ክርስቲያናዊ ሕይወት
ለአንድ ዓመት መሞከር ትችላለህ?
ምኑን? የዘወትር አቅኚነትን! የሚያስገኝልህን የተትረፈረፈ በረከት ተመልከት!—ምሳሌ 10:22
አቅኚ ከሆንክ . . .
ለወንጌላዊ የሚያስፈልጉ ክህሎቶችን ታዳብራለህ እንዲሁም በአገልግሎት ይበልጥ ትደሰታለህ
ከይሖዋ ጋር ያለህ ዝምድና ይጠናከራል። ስለ ይሖዋ ለሌሎች በተናገርክ መጠን አስደናቂ የሆኑ ባሕርያቱ ይበልጥ እውን ይሆኑልሃል
ከራስ ፍላጎት ይልቅ ከመንግሥቱ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ማስቀደም የሚያስገኘውን እርካታና ሌሎችን ለመርዳት ራስን ማቅረብ የሚያስገኘውን ደስታ ታጣጥማለህ። —ማቴ 6:33፤ ሥራ 20:35
የወረዳ የበላይ ተመልካቹ ጉባኤውን በሚጎበኝበት ወቅት ከአቅኚዎች ጋር በሚያደርገው ስብሰባ፣ ከወረዳ ስብሰባ ጋር ተያይዞ በሚደረገው ልዩ ስብሰባ እንዲሁም በአቅኚነት ትምህርት ቤት የመካፈል መብት ታገኛለህ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስጀመርና ጥናት የመምራት አጋጣሚህ ሰፊ ይሆናል
አብረውህ ከሚያገለግሉት ጋር ይበልጥ ሰፋ ያለ ጊዜ የማሳለፍና እርስ በርስ የመበረታታት አጋጣሚ ታገኛለህ።—ሮም 1:11, 12