የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች
ከሐምሌ 4-10
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | 2 ሳሙኤል 18–19
“ቤርዜሊ—ልክን በማወቅ ረገድ ግሩም ምሳሌ”
ቤርዜሊ—አቅሙን የሚያውቅ ሰው
ዳዊት ቤርዜሊ ላደረገለት እርዳታ ከፍተኛ አድናቆት እንደነበረው አያጠራጥርም። ሆኖም ዳዊት ቤርዜሊ አብሮት እንዲሄድ የጠየቀው ለተደረገለት እርዳታ ቁሳዊ ነገር በመስጠት ብድሩን መመለስ ስለፈለገ ብቻ አይመስልም። ቤርዜሊ ባለጸጋ ስለነበር እንዲህ የመሰለው እርዳታ አያስፈልገውም። ዳዊት ይህን ያደረገው የዕድሜ ባለጸጋ የሆነው ቤርዜሊ ያለው ግሩም ባሕርይ ስለማረከው በቤተ መንግሥቱ እንዲኖር ፈልጎ ሳይሆን አይቀርም። ቤርዜሊ በቤተ መንግሥቱ መኖሩ የንጉሡ ወዳጅ የመሆን አጋጣሚ ስለሚሰጠው ትልቅ ክብር ነበር።
ቤርዜሊ—አቅሙን የሚያውቅ ሰው
ቤርዜሊ ይህን ያደረገበት አንዱ ምክንያት ዕድሜው ስለገፋና ከዚህ ጋር የተያያዙ አንዳንድ ችግሮች ስለነበሩበት ይሆናል። ምናልባትም ቤርዜሊ በሕይወት ብዙ እንደማይቆይ ተሰምቶት ሊሆን ይችላል። (መዝሙር 90:10) ዳዊትን ለመርዳት የቻለውን ሁሉ አድርጓል፤ ይሁንና የዕድሜ መግፋት ያስከተለበትን የአቅም ገደብም ተገንዝቧል። ቤርዜሊ፣ ክብርና ዝና የማግኘት ሐሳብ እውነታውን ከመመልከት እንዲያግደው አልፈቀደም። የሥልጣን ጥመኛ ከነበረው ከአቤሴሎም በተቃራኒ ቤርዜሊ ልኩን የሚያውቅ፣ ትሑትና ጥበበኛ ሰው መሆኑን አሳይቷል።—ምሳሌ 11:2
ቤርዜሊ—አቅሙን የሚያውቅ ሰው
የቤርዜሊ ታሪክ ሚዛናዊ የመሆንን አስፈላጊነት ጎላ አድርጎ ያሳያል። በአንድ በኩል ዘና ያለ ሕይወት መምራት ስለምንፈልግና ኃላፊነት ለመሸከም እንደማንበቃ ሆኖ ስለሚሰማን ብቻ አንድ ልዩ መብት ከመቀበል ወይም እንዲህ ያለውን የአገልግሎት መብት ለማግኘት ከመጣጣር ወደኋላ ማለት የለብንም። አምላክ ጥንካሬና ጥበብ እንደሚሰጠን ከታመንን ጉድለታችንን ይሞላልናል።—ፊልጵስዩስ 4:13፤ ያዕቆብ 4:17፤ 1 ጴጥሮስ 4:11
በሌላ በኩል ደግሞ ያለብንን የአቅም ገደብ አምነን መቀበል አለብን። ለምሳሌ ያህል፣ አንድ ክርስቲያን በመንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች የተጠመደ ሊሆን ይችላል። በመሆኑም ተጨማሪ ኃላፊነቶችን መቀበሉ የቤተሰቡን መንፈሳዊና ቁሳዊ ፍላጎት ማሟላትን ጨምሮ ሌሎች ቅዱስ ጽሑፋዊ ግዴታዎቹን ችላ ወደማለት ሊመራው እንደሚችል ይገነዘብ ይሆናል። በዚህ ጊዜ የቀረበለትን ተጨማሪ መብት ላለመቀበል መወሰኑ ልኩን እንደሚያውቅና ምክንያታዊ እንደሆነ የሚያሳይ አይደለም?—ፊልጵስዩስ 4:5 NW፤ 1 ጢሞቴዎስ 5:8
መንፈሳዊ ዕንቁዎች
‘ሩጫውን ጨርሱ’
19 አቅም የሚያሳጣ ችግር ቢኖርብህም ሌሎች ችግርህን እንደማይረዱልህ ከተሰማህ የሜፊቦስቴ ምሳሌ ያበረታታሃል። (2 ሳሙ. 4:4) ሜፊቦስቴ የአካል ጉዳተኛ ነበር፤ በዚያ ላይ ደግሞ ንጉሥ ዳዊት በተሳሳተ መንገድ ስለተረዳው በደል አድርሶበታል። ሜፊቦስቴ እነዚህ ነገሮች የደረሱበት በእሱ ጥፋት አይደለም። ያም ቢሆን በደረሱበት ነገሮች የተነሳ ምሬት እንዲያድርበት አልፈቀደም፤ ከዚህ ይልቅ በሕይወቱ ላጋጠሙት መልካም ነገሮች አድናቆት ነበረው። ንጉሥ ዳዊት ቀደም ሲል ላሳየው ደግነትም አመስጋኝ ነበር። (2 ሳሙ. 9:6-10) በመሆኑም ዳዊት በተሳሳተ መንገድ ተረድቶት በበደለው ወቅት ነገሩን ሰፋ አድርጎ ለመመልከት ጥረት አድርጓል። ሜፊቦስቴ፣ ዳዊት የሠራው ስህተት እንዲመረር አላደረገውም። እንዲሁም ዳዊት ባደረገበት ነገር የተነሳ ይሖዋን አልወቀሰም። ሜፊቦስቴ ትኩረት ያደረገው ይሖዋ የቀባውን ንጉሥ ለመደገፍ ማድረግ በሚችለው ነገር ላይ ነበር። (2 ሳሙ. 16:1-4፤ 19:24-30) ይሖዋ ግሩም የሆነው የሜፊቦስቴ ታሪክ በቃሉ ውስጥ እንዲመዘገብ ያደረገው ለእኛ ጥቅም ሲል ነው።—ሮም 15:4
ከሐምሌ 11-17
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | 2 ሳሙኤል 20–21
“ይሖዋ የፍትሕ አምላክ ነው”
it-1 932 አን. 1
ገባኦን
ገባኦናውያን ለበርካታ መቶ ዘመናት እንደ ሕዝብ ሆነው ቀጥለው ነበር፤ እርግጥ ንጉሥ ሳኦል ሊያጠፋቸው ሞክሮ ነበር። ሆኖም ገባኦናውያን፣ ይሖዋ የተፈጸመባቸውን ግፍ እስኪያጋልጥ ድረስ በትዕግሥት ጠብቀዋል። ይሖዋ በዳዊት ዘመን በተከሰተው ለሦስት ዓመት የዘለቀ ረሃብ አማካኝነት ይህን አድርጓል። ዳዊት ይሖዋን ጠይቆ ይህ የሆነው በደም ዕዳ ምክንያት እንደሆነ ካወቀ በኋላ ስርየት ለማስገኘት ምን መደረግ እንዳለበት ለማወቅ ገባኦናውያንን ጠየቃቸው። ገባኦናውያን ጉዳዩ “በብርና በወርቅ የሚፈታ” እንዳልሆነ ገለጹ፤ ደግሞም ይህን ማለታቸው ትክክል ነበር፤ ምክንያቱም በሕጉ መሠረት ለነፍሰ ገዳይ ሕይወት ቤዛ መቀበል አይቻልም። (ዘኁ 35:30, 31) በተጨማሪም ገባኦናውያን ያለሕጋዊ ፈቃድ ማንንም ሰው መግደል እንደማይችሉ ተገንዝበው ነበር። በመሆኑም የሳኦል ሰባት “ወንዶች ልጆች” እንዲሰጧቸው የጠየቁት ዳዊት ተጨማሪ ጥያቄ ካቀረበላቸው በኋላ ነው። የደም ዕዳው በሳኦልና በእሱ ቤት ላይ መሆኑ እንደሚጠቁመው በነፍስ ግድያው ግንባር ቀደም የነበረው ሳኦል ቢሆንም እንኳ ‘ወንዶች ልጆቹም’ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በጉዳዩ ላይ እጃቸው ሊኖርበት ይችላል። (2ሳሙ 21:1-9) ሁኔታው እንዲህ ከሆነ፣ የተፈጸመው ነገር ልጆችን በአባቶቻቸው ኃጢአት እንደመግደል አይቆጠርም (ዘዳ 24:16)፤ ከዚህ ይልቅ ይህ እርምጃ የተወሰደው “ሕይወት ስለ ሕይወት” በሚለው ሕግ መሠረት ፍትሕ እንዲፈጸም ነው።—ዘዳ 19:21
መንፈሳዊ ዕንቁዎች
‘ለደስታችን ከእኛ ጋር አብረው የሚሠሩት’ ክርስቲያን ሽማግሌዎች
14 በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የይሖዋ ሕዝቦች፣ ሰይጣንና ወኪሎቹ በመንገዳቸው ላይ ምንም ዓይነት እንቅፋት ቢያስቀምጡም አገልግሎታቸውን ይፈጽማሉ። አንዳንዶቻችን ግዙፍ ከሆኑ ችግሮች ጋር ፊት ለፊት የተፋጠጥንባቸው ጊዜያት አሉ፤ ይሁንና በይሖዋ ሙሉ በሙሉ ስለታመንን እነዚህን “ጎልያዶች” ማሸነፍ ችለናል። ያም ቢሆን ይህ ዓለም የሚያሳድርብንን ጫና ለማሸነፍ የምናደርገው ያልተቋረጠ ትግል አንዳንድ ጊዜ እንድንዝልና ተስፋ እንድንቆርጥ ሊያደርገን ይችላል። በሌላ ጊዜ ቢሆን ኖሮ ልንቋቋማቸው የምንችላቸው ነገሮች በዚህ ወቅት በመንፈሳዊ ‘ሊገድሉን’ ይችላሉ። በብዙዎች ሕይወት እንደሚታየው፣ እንዲህ ያሉ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙን ሽማግሌዎች የሚያደርጉልን ወቅታዊ እርዳታ ደስታችንና ብርታታችን እንደገና እንዲመለስ ያደርጋል። በ60ዎቹ ዕድሜ አጋማሽ ላይ የምትገኝ አንዲት አቅኚ እንዲህ ብላለች፦ “ከተወሰነ ጊዜ በፊት ጥሩ ስሜት አይሰማኝም ነበር፤ እንዲሁም አገልግሎት መውጣት አድካሚ ሆኖብኝ ነበር። ከዚያም አንድ ሽማግሌ ኃይሌ እንደተሟጠጠ ስለተገነዘበ ጠጋ ብሎ አነጋገረኝ። በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ የሚያንጽ ውይይት አደረግን። የሰጠኝን ምክር በሥራ ላይ ማዋሌ ጠቅሞኛል።” አክላም “ይህ ሽማግሌ መድከሜን አስተውሎ እኔን ለመርዳት መነሳሳቱ አፍቃሪ እንደሆነ ያሳያል!” ብላለች። ሁኔታችንን የሚከታተሉና ልክ እንደ አቢሳ እኛን ‘ለመታደግ’ ዝግጁ የሆኑ አፍቃሪ ሽማግሌዎች እንዳሉ ማወቃችን ምንኛ የሚያስደስት ነው?
ከሐምሌ 18-24
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | 2 ሳሙኤል 22
“በይሖዋ እርዳታ ታመኑ”
በእርግጥ ‘ወደ አምላክ መቅረብ’ ትችላለህ?
11 አምላክ ‘ታላቅ ኃይል’ እንዳለው ማንበብ አንድ ነገር ነው። (ኢሳይያስ 40:26) ሆኖም እስራኤላውያንን ነፃ በማውጣት ቀይ ባሕርን እንዴት እንዳሻገራቸውና ለ40 ዓመታት በምድረ በዳ ምን ያህል እንደተንከባከባቸው ማንበብ ፈጽሞ የተለየ ነገር ነው። ባሕሩ ለሁለት ከተከፈለ በኋላ እንደ ግድግዳ በቆመው ውኃ መካከል 3,000,000 የሚሆነው የእስራኤል ሕዝብ በደረቅ ምድር ሲሻገር በዓይነ ሕሊናህ ልትመለከት ትችላለህ። (ዘጸአት 14:21፤ 15:8) አምላክ እስራኤላውያንን በምድረ በዳ ምን ያህል እንደተንከባከባቸው ተመልከት። ከዐለት ውስጥ ውኃ ሲያፈልቅላቸውና ከሰማይ መና ሲያወርድላቸው በምናብህ ለማየት ሞክር። (ዘጸአት 16:31፤ ዘኍልቁ 20:11) ይህ ዘገባ ይሖዋ ኃይል እንዳለው ብቻ ሳይሆን ኃይሉን ሕዝቦቹን ለመንከባከብና ለመጠበቅ እንደሚጠቀምበት ያሳያል። የምንጸልየው “መጠጊያችንና ኃይላችን፣ ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን” ወደሆነ ኃያል አምላክ መሆኑን ማወቃችን የሚያጽናና አይደለም?—መዝሙር 46:1
‘ታማኝ መሆንህን ታሳያለህ’
እስቲ ዳዊት የተናገረውን ሐሳብ አንድ በአንድ እንመርምር። ‘ታማኝ መሆንህን ታሳያለህ’ ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ሐረግ “ፍቅራዊ ደግነትህን ታሳያለህ” ተብሎም ሊተረጎም ይችላል። እውነተኛ ታማኝነት በፍቅር ላይ የተመሠረተ ነው። ይሖዋ ለእሱ ታማኝ ከሚሆኑ ሰዎች ጋር ራሱን በፍቅር ያቆራኛል።
ታማኝነት በተግባር የሚገለጽ ከስሜት ያለፈ ነገር መሆኑን ልብ በል። ዳዊት ከራሱ ተሞክሮ እንደተረዳው ይሖዋ ታማኝ መሆኑን ያሳያል። ዳዊት ሕይወቱ በጨለማ በተዋጠበት ጊዜ ይሖዋ ይህን ታማኝ ንጉሥ ረድቶታል፣ በታማኝት ጠብቆታል እንዲሁም መመሪያ ሰጥቶታል። ውለታ የማይረሳው ዳዊት ‘ከጠላቶቹ ሁሉ እጅ ሊታደገው’ የሚችለው ይሖዋ እንደሆነ አውቋል።—2 ሳሙኤል 22:1
ታዲያ ዳዊት ከተናገረው ሐሳብ ምን ትምህርት ማግኘት እንችላለን? ይሖዋ አይለወጥም። (ያዕቆብ 1:17) ለሚያወጣው መመሪያ ታማኝ ከመሆኑም በላይ የገባውን ቃል ይፈጽማል። ዳዊት በሌላ መዝሙሩ ላይ ይሖዋ “ታማኞቹንም አይጥልም” በማለት ጽፏል።—መዝሙር 37:28
መንፈሳዊ ዕንቁዎች
ራሳችሁን ዝቅ አድርጋችሁ የመመልከት መንፈስ አዳብሩ
7 አምላክ በትሕትና ረገድ የተወው ምሳሌ በመዝሙራዊው ዳዊት ላይ ይህ ነው የማይባል በጎ ተጽዕኖ አሳድሯል። ዳዊት “የማዳንህን ጋሻ ሰጥተኸኛል፤ ድጋፍህ [“ትሕትናህ፣” NW] ታላቅ አድርጎኛል” ሲል ለይሖዋ ዘምሯል። (2 ሳሙ. 22:36) ዳዊት በእስራኤል ውስጥ ታላላቅ ነገሮችን ማከናወን የቻለው ይሖዋ ራሱን ዝቅ አድርጎ ወይም ትሑት ሆኖ ለእሱ ትኩረት ስለሰጠው እንደሆነ ተገንዝቧል። (መዝ. 113:5-7) የእኛስ ሁኔታ ከዚህ ይለያል? የባሕርይን፣ የችሎታንና የመብትን ነገር ካነሳን ማናችንስ ብንሆን ከይሖዋ ‘ያልተቀበልነው ምን ነገር አለ?’ (1 ቆሮ. 4:7) ከሁሉ እንደሚያንስ አድርጎ የሚያስብ ሰው “ታላቅ” ነው ሊባል የሚችለው የይሖዋ አገልጋይ እንደመሆኑ መጠን ይበልጥ ተፈላጊ በመሆኑ ነው። (ሉቃስ 9:48) እስቲ ይህን ጉዳይ እንመልከት።
ከሐምሌ 25-31
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | 2 ሳሙኤል 23–24
“የምትሰጡት ነገር መሥዋዕት ነው?”
it-1 146
አረውና
አረውና መሬቱን እንዲሁም ለመሥዋዕት የሚያስፈልጉትን ከብቶችና እንጨቶች በነፃ ለመስጠት ራሱን አቅርቦ የነበረ ይመስላል፤ ሆኖም ዳዊት ገንዘብ ሳይከፍል እነዚህን ነገሮች ለመቀበል አሻፈረኝ አለ። በ2 ሳሙኤል 24:24 ላይ የሚገኘው ዘገባ ዳዊት አውድማውንና ከብቶቹን በ50 የብር ሰቅል (110 ዶላር) እንደገዛ ይናገራል። ሆኖም በ1 ዜና መዋዕል 21:25 ላይ የሚገኘው ዘገባ ዳዊት ለቦታው 600 የወርቅ ሰቅል (77,000 ዶላር ገደማ) እንደከፈለ ይናገራል። የሁለተኛ ሳሙኤል ጸሐፊ የተናገረው ዳዊት የመሠዊያውን ቦታ እንዲሁም በዚያ ወቅት ላቀረበው መሥዋዕት የሚያስፈልጉትን ነገሮች ስለመግዛቱ ብቻ ነው፤ ስለዚህ እሱ የጠቀሰው ዋጋ እነዚህን ነገሮች ለመግዛት የወጣውን ገንዘብ ብቻ የሚያመለክት ይመስላል። በሌላ በኩል ደግሞ የአንደኛ ዜና መዋዕል ጸሐፊ ዘገባውን የጻፈው በኋላ ላይ በዚያ ቦታ ከተሠራው ቤተ መቅደስ አንጻር ሲሆን የመሬቱንም ግዢ አያይዞ የጠቀሰው ከቤተ መቅደሱ ግንባታ ጋር ነው። (1ዜና 22:1-6፤ 2ዜና 3:1) ቤተ መቅደሱ የተገነባበት ቦታ በጣም ትልቅ ከመሆኑ አንጻር 600ው የወርቅ ሰቅል የተከፈለው ዳዊት መጀመሪያ ላይ መሠዊያውን ለመሥራት ለተጠቀመበት ትንሽ ቦታ ሳይሆን ቤተ መቅደሱ ያረፈበትን ሰፊ ቦታ ለመግዛት ይመስላል።
‘ከእውነት መሠረታዊ ገጽታዎች’ ትምህርት ማግኘት
8 አንድ እስራኤላዊ ለይሖዋ ያለውን ልባዊ ምስጋና ለመግለጽ ሲል በራሱ ተነሳስቶ መሥዋዕት የሚያቀርብበት ጊዜ አለ፤ ወይም ደግሞ የእሱን ሞገስ ለማግኘት ሲል የሚቃጠል መሥዋዕት ሊያቀርብ ይችላል። በዚህ ወቅት ተስማሚ የሆነ እንስሳ መምረጥ እንደማያስቸግረው የታወቀ ነው። ይህ የአምላክ አገልጋይ ለይሖዋ ምርጡን መስጠት መቻሉ ያስደስተዋል። በዛሬው ጊዜ የሚገኙ ክርስቲያኖች የሙሴ ሕግ እንደሚያዘው ቃል በቃል መሥዋዕት ማቅረብ አይጠበቅባቸውም፤ ያም ሆኖ ጊዜያቸውን፣ ኃይላቸውንና ሀብታቸውን ይሖዋን ለማገልገል ስለሚጠቀሙበት መሥዋዕት ያቀርባሉ ሊባል ይችላል። ሐዋርያው ጳውሎስ ክርስቲያናዊ ተስፋችንን ‘በይፋ ማወጅ’ እንዲሁም ‘መልካም ማድረግና ያለንን ነገር ለሌሎች ማካፈል’ ይሖዋን ደስ የሚያሰኙ መሥዋዕቶች እንደሆኑ ተናግሯል። (ዕብ. 13:15, 16) የይሖዋ ሕዝቦች እንዲህ በመሰሉ እንቅስቃሴዎች በሚካፈሉበት ወቅት የሚያሳዩት መንፈስ አምላክ ለሰጣቸው ነገሮች ምን ያህል አድናቂና አመስጋኝ እንደሆኑ ያሳያል። በመሆኑም በጥንት ዘመን የነበሩ የአምላክ አገልጋዮች በፈቃደኝነት መሥዋዕቶችን በሚያቀርቡበት ወቅትም ሆነ በዛሬው ጊዜ ያሉ ክርስቲያኖች ይሖዋን በሚያገለግሉበት ጊዜ የሚያሳዩት ዝንባሌና ይህን ለማድረግ የሚያነሳሳቸው ውስጣዊ ግፊት ተመሳሳይ ነው።
መንፈሳዊ ዕንቁዎች
የሁለተኛ ሳሙኤል መጽሐፍ ጎላ ያሉ ነጥቦች
23:15-17፦ ዳዊት አምላክ ስለ ደምና ስለ ሕይወት ላወጣው ሕግ ጥልቅ አክብሮት ስለነበረው በዚህ ጥቅስ ላይ እንደተገለጸው ይህን ሕግ የሚያስጥስ የሚመስል ነገር በገጠመው ወቅት ድርጊቱን ከመፈጸም ተቆጥቧል። እኛም ብንሆን ሁሉንም የአምላክ ሕጎች በመጠበቅ ረገድ የእርሱ ዓይነት ዝንባሌ ልንኮተኩት ይገባናል።
ከነሐሴ 1-7
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | 1 ነገሥት 1–2
“ከስህተታችሁ ትማራላችሁ?”
it-2 987 አን. 4
ሰለሞን
አዶንያስና አብረውት ያሴሩት ሰዎች እምብዛም ከማትርቀው ከግዮን የሚሰማውን ሙዚቃና “ንጉሥ ሰለሞን ለዘላለም ይኑር” እያለ የሚጮኸውን ሕዝብ ሲሰሙ በፍርሃትና ግራ በመጋባት ሸሹ። ሰለሞን ገና ሥልጣን ከመያዙ የበቀል እርምጃ ለመውሰድ ፈቃደኛ ባለመሆን የእሱ ግዛት በሰላም ተለይቶ እንደሚታወቅ ፍንጭ ሰጥቷል። አዶንያስ በሰለሞን ቦታ ቢሆን ኖሮ ሰለሞን ሕይወቱን የማጣቱ አጋጣሚ ሰፊ ይሆን ነበር። አዶንያስ ሕይወቱን ለማትረፍ ወደ ቤተ መቅደሱ ሸሸ፤ ስለዚህ ሰለሞን አዶንያስን ልኮ አስጠራው። ሰለሞን አዶንያስን መጥፎ ነገር ካልተገኘበት እንደማይገደል ከነገረው በኋላ ወደ ቤቱ አሰናበተው።—1ነገ 1:41-53
it-1 49
አዶንያስ
ይሁንና ዳዊት ከሞተ በኋላ አዶንያስ ወደ ቤርሳቤህ ቀርቦ፣ የዳዊት ሞግዚትና ተንከባካቢ የነበረችውን ወጣቷን አቢሻግን እንዲድርለት ሰለሞንን እንድትጠይቅለት አግባባት። አዶንያስ በጉዳዩ የአምላክ እጅ እንዳለበት መቀበሉን ለይስሙላ የተናገረ ቢሆንም “ንግሥናው የእኔ ሊሆን [ነበር፤] እስራኤልም ሁሉ ይነግሣል ብለው ይጠብቁ [ነበር]” ማለቱ መብቱን እንደተነጠቀ የተሰማው መሆኑን ይጠቁማል። (1ነገ 2:13-21) አዶንያስ ይህን ጥያቄ ያቀረበው ንግሥናውን በማጣቱ የሆነ ካሳ እንዲሰጠው አስቦ ብቻ ሊሆን ይችላል፤ ሆኖም በጥንት ምሥራቃውያን ልማድ መሠረት የአንድን ንጉሥ ሚስቶችና ቁባቶች መውሰድ የሚችለው ሕጋዊ ወራሹ ብቻ ነበር፤ ስለዚህ የአዶንያስ ጥያቄ በልቡ ውስጥ አሁንም የሥልጣን ጥመኝነት እንዳለ ይጠቁማል። (ከ2ሳሙ 3:7፤ 16:21 ጋር አወዳድር።) ሰለሞንም አዶንያስ በእናቱ አማካኝነት ያቀረበውን ጥያቄ የተረዳው በዚህ መንገድ ስለሆነ አዶንያስ እንዲገደል አዘዘ፤ በናያህም ይህን ትእዛዝ ወዲያውኑ ፈጸመ።—1ነገ 2:22-25
መንፈሳዊ ዕንቁዎች
የአንደኛ ነገሥት መጽሐፍ ጎላ ያሉ ነጥቦች
2:37, 41-46፦ የይሖዋን ሕግ እየጣሱ ከቅጣት አመልጣለሁ ብሎ ማሰብ በጣም አደገኛ ነው! ሆን ብለው ‘ወደ ሕይወት ከሚያደርሰው ቀጭን መንገድ’ የሚወጡ ሰዎች ይህ መጥፎ አካሄድ የሚያመጣባቸውን መዘዝ ይቀምሳሉ።—ማቴዎስ 7:14
ከነሐሴ 8-14
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | 1 ነገሥት 3–4
“የጥበብ ዋጋ”
ጥሩ አርዓያም የማስጠንቀቂያ ምሳሌም ሊሆነን የሚችል ሰው
4 ሰለሞን በንግሥና ዘመኑ መጀመሪያ ላይ አምላክ በሕልም ተገልጦለት የፈለገውን እንዲጠይቅ ግብዣ አቀረበለት። እሱም ምንም ተሞክሮ እንደሌለው ስለተገነዘበ ጥበብ እንዲሰጠው ጠየቀ። (1 ነገሥት 3:5-9ን አንብብ።) ሰለሞን ሀብትና ክብር ከመጠየቅ ይልቅ ጥበብ እንዲሰጠው መለመኑ አምላክን ስላስደሰተው “ጥበብና አስተዋይ ልቡና” ብቻ ሳይሆን ብልጽግናም ሰጠው። (1 ነገ. 3:10-14) የሰለሞን ጥበብ እጅግ ታላቅ ከመሆኑ የተነሳ የሳባ ንግሥት የእሱን ጥበብ በገዛ ዓይኗ ለማየት ረጅም ርቀት ተጉዛ መምጣቷን ኢየሱስ ጠቅሷል።—1 ነገ. 10:1, 4-9
5 እርግጥ ነው፣ እኛ በግለሰብ ደረጃ ተአምራዊ በሆነ መንገድ ጥበብ እናገኛለን ብለን አንጠብቅም። ሰለሞን ‘ጥበብን የሚሰጠው’ ይሖዋ እንደሆነ ቢናገርም “ጆሮህን ወደ ጥበብ [አቅና]፣ ልብህንም ወደ ማስተዋል [መልስ]” በማለት ይህን አምላካዊ ባሕርይ ለማዳበር ጥረት ማድረግ እንደሚኖርብን ጠቁሟል። ጥበብን ከማግኘት ጋር በተያያዘ “ብትማጠን፣” “ብትፈልጋት” እና “ብትሻት” የሚሉ አባባሎችን መጠቀሙ ይህን ማድረግ ትጋት የሚጠይቅ መሆኑን ያሳያል። (ምሳሌ 2:1-6) ከዚህ በግልጽ መመልከት እንደምንችለው ጥበብን ማግኘት የሚቻል ነገር ነው።
6 ‘መለኮታዊውን ጥበብ ከፍ አድርጎ በመመልከት ረገድ የሰለሞንን ምሳሌ ለመከተል ጥረት አደርጋለሁ?’ ብለን ራሳችንን መጠየቃችን ተገቢ ነው። የኢኮኖሚው አለመረጋጋት ብዙዎች በገንዘብና በሥራቸው ላይ እንዲያተኩሩ አድርጓል፤ አሊያም ምን መማር እንዳለባቸውና እስከምን ድረስ መማር እንዳለባቸው በሚያደርጉት ውሳኔ ላይ ተጽዕኖ አሳድሮባቸዋል። አንተና ቤተሰብህስ በዚህ ረገድ እንዴት ናችሁ? የምታደርጉት ምርጫ መለኮታዊውን ጥበብ ከፍ አድርጋችሁ እንደምትመለከቱና ይህን ጥበብ ለማግኘት እንደምትጓጉ ያሳያል? ጥበብን የበለጠ ለማግኘት ቅድሚያ በምትሰጧቸው ነገሮች ወይም በግቦቻችሁ ላይ ማስተካከያ ማድረግ ይኖርባችሁ ይሆን? በእርግጥም ጥበብን ለማግኘት ጥረት የምታደርጉና ያገኛችሁትን ጥበብ በሕይወታችሁ ውስጥ የምትጠቀሙበት ከሆነ ዘላቂ ጥቅም ታገኛላችሁ። ሰለሞን እንዲህ በማለት ጽፏል፦ “በዚያን ጊዜ ጽድቅን፣ ፍትሕን፣ ሚዛናዊነትን፣ መልካሙንም መንገድ ሁሉ ትገነዘባለህ።”—ምሳሌ 2:9
መንፈሳዊ ዕንቁዎች
ይሖዋ የቃል ኪዳን አምላክ ነው
15 ይሖዋ የእምነት አባት ለሆነው ለአብርሃም በገባው ቃል መሠረት በሕጉ ሥር በብሔር መልክ የተደራጁትን የአብርሃም ዝርያዎች ባርኳቸዋል። በ1473 ከዘአበ በሙሴ እግር በተተካው በኢያሱ መሪነት እስራኤላውያኑ ወደ ከነዓን ምድር ገብተዋል። ከዚያ በኋላ የተከናወነው ምድሪቱን በየነገዱ የመከፋፈሉ ሥራ ይሖዋ ምድሪቱን ለአብርሃም ዘር እንደሚሰጥ የገባውን ቃል ያስፈጸመ ነበር። የእስራኤል ብሔር የታመነ ሆኖ ሲገኝ ይሖዋ በጠላቶቻቸው ላይ ድል እንደሚቀዳጁ የገባላቸውን ቃል ይጠብቅ ነበር። ይህ በተለይ በንጉሥ ዳዊት የግዛት ዘመን በተግባር ታይቷል። በዳዊት ልጅ በሰሎሞን ዘመን ደግሞ የአብርሃም ቃል ኪዳን ሦስተኛ ዘርፍ ፍጻሜውን አግኝቷል። “ይሁዳና እስራኤልም እንደ ባሕር አሸዋ ብዛት ብዙ ነበሩ፤ በልተውም ጠጥተውም ደስ ብሏቸው ነበር።”—1 ነገሥት 4:20
ከነሐሴ 15-21
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | 1 ነገሥት 5–6
“እጃቸው ብቻ ሳይሆን ልባቸውም በግንባታ ሥራው ተካፍሏል”
ይህን ያውቁ ኖሯል?
የሊባኖስ ዝግባ በጥንካሬው፣ በውበቱና በጥሩ መዓዛው የታወቀ ነበር፤ በምስጥ በቀላሉ የማይበላ መሆኑም ሳይጠቀስ አይታለፍም። በመሆኑም ሰለሞን ቤተ መቅደሱን ምርጥ በሆነ እንጨት መገንባት ፈልጎ ነበር። በአንድ ወቅት የሊባኖስን ተራሮች ይሸፍን የነበረው የዝግባ ዛፍ አሁን እጅግ ተመናምኗል።
it-1 424
አርዘ ሊባኖስ
የአርዘ ሊባኖስ ሳንቃ ይህን ያህል በስፋት ጥቅም ላይ እንዲውል ከመደረጉ አንጻር ዛፎቹን ለመቁረጥ፣ በሜድትራንያን የባሕር ዳርቻ ወደሚገኙት ወደ ጢሮስ ወይም ወደ ሲዶና ለማጓጓዝ፣ እንዲሁም አንድ ላይ አስሮ በባሕር ላይ በማንሳፈፍ ምናልባትም ወደ ኢዮጴ እንዲደርሱ ለማድረግ በሺዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞች ያስፈልጉ ነበር። ከዚያም ሳንቃዎቹን በመሬት ላይ አጓጉዘው ኢየሩሳሌም ያደርሷቸዋል። ይህ ሥራ የተከናወነው በሰለሞንና በኪራም መካከል በተደረገው ውል አማካኝነት ነው። (1ነገ 5:6-18፤ 2ዜና 2:3-10) የሳንቃዎቹ አቅርቦት ከዚያ በኋላም ስለቀጠለ ሰለሞን በግዛት ዘመኑ ‘አርዘ ሊባኖሱን ከብዛቱ የተነሳ እንደ ሾላ ዛፍ’ እንዳደረገው ሊገለጽ ችሏል።—1ነገ 10:27፤ ከኢሳ 9:9, 10 ጋር አወዳድር።
it-2 1077 አን. 1
ቤተ መቅደስ
ሰለሞን ሥራውን ለማደራጀት ከመላው እስራኤል 30,000 ሰዎችን በመመልመል በየወሩ አሥር አሥር ሺህ እያደረገ በየተራ ወደ ሊባኖስ ይልካቸው ነበር፤ እነሱም በየመሃሉ ለሁለት ወር በቤታቸው ይቀመጡ ነበር። (1ነገ 5:13, 14) ሰለሞን በምድሪቱ ከሚኖሩት “የባዕድ አገር ሰዎች” መካከል 70,000ዎቹን የጉልበት ሠራተኞች፣ 80,000ዎቹን ደግሞ ድንጋይ ጠራቢዎች አድርጎ መለመለ። (1ነገ 5:15፤ 9:20, 21፤ 2ዜና 2:2) በተጨማሪም 550 ሰዎችን ሥራውን በበላይነት የሚቆጣጠሩ አለቆች፣ 3,300 ሰዎችን ደግሞ ረዳቶቻቸው አድርጎ ሾመ። (1ነገ 5:16፤ 9:22, 23) ከሁኔታዎች መረዳት እንደሚቻለው ከእነዚህ ሰዎች መካከል 250ዎቹ እስራኤላውያን፣ 3,600ዎቹ በእስራኤል የሚኖሩ “የባዕድ አገር ሰዎች” ነበሩ።—2ዜና 2:17, 18
መንፈሳዊ ዕንቁዎች
g 5/12 17 ሣጥን
መጽሐፍ ቅዱስ—ትክክለኛ ትንቢት የያዘ መጽሐፍ፣ ክፍል 1
ዝንፍ የማይል የጊዜ አጠባበቅ
ንጉሥ ሰለሞን በኢየሩሳሌም የቤተ መቅደሱን ሥራ እንደጀመረ የሚገልጸው በ1 ነገሥት 6:1 ላይ የሚገኘው ዘገባ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጹት ነገሮች፣ ከተባለው ጊዜ ዝንፍ ሳይሉ በትክክል እንደሚፈጸሙ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ነው። ጥቅሱ እንዲህ ይላል፦ “እስራኤላውያን ከግብፅ በወጡ በአራት መቶ ሰማንያ ዓመት፣ [479 ሙሉ ዓመታት] ሰሎሞን በእስራኤል ላይ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፣ ዚፍ በተባለው በሁለተኛው ወር ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ መሥራት ጀመረ።”
በመጽሐፍ ቅዱስ የዘመን አቆጣጠር መሠረት የሰለሞን አራተኛ ዘመነ መንግሥት የዋለው በ1034 ዓ.ዓ. ነው። ከዚህ ዓመት ጀምረን 479 ሙሉ ዓመታት ወደኋላ ስንቆጥር እስራኤላውያን ከግብፅ ወደ ወጡበት ዓመት ማለትም ወደ 1513 ዓ.ዓ. ያደርሰናል።
ከነሐሴ 22-28
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | 1 ነገሥት 7
“ከሁለቱ ዓምዶች ምን እንማራለን?”
‘ከኮረብቶቿ መዳብ ቆፍረህ ታወጣለህ’
ንጉሥ ሰለሞን በኢየሩሳሌም የሚገኘውን ቤተ መቅደስ በሚገነባበት ወቅት ከፍተኛ መጠን ያለው መዳብ ተጠቅሟል። አብዛኛው መዳብ የተገኘው አባቱ ዳዊት ከሶርያ ጋር በተዋጋ ጊዜ ካገኘው ምርኮ ነው። (1 ዜና መዋዕል 18:6-8) ካህናቱ ለመታጠብ የሚጠቀሙበት “ከቀለጠ” መዳብ የተሠራው ግዙፍ የመታጠቢያ ገንዳ 66,000 ሊትር የሚይዝና እስከ 30,000 ኪሎ ግራም የሚመዝን ነበር። (1 ነገሥት 7:23-26, 44-46) ከዚያም በቤተ መቅደሱ መግቢያ ላይ የቆሙ ሁለት ትላልቅ የመዳብ ምሰሶዎች ነበሩ። እነዚህ ምሰሶዎች ቁመታቸው 8 ሜትር ሲሆን ምሰሶዎቹ አናት ላይ 2.2 ሜትር ርዝመት ያላቸው ጉልላቶች ነበሩ፤ ውስጣቸው ክፍት የሆኑት እነዚህ ምሰሶዎች ውፍረታቸው 7.5 ሴንቲ ሜትር ዲያሜትራቸው ደግሞ 1.7 ሜትር ነበር። (1 ነገሥት 7:15, 16፤ 2 ዜና መዋዕል 4:17) እነዚህን ነገሮች ለመሥራት ብቻ የዋለውን የመዳብ መጠን ማስላት ናላ የሚያዞር ነው።
it-1 348
ቦዔዝ፣ 2
ግርማ በተላበሰው የሰለሞን ቤተ መቅደስ በረንዳ ላይ ከቆሙት ሁለት ግዙፍ የመዳብ ዓምዶች መካከል በስተ ሰሜን ያለው ስሙ ቦዔዝ ነበር፤ ትርጉሙም “በብርታት” ማለት ሳይሆን አይቀርም። በስተ ደቡብ ያለው ዓምድ ደግሞ ስሙ ያኪን ነበር፤ ትርጉሙም “[ይሖዋ] አጽንቶ ይመሥርት” ማለት ነው። ስለዚህ አንድ ሰው ወደ ምሥራቅ ዞሮ ከቀኝ ወደ ግራ አንድ ላይ ቢያነብባቸው ‘[ይሖዋ ቤተ መቅደሱን] በብርታት አጽንቶ ይመሥርት’ የሚል መልዕክት ያስተላልፋሉ።—1ነገ 7:15-21፤ የዓምድ ራስ የሚለውን ተመልከት።
መንፈሳዊ ዕንቁዎች
it-1 263
መታጠብ
ይሖዋን በቅድስና እና በንጽሕና ማምለክ የሚፈልጉ ሰዎች አካላዊ ንጽሕናቸውን እንዲጠብቁ ይጠበቅባቸዋል። በማደሪያው ድንኳን፣ በኋላም በቤተ መቅደሱ ከሚቀርበው አገልግሎት ጋር በተያያዘ ይህ ታይቷል። ሊቀ ካህናቱ አሮንና ወንዶች ልጆቹ በተሾሙበት ወቅት የክህነት ልብሳቸውን ከመልበሳቸው በፊት ታጥበው ነበር። (ዘፀ 29:4-9፤ 40:12-15፤ ዘሌ 8:6, 7) ካህናቱ እጃቸውንና እግራቸውን ለመታጠብ በማደሪያ ድንኳኑ ውስጥ በሚገኘው የመዳብ ገንዳ፣ በኋላ ደግሞ በሰለሞን ቤተ መቅደስ ውስጥ በነበረው ከቀለጠ ብረት የተሠራ ትልቅ ባሕር ውስጥ የነበረውን ውኃ ይጠቀሙ ነበር። (ዘፀ 30:18-21፤ 40:30-32፤ 2ዜና 4:2-6) በስርየት ቀን ሊቀ ካህናቱ ሁለት ጊዜ ገላውን ይታጠብ ነበር። (ዘሌ 16:4, 23, 24) ለአዛዜል የሚሆነውን ፍየል የሚወስደው ሰው፣ መሥዋዕት ሆነው ከቀረቡት እንስሳት የተረፉትን ነገሮች የሚወስደው ሰው እንዲሁም መሥዋዕት ሆና የምትቀርበውን ቀይ ላም ከሰፈር ውጭ የሚወስዳት ሰው ወደ ሰፈሩ ተመልሰው ከመግባታቸው በፊት ገላቸውን መታጠብ እንዲሁም ልብሳቸውን ማጠብ ነበረባቸው።—ዘሌ 16:26-28፤ ዘኁ 19:2-10
ከነሐሴ 29–መስከረም 4
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | 1 ነገሥት 8
“ሰለሞን በሕዝብ ፊት ያቀረበው ትሕትና የሚንጸባረቅበት ልባዊ ጸሎት”
መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናት የጸሎትህን ይዘት አሻሽል
9 ጸሎት፣ ተሰሚነት እንዲያገኝ ከልብ የመነጨ መሆን አለበት። በ1 ነገሥት ምዕራፍ 8 ላይ ተመዝግቦ እንደሚገኘው በ1026 ዓ.ዓ. የይሖዋ ቤተ መቅደስ ሲመረቅ በኢየሩሳሌም ተሰብስቦ በነበረው ሕዝብ ፊት ሰለሞን ልባዊ ጸሎት አቅርቧል። የቃል ኪዳኑ ታቦት ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ ሲገባና የይሖዋ ደመና ቤተ መቅደሱን ሲሞላው ሰለሞን አምላክን አወድሷል።
10 ሰለሞን ያቀረበውን ጸሎት በጥሞና ስታነብ ስለ ልብ በተደጋጋሚ ጊዜ እንደጠቀሰ መመልከት ትችላለህ። ሰለሞን የሰውን ልብ የሚያውቀው ይሖዋ ብቻ መሆኑን ገልጿል። (1 ነገ. 8:38, 39) በዚሁ ጸሎት ላይ አንድ ኃጢአት የሠራ ሰው ‘በፍጹም ልቡ ወደ አምላክ ቢመለስ’ ይሖዋ ሊቀበለው እንደሚችል ተገልጿል። እንዲሁም ጠላት የአምላክን ሕዝቦች ማርኮ ቢወስዳቸው ሕዝቡ ልባቸው ከይሖዋ ጋር ፍጹም እስከሆነ ድረስ ልመናቸው ተሰሚነት ያገኛል። (1 ነገ. 8:48, 58, 61) ከዚህ በግልጽ ለመመልከት እንደሚቻለው የምታቀርባቸው ጸሎቶች ከልብ የመነጩ መሆን አለባቸው።
ታማኝ እጆችን እያነሣችሁ ጸልዩ
7 በሕዝብ ፊትም ሆነ በግላችን በምንጸልይበት ጊዜ ጸሎቶቻችን የትሕትናን ዝንባሌ የሚያንጸባርቁ መሆን እንዳለባቸው የሚያመለክተውን አስፈላጊ የሆነ ቅዱስ ጽሑፋዊ መሠረታዊ ሥርዓት በአእምሯችን ልንይዝ ይገባል። (2 ዜና መዋዕል 7:13, 14) ንጉሥ ሰሎሞን በኢየሩሳሌም የተሠራው የይሖዋ ቤተ መቅደስ ለይሖዋ አገልግሎት በተወሰነበት ሥነ ሥርዓት በሕዝብ ፊት ባቀረበው ጸሎት ላይ ትሕትና አሳይቷል። ሰሎሞን በምድር ላይ ከተገነቡት እጹብ ድንቅ ሕንፃዎች መካከል አንዱን ገንብቶ መጨረሱ ነበር። ሆኖም በትሕትና እንዲህ ሲል ጸልዮአል:- “እግዚአብሔር ከሰው ጋር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ፣ ሰማይ ከሰማያትም በላይ ያለው ሰማይ ይይዝህ ዘንድ አይችልም፤ ይልቁንስ እኔ የሠራሁት ቤት እንዴት ያንስ!”—1 ነገሥት 8:27
8 ሌሎችን ወክለን በሕዝብ ፊት በምንጸልይበት ጊዜ ልክ እንደ ሰሎሞን ትሑቶች መሆን አለብን። የግብዝነት መንፈስ በሚያንጸባርቅ መንገድ መጸለይ ባይኖርብንም እንኳ የድምፃችን ቃና ትሕትናችንን ሊያሳይ ይችላል። ትሕትና የተሞላበት ጸሎት በተራቀቀ አማርኛ ወይም ደግሞ በተጋነኑ ቃላት የሚቀርብ አይደለም። የሰዎችን ትኩረት የሚስበው ጸሎቱን ወደሚያቀርበው ሰው ሳይሆን ጸሎቱ ወደሚቀርብለት አካል ነው። (ማቴዎስ 6:5) በተጨማሪም ትሕትና በጸሎታችን ውስጥ በምንናገራቸው ነገሮችም ላይ ይንጸባረቃል። በትሕትና የምንጸልይ ከሆነ አምላክ አንዳንድ ነገሮችን እኛ በፈለግነው መንገድ እንዲያከናውን እንደምንጠይቅ በሚያሳይ መንገድ አንጸልይም። ከዚህ ይልቅ ይሖዋ ከቅዱስ ፈቃዱ ጋር የሚስማማ እርምጃ እንዲወስድ እንለምነዋለን። መዝሙራዊው “አቤቱ፣ እባክህ፣ አሁን አድን፤ አቤቱ፣ እባክህ፣ አሁን አቅና” ብሎ በተማጸነ ጊዜ ትክክለኛውን አመለካከት በሚገባ አሳይቷል።—መዝሙር 118:25፤ ሉቃስ 18:9–14
መንፈሳዊ ዕንቁዎች
it-1 1060 አን. 4
ሰማይ
በኢየሩሳሌም የሚገኘውን ቤተ መቅደስ የሠራው ሰለሞን “ሰማያት፣ አዎ ሰማየ ሰማያት እንኳ” አምላክን ሊይዙት እንደማይችሉ ተናግሯል። (1ነገ 8:27) ይሖዋ የሰማያት ፈጣሪ እንደመሆኑ መጠን የሁሉም የበላይ ነው፤ “ስሙ ብቻውን ከሌሎች ሁሉ በላይ [ነው]። ግርማው ከምድርና ከሰማይ በላይ ነው።” (መዝ 148:13) አንድ ሰው አንድን ዕቃ በአውራ ጣቱ እና በትንሽ ጣቱ መሃል አድርጎ በስንዝሩ እንደሚለካ ሁሉ ይሖዋ ግዑዙን ሰማይ በቀላሉ መለካት ይችላል። (ኢሳ 40:12) ሰለሞን የተናገረው ሐሳብ አምላክ የተወሰነ መኖሪያ ቦታ እንደሌለው የሚያመለክት አይደለም። ወይም ደግሞ አምላክ ቃል በቃል በሁሉም ቦታ እና በሁሉም ነገር ውስጥ ይገኛል ማለት አይደለም። ሰለሞን ይሖዋ ‘ከመኖሪያ ቦታው ከሰማያት ሆኖ እንደሚሰማ’ መናገሩ ይህን ያሳያል፤ እዚህ ላይ የተጠቀሰው ሰማይ መንፈሳዊውን ዓለም ያመለክታል።—1ነገ 8:30, 39