-
ወዳጃችንም ጠላታችንም የሆነው ሻጋታ!ንቁ!—2006 | ጥር
-
-
ሻጋታ ማይኮቶክሲን የሚባሉ መርዛማ ንጥረ ነገሮች ማመንጨት የሚችል ሲሆን እነዚህም በሰዎችና በእንስሳት ላይ ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ። ለእነዚህ ንጥረ ነገሮች የምንጋለጠው ስንተነፍስ፣ ስንበላና ስንጠጣ ወይም ቆዳችን ላይ ሲያርፉ ነው። ይሁን እንጂ ሻጋታ በጣም ጠቃሚ ጎኖችም ስላሉት ሁልጊዜ ጎጂ ነው ማለት አይቻልም።
የሻጋታ ጠቃሚ ጎን
በ1928፣ አሌክሳንደር ፍሌሚንግ የተባሉት ሳይንቲስት አረንጓዴ ሻጋታ ጀርሞችን የማጥፋት ኃይል እንዳለው በአጋጣሚ ተመለከቱ። ከጊዜ በኋላ ፔኒሲሊየም ኖታተም ተብሎ የተሰየመው ይህ ሻጋታ ባክቴሪያዎችን የሚገድል ቢሆንም በሰዎችና በእንስሳት ላይ ግን ምንም ጉዳት እንደማያስከትል ተረጋገጠ። ይህ ግኝት “ከዘመናዊ መድኃኒቶች ሁሉ በርካታ ሕይወት እንዳተረፈ” የሚነገርለትን ፔኒሲሊን የተባለውን መድኃኒት ለመሥራት መንገድ ጠርጓል። ፍሌሚንግ፣ ሃዋርድ ፍሎሬ እና ኧርነስ ቼይን ከተባሉ የምርምር ባልደረቦቻቸው ጋር ላከናወኑት ሥራ ሦስቱም በ1945 በሕክምና መስክ የኖቤል ተሸላሚ ሆነዋል። ከዚያን ጊዜ ወዲህ ሻጋታ መድኃኒትነት ያላቸው ሌሎች በርካታ ንጥረ ነገሮችን ያስገኘ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ለደም መርጋት፣ ማይግሬን በመባል ለሚታወቀው ኃይለኛ ራስ ምታት እንዲሁም ፓርኪንሰንስ ዲዚዝ ለሚባለው የነርቭ ሕመም የሚሰጡት መድኃኒቶች ይገኙበታል።
ሻጋታ ለምግብ ጥሩ ጣዕም በመስጠት ረገድም ጥቅም አለው። ፎርማጆን (ቺዝ) እንደ ምሳሌ እንውሰድ። ብሪ፣ ካምምበርት፣ ብሉ ቺዝ፣ ጎርገንዞላ፣ ሮክፈርት እንዲሁም ስቲልተን የተባሉት የፎርማጆ ዓይነቶች የየራሳቸው ለየት ያለ ጣዕም ሊኖራቸው የቻለው ፔኒሲሊየም በተባለው ሻጋታ ምክንያት መሆኑን ታውቅ ነበር? በተመሳሳይም ሻጋታ የአሳማ ሥጋን ለማጣፈጥ እንዲሁም ሶይ ሶስ ለሚባለው የምግብ ማጣፈጫም ሆነ ለቢራ ጥሩ ጣዕም ለመስጠት ያገለግላል።
ሻጋታ ወይን ለመጥመቅም የሚያበረክተው አስተዋጽኦ አለ። ትክክለኛ የሆኑት የወይን ፍሬዎች በተገቢው ጊዜ ከተቆረጡና በእያንዳንዱ ዘለላ ላይ ተስማሚ መጠን ያለው ፈንገስ የሚገኝ ከሆነ ጣፋጭ ወይን መጥመቅ ይቻላል። ቦትራይተስ ሲኒሪያ የተባለው ሻጋታ በወይን ፍሬዎቹ ውስጥ ያለው የስኳር መጠን እንዲጨምር ስለሚያደርግ ጥሩ ጣዕም ይሰጠዋል። ወይኑ እንዲፈላ በሚቀመጥበት መጋዘን ደግሞ ክላዶስፖሪየም ሴላር የተባለው ሻጋታ ወይኑ የበለጠ ግሩም ጣዕም እንዲኖረው ያደርጋል። ሃንጋሪያውያን ወይን አምራቾች ‘ምርጥ የሆነ ሻጋታ ድንቅ ወይን ያስገኛል’ የሚል ምሳሌያዊ አባባል አላቸው።
የሻጋታ ጎጂ ገጽታ
አንዳንድ የሻጋታ ዓይነቶች ጎጂ መሆናቸው ከታወቀ ቆይቷል። በስድስተኛው መቶ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በፊት አሦራውያን ክላቪሲፐስ ፐርፑሪያ በተባለው ሻጋታ በመጠቀም የጠላቶቻቸውን የውኃ ጉድጓዶች ይመርዙ ነበር። ይህም ጥንታዊ ባዮሎጂያዊ የጦር ስልት መሆኑ ነው። አንዳንድ ጊዜ በአጃ ላይ የሚበቅለው ይኸው የሻጋታ ዝርያ በመካከለኛው መቶ ዘመን ብዙ ሰዎች በሚጥል ሕመም፣ ሰውነትን በኃይል በሚያቃጥል ስሜት፣ በማይሽር ቁስል እንዲሁም በቅዠት እንዲሠቃዩ አድርጓቸዋል። ዛሬ ኧርገቲዝም በመባል የሚጠራው ይህ በሽታ በወቅቱ የቅዱስ አንቶኒ እሳት ይባል ነበር፤ የዚህ ዓይነት ስያሜ የተሰጠው በበሽታው የተጠቁ ብዙ ሰዎች ተአምራዊ ፈውስ እንደሚያገኙ
-
-
መልስህ ምንድን ነው?ንቁ!—2006 | ጥር
-
-
1. የገሊላ ባሕር።—ዮሐንስ 6:1, 16
◆ ኢየሱስ እና ጴጥሮስ።—ማቴዎስ 14:26-31
◆ ጴጥሮስ መጠራጠር ጀመረ፤ ኢየሱስ አልተጠራጠረም።—ማቴዎስ 14:31
2. 539 ከክርስቶስ ልደት በፊት
3. 647 ከክርስቶስ ልደት በፊት
4. 1077 ከክርስቶስ ልደት በፊት
5. ሰሜጋር።—መሳፍንት 3:31
6. ዮናታን።—1 ሳሙኤል 14:27
-