የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb22 መስከረም ገጽ 13
  • “ለዘላለም በደስታ ኑር!” ያሉት ጠቃሚ ገጽታዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ለዘላለም በደስታ ኑር!” ያሉት ጠቃሚ ገጽታዎች
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2022
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችሁን በቪዲዮ ተጠቅማችሁ አስተምሩ
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2019
  • የመጠበቂያ ግንብ መጽሔት አዲሱ የጥናት እትም
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • የቴክኖሎጂ ውጤቶችን የምትጠቀመው በጥበብ ነው?
    ንቁ!—2015
  • አልተሳሳትክም! ይህ የጥናት እትም ነው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2022
mwb22 መስከረም ገጽ 13

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ለዘላለም በደስታ ኑር! ያሉት ጠቃሚ ገጽታዎች

ለዘላለም በደስታ ኑር! የተባለው መጽሐፍ ላይ ያሉትን ቪዲዮዎችና የአመለካከት ጥያቄዎች ወደሃቸዋል? “አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ”፣ “ግብ” እና “ምርምር አድርግ” የሚሉትን ገጽታዎችስ? ደቀ መዛሙርት በማድረጉ ሥራ ስትካፈል ልትጠቀምባቸው የምትችል ምን ሌሎች ገጽታዎች አሉ?—ማቴ 28:19, 20

“ለዘላለም በደስታ ኑር!” የተባለው መጽሐፍ “JW ላይብረሪ” አፕሊኬሽን ላይ ተከፍቶ። ተቀንጭቦ የተወሰደው ምስል “በክፍል 1 ሥር የሚገኙ ተጨማሪ መረጃዎች” የሚለውን ክፍል ያሳያል።

ሚዲያ፦ ማስጠናት የምትመርጠው በታተመው መጽሐፍ ተጠቅመህ ከሆነ ቪዲዮዎቹንና ሌሎች የሚዲያ ፋይሎችን አንድ ቦታ ላይ ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው? በኤሌክትሮኒክ ቅጂው ላይ ከአራቱ ዋና ዋና ክፍሎች አንዱን ምረጥ። ከተዘረዘሩት ምዕራፎች በታች በዚያ ክፍል ሥር የሚገኙ ቪዲዮዎችን ማግኘት የምትችልበት አማራጭ አለ። (ምስል 1⁠ን ተመልከት።)

“ለሕትመት የተቀናበረ” የሚለው አማራጭ፦ የምታጠኑት በኤሌክትሮኒክ መሣሪያ ተጠቅማችሁ ከሆነ በጥናቱ ወቅት አለፍ አለፍ እያልክ “ለሕትመት የተቀናበረ” የሚለውን አማራጭ መጠቀምህ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። ምዕራፉን ከከፈትክ በኋላ በገጹ አናት ላይ የሚገኘውን ሦስት ነጥብ ጠቅ አድርግ፤ ከዚያም “ለሕትመት የተቀናበረ” የሚለውን ምረጥ። ይህ የእይታ ማስተካከያ የሚጠቅምህ እንዴት ነው? እየተወያያችሁበት ያለው ነጥብ ከአጠቃላይ የምዕራፉ ጭብጥ ጋር ያለውን ዝምድና ለማስተዋል ይረዳሃል። ወደ ቀድሞው የእይታ አማራጭ ለመመለስ ሦስት ነጥቡን ጠቅ ካደረግህ በኋላ “ለዲጂታል የተዘጋጀ” የሚለውን ምረጥ።

“ለዘላለም በደስታ ኑር!” የተባለው መጽሐፍ “JW ላይብረሪ” አፕሊኬሽን ላይ ተከፍቶ። ተቀንጭበው የተወሰዱት ምስሎች “ብቃቱን አሟላለሁ?” እና “ተጨማሪ ሐሳብ” የሚሉትን ክፍሎች ያሳያሉ።

“ብቃቱን አሟላለሁ?”፦ በመጽሐፉ መጨረሻ ላይ የሚገኙት እነዚህ ሣጥኖች፣ አንድ ሰው ከጉባኤው ጋር ለመስበክና ለመጠመቅ የሚያስፈልጉትን ብቃቶች ይገልጻሉ። (ምስል 2⁠ን ተመልከት።)

ተጨማሪ ሐሳብ፦ አስፈላጊ ስለሆኑ አንዳንድ ርዕሰ ጉዳዮች ተጨማሪ ማብራሪያ ይሰጣል። በኤሌክትሮኒክ ቅጂው ላይ ከእያንዳንዱ ተጨማሪ ሐሳብ በታች ሊንክ አለ፤ ሊንኩን ጠቅ ስታደርገው ምዕራፉ ላይ ወደነበርክበት ቦታ ይመልስሃል። (ምስል 2⁠ን ተመልከት።)

ጥናትህ ለዘላለም በደስታ ኑር! የተባለውን መጽሐፍ ሳይጨርስ ቢጠመቅ እንኳ እስከ መጨረሻው አስጠናው። ከተጠመቀ በኋላም እንኳ ጥናቱን ስትመራ ሰዓቱን፣ ተመላልሶ መጠየቁንና ጥናቱን ሪፖርት ማድረግ ትችላለህ። አንድ አስፋፊ አብሮህ ጥናቱ ላይ ከተገኘና ተሳትፎ ካደረገ እሱም ሰዓቱን ሪፖርት ማድረግ ይችላል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ