የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መናዘዝ ፈውስ ያስገኛል
    መጠበቂያ ግንብ—2001 | ሰኔ 1
    • ማግኘትና ከአምልኮ አጋሮች ጋር የሚመሠረተው ገንቢ ወዳጅነት መንፈሳዊነትን መልሰው የሚያድሱ ናቸው። አዎን፣ ተጸጽቶ ንስሐ የገባው ግለሰብ በክርስቶስ ቤዛ አማካኝነት ‘የአምላክን የጸጋ ባለ ጠግነት’ ሊያጣጥም ይችላል።​—⁠ኤፌሶን 1:​7

      ‘ንጹሕ ልብ እና የቀና መንፈስ’

      ዳዊት ኃጢአቱን ከተናዘዘ በኋላ የማልረባ ነኝ በሚል ስሜት አልተዋጠም። ኃጢአትን ስለ መናዘዘ በጻፈው መዝሙር ውስጥ የተጠቀመባቸው አገላለጾች እፎይታ እንደተሰማውና አምላክን በታማኝነት ለማገልገል ቁርጥ ውሳኔ እንዳደረገ የሚያሳዩ ናቸው። ለምሳሌ ያህል፣ መዝሙር 32ን ተመልከት። በቁጥር 1 ላይ “መተላለፉ የቀረችለት ኃጢአቱም የተከደነችለት ምስጉን ነው” የሚል እናነባለን። አንድ ሰው የሠራው ኃጢአት የቱንም ያህል ከባድ ቢሆን ከልቡ ንስሐ ከገባ የኋላ ኋላ ደስታ ማግኘቱ የማይቀር ነው። ንስሐው ልባዊ መሆኑን ማሳየት የሚቻልበት አንደኛው መንገድ ልክ እንደ ዳዊት ለፈጸመው ጥፋት ሙሉ በሙሉ ተጠያቂው እርሱ መሆኑን አምኖ በመቀበል ነው። (2 ሳሙኤል 12:​13) ምንም ስህተት እንዳልፈጸመ ለማሳመን በመሞከር በይሖዋ ፊት ራሱን ንጹሕ አድርጎ ለማቅረብ ወይም ስህተቱን በሌሎች ላይ ለማላከክ አልሞከረም። ቁጥር 5 “ኃጢአቴን ለአንተ አስታወቅሁ፣ በደሌንም አልሸፈንሁም፤ ለእግዚአብሔር መተላለፌን እነግራለሁ አልሁ፤ አንተም የልቤን ኃጢአት ተውህልኝ” ይላል። እውነተኛ ንስሐ ግለሰቡ ቀደም ሲል የሠራው ኃጢአት ከሚያሳድርበት የህሊና ወቀሳ ስለሚያሳርፈው እፎይታ ያስገኝለታል።

      ዳዊት ይሖዋ ይቅር እንዲለው ከተማጸነ በኋላ “አቤቱ፣ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፣ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ” በማለት ጠይቋል። (መዝሙር 51:​10) ዳዊት “ንጹሕ ልብ” እና “የቀና መንፈስ” መጠየቁ በውስጡ ያለውን የኃጢአተኝነት ዝንባሌ እንደተገነዘበና ልቡን ለማንጻትና በአዲስ መንፈስ እንደገና ለመጀመር የአምላክ እርዳታ እንደሚያስፈልገው የሚያሳይ ነው። በትካዜ ከመዋጥ ይልቅ አምላክን በማገልገል ወደፊት ለመግፋት ቆርጦ ነበር። “አቤቱ፣ ከንፈሮቼን ክፈት፣ አፌም ምስጋናህን ያወራል” በማለት ጸልዮአል።​—⁠መዝሙር 51:​15

      ዳዊት ልባዊ ንስሐ በመግባቱና እሱን ለማገልገል ቁርጥ ውሳኔ በማድረጉ ይሖዋ የሰጠው ምላሽ ምን ነበር? “አስተምርሃለሁ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ፤ ዓይኖቼን በአንተ ላይ አጠናለሁ” በማለት ደስ የሚያሰኝ ማረጋገጫ ሰጥቶታል። (መዝሙር 32:​8) ይሖዋ ንስሐ ለሚገቡ ሰዎች ስሜትና ፍላጎት እንደሚያስብ ይህ ማረጋገጫ ይሰጣል። ይሖዋ ለዳዊት አንድን

  • የአንባብያን ጥያቄዎች
    መጠበቂያ ግንብ—2001 | ሰኔ 1
    • የአንባብያን ጥያቄዎች

      ይሖዋ በቤዛዊ መሥዋዕቱ አማካኝነት ኃጢአትን ይቅር ለማለት ፈቃደኛ ሆኖ ሳለ ክርስቲያኖች በጉባኤ ውስጥ ላሉ ሽማግሌዎች መናዘዝ የሚያስፈልጋቸው ለምንድን ነው?

      ከዳዊትና ከቤርሳቤህ ታሪክ ማየት እንደሚቻለው ዳዊት የፈጸመው ኃጢአት ከባድ ቢሆንም እንኳ ከልቡ ንስሐ በመግባቱ ምክንያት ይሖዋ ይቅር ብሎታል። ነቢዩ ናታን ቀርቦ ባነጋገረው ጊዜ ዳዊት ያለምንም ማንገራገር “እግዚአብሔርን በድያለሁ” በማለት ኃጢአቱን ተናዝዟል።​—⁠2 ሳሙኤል 12:​13

      ይሁን እንጂ ይሖዋ ከልቡ ንስሐ የገባን ኃጢአተኛ ይቅር ከማለቱም በላይ ስህተት የፈጸመው ግለሰብ በመንፈሳዊ እንዲያገግም ለመርዳት ፍቅራዊ ዝግጅቶችን ያደርጋል። በዚህ ረገድ ዳዊት እርዳታ የተደረገለት በነቢዩ ናታን በኩል ነበር። በዛሬው ጊዜ በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ በመንፈሳዊ የጎለመሱ ሽማግሌዎች አሉ። ደቀ መዝሙሩ ያዕቆብ ሁኔታውን ሲያብራራ እንዲህ ብሏል:- “ከእናንተ [በመንፈሳዊ] የታመመ ማንም ቢኖር የቤተ ክርስቲያንን ሽማግሌዎች ወደ እርሱ ይጥራ፤ በጌታም ስም እርሱን ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት። የእምነትም ጸሎት ድውዩን ያድናል ጌታም ያስነሣዋል፤ ኃጢአትንም ሠርቶ እንደ ሆነ ይሰረይለታል።”​—⁠ያዕቆብ 5:​14, 15

      ተሞክሮ ያላቸው ሽማግሌዎች ኃጢአት በመፈጸሙ ምክንያት ጸጸት የሚያብከነክነውን ሰው ለማጽናናት ማድረግ የሚችሏቸው ብዙ ነገሮች አሉ። እሱን ቀርበው በሚረዱበት ጊዜ ይሖዋን ለመምሰል ይጣጣራሉ። ጠንከር ያለ ተግሣጽ መስጠት አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜም እንኳ ሸካራ ቃላትን ከመናገር

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ