ቀን [የሚካሄደውን] ጦርነት” ይጀምራል። (ራእይ 16:14, 16) ወደፊት እነዚህ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙን ደፋር ሆነን ለመገኘት በአሁኑ ጊዜ የእምነት ፈተናዎች ሲደርሱብን ጸንተን መቆም ይኖርብናል።

ይህን ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?

  • ላቅ ላሉት የይሖዋ የሥነ ምግባር መሥፈርቶች በድፍረት ጥብቅና ቁሙ።—ኢሳ 5:20

  • ከእምነት ባልንጀሮቻችሁ ጋር በመሰብሰብ ይሖዋን ማምለካችሁን ቀጥሉ።—ዕብ 10:24, 25

  • ከይሖዋ ድርጅት የሚመጣውን መመሪያ ለመቀበል ፈጣን ሁኑ።—ዕብ 13:17

  • ይሖዋ በጥንት ዘመን ሕዝቦቹን ያዳነው እንዴት እንደሆነ አሰላስሉ።—2ጴጥ 2:9

  • ወደ ይሖዋ ጸልዩ፤ በእሱም ታመኑ።—መዝ 112:7, 8

ከፊታችን የሚጠብቁን ድፍረት የሚጠይቁ ክስተቶች—ተቀንጭቦ የተወሰደ የሚለውን አጭር ድራማ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ‘ከፊታችን የሚጠብቁን ድፍረት የሚጠይቁ ክስተቶች’ ከተባለው ቪዲዮ ላይ የተወሰደ ፎቶግራፍ። አንዲት እህት በስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ሆና ስለ ጉባኤዎች ውህደት የሚገልጸውን ማስታወቂያ ካነበበች በኋላ በስጋት ስትመለከት።

    አስፋፊዎቹ ጉባኤያቸው ከሌሎች ጉባኤዎች ጋር ሲዋሃድ ምን የታዛዥነት ፈተና አጋጠማቸው?

  • ‘ከፊታችን የሚጠብቁን ድፍረት የሚጠይቁ ክስተቶች’ ከተባለው ቪዲዮ ላይ የተወሰደ ፎቶግራፍ። ያቺው እህት ስለ ጉባኤ ድልድሉ ከሁለት እህቶች ጋር ስትነጋገር።

    ድፍረትና ታዛዥነት ምን ተያያዥነት አላቸው?

  • ‘ከፊታችን የሚጠብቁን ድፍረት የሚጠይቁ ክስተቶች’ ከተባለው ቪዲዮ ላይ የተወሰደ ፎቶግራፍ። አንድ ልጅ ‘የአምላክ መንግሥት እየገዛ ነው!’ በተባለው መጽሐፍ ላይ በሚገኘው አርማጌዶንን የሚያሳይ ሥዕል ላይ ካሰላሰለ በኋላ ተጨንቆ።

    አርማጌዶን ሲመጣ ድፍረት የሚያስፈልገን ለምንድን ነው?

  • ‘ከፊታችን የሚጠብቁን ድፍረት የሚጠይቁ ክስተቶች’ ከተባለው ቪዲዮ ላይ የተወሰደ ፎቶግራፍ። ኢዮሳፍጥና ሌሎች የይሁዳ ሰዎች ጦር ሜዳው ጋ ሲደርሱ ሁሉም የጠላት ወታደሮች ሞተው ሲያዩ።

    ከፊታችን ለሚጠብቁን ድፍረት የሚጠይቁ ክስተቶች ከአሁኑ ተዘጋጁ

    ይሖዋ ባለው የማዳን ኃይል ላይ ያለንን እምነት ለማጠናከር የሚረዳን የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ የትኛው ነው?—2ዜና 20:1-24

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ