መዝሙር 1
የይሖዋ ባሕርያት
በወረቀት የሚታተመው
(ራእይ 4:11)
1. ይሖዋ ’ምላክ ሆይ፣ ታላቅ ነው ኃይልህ፤
ሁሉን ፈጥረሃል፤ የብርሃን አባት ነህ።
ይናገራል ፍጥረት ያንተን ክብር፤
ያወድሱሃል ሰማይ ምድር።
2. ዙፋንህ ጸንቷል በጽድቅ፣ በፍትሕ።
እንከን የላቸው ሕግህ፣ ት’ዛዛትህ።
ታላቅ ጥበብ እንዳለህ አውቀናል፤
ከቃልህ ይህን ተረድተናል።
3. ፍቅርህ ፍጹም ነው፣ አቻም የሌለው፤
ወደር የለውም፣ ስጦታህ ብዙ ነው፤
ደስ ይለናል ስላንተ መናገር፤
ስለ ታላቅ ስምህ መመሥከር።
(በተጨማሪም መዝ. 36:9፤ 145:6-13ን፣ መክ. 3:14ን እና ያዕ. 1:17ን ተመልከት።)