የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች
© 2024 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
ከሐምሌ 1-7
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | መዝሙር 57–59
ይሖዋ ሕዝቦቹን የሚቃወሙ ሰዎች እንዳይሳካላቸው ያደርጋል
“እስከ ምድር ዳር ድረስ”
14 እስጢፋኖስ በጠላቶቹ እጅ ከመገደሉ በፊት ድፍረት የተሞላበት ምሥክርነት ሰጥቷል። (ሥራ 6:5፤ 7:54-60) እሱ መገደሉን ተከትሎ በተከሰተው “ከባድ ስደት” የተነሳ ከሐዋርያት በስተቀር ሁሉም ደቀ መዛሙርት በመላው ይሁዳና በሰማርያ ተበታተኑ። ይሁን እንጂ ስደቱ የምሥክርነቱን ሥራ አላስቆመውም። ፊልጶስ ወደ ሰማርያ ሄዶ “ስለ ክርስቶስ ይሰብክላቸው ጀመር”፤ ይህም ጥሩ ውጤት አስገኝቷል። (ሥራ 8:1-8, 14, 15, 25) በተጨማሪም ዘገባው እንዲህ ይላል፦ “ከእስጢፋኖስ ሞት በኋላ በተቀሰቀሰው ስደት የተነሳ የተበተኑት ደቀ መዛሙርት እስከ ፊንቄ፣ ቆጵሮስና አንጾኪያ ድረስ ሄዱ፤ ቃሉን ይናገሩ የነበረው ግን ለአይሁዳውያን ብቻ ነበር። ይሁን እንጂ ከእነሱ መካከል የቆጵሮስና የቀሬና ሰዎች የሆኑ አንዳንዶች ወደ አንጾኪያ መጥተው ግሪክኛ ተናጋሪ የሆኑ ሰዎችን በማነጋገር የጌታ ኢየሱስን ምሥራች ይሰብኩላቸው ጀመር።” (ሥራ 11:19, 20) አዎ፣ በዚያን ጊዜ የተነሳው ስደት የመንግሥቱ መልእክት እንዲዳረስ ምክንያት ሆኗል።
15 በእኛ ዘመንም በቀድሞዋ ሶቪየት ኅብረት ውስጥ ተመሳሳይ ነገር ተከስቷል። በተለይ በ1950ዎቹ ዓመታት በሺዎች የሚቆጠሩ የይሖዋ ምሥክሮች በግዞት ወደ ሳይቤሪያ ተወስደው ነበር። ምሥክሮቹ በተለያዩ ቦታዎች እንዲሰፍሩ ስለተደረገ ምሥራቹ በዚያ ሰፊ ምድር ሊዳረስ ችሏል። ይህን ያህል ብዛት ያላቸው የይሖዋ ምሥክሮች በራሳቸው እስከ 10,000 ኪሎ ሜትር ርቀት ተጉዘው ምሥራቹን እንስበክ ቢሉ ለዚህ ሁሉ የሚበቃ ገንዘብ ከየት ያገኙ ነበር? አሁን ግን መንግሥት በራሱ ወጪ ልኳቸዋል። አንድ ወንድም እንዳለው “በሳይቤሪያ የሚኖሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ልበ ቅን ሰዎች እውነትን እንዲያውቁ ያደረጉት ራሳቸው ባለሥልጣናቱ ናቸው።”
መንፈሳዊ ዕንቁዎች
“ጸንታችሁ ቁሙ፤ አትነቃነቁ”
16 ልብህን አጽና። ንጉሥ ዳዊት ለይሖዋ ያለውን የማይናወጥ ፍቅር ሲገልጽ “አምላክ ሆይ፣ ልቤ ጽኑ ነው” ሲል ዘምሯል። (መዝ. 57:7) እኛም በይሖዋ ሙሉ በሙሉ በመተማመን ጽኑ ልብ እንዲኖረን ማድረግ እንችላለን። (መዝሙር 112:7ን አንብብ።) ቀደም ሲል የተጠቀሰው ቦብ ይህን ማድረጉ እንዴት እንደረዳው እንመልከት። ለምናልባቱ ካስፈለገ ደም እንደሚቀመጥለት ሲነገረው ምላሽ የሰጠው ወዲያውኑ ነው። ምንም ሆነ ምን፣ ደም የመስጠት ሐሳብ ካላቸው ወዲያውኑ ሆስፒታሉን ለቆ እንደሚወጣ ገለጸ። ቦብ “አንዳች ጥርጣሬም ሆነ ስጋት አልነበረኝም” ሲል በኋላ ላይ ተናግሯል።
17 ቦብ ሆስፒታል ከመግባቱ ከረጅም ጊዜ በፊት በአቋሙ ለመጽናት ቁርጥ ውሳኔ ባያደርግ ኖሮ እንዲህ ዓይነት ጥንካሬ አይኖረውም ነበር። በመጀመሪያ፣ ይሖዋን የማስደሰት ፍላጎት እንዲያድርበት አድርጓል። ሁለተኛ፣ መጽሐፍ ቅዱስና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎቻችን ስለ ሕይወትና ስለ ደም ቅድስና የሚናገሩትን ነገር በጥልቀት አጥንቷል። ሦስተኛ፣ የይሖዋን መመሪያ መከተል ውሎ አድሮ ዘላቂ ጥቅም እንደሚያስገኝ ራሱን አሳምኗል። እኛም ምንም ዓይነት ፈተና ቢያጋጥመን እንዲህ ዓይነት ጽኑ ልብ ሊኖረን ይችላል።
ከሐምሌ 8-14
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | መዝሙር 60–62
ይሖዋ ከለላ፣ ጥበቃና መረጋጋት ይሰጠናል
it-2 1118 አን. 7
ግንብ
ምሳሌያዊ ፍቺ። ይሖዋን በእምነትና በታዛዥነት የሚጠባበቁ ሰዎች አስተማማኝ ከለላ አላቸው፤ ዳዊትም “አንተ [ይሖዋ] መጠጊያዬ ነህና፤ ከጠላት የምትጠብቀኝ ጽኑ ግንብ ነህ” በማለት የዘመረው ለዚህ ነው። (መዝ 61:3) የስሙን ትርጉም የሚገነዘቡ እንዲሁም በስሙ የሚታመኑና ስሙን በታማኝነት የሚወክሉ ሰዎች የሚፈሩት ነገር አይኖርም፤ ምክንያቱም “የይሖዋ ስም ጽኑ ግንብ ነው። ጻድቅ ወደዚያ በመሮጥ ጥበቃ ያገኛል።”—ምሳሌ 18:10፤ ከ1ሳሙ 17:45-47 ጋር አወዳድር።
it-2 1084 አን. 8
ድንኳን
“ድንኳን” በሌሎች በርካታ ቦታዎች ላይ ሌላ ምሳሌያዊ ፍቺ አለው። ድንኳን ሰዎች እረፍት የሚያገኙበት ቦታ ነው፤ እንዲሁም ከዝናብና ከፀሐይ ጥበቃ ያደርግላቸዋል። (ዘፍ 18:1) በወቅቱ ከነበረው የእንግዳ አቀባበል ልማድ አንጻር እንግዶች ወደ አንድ ሰው ድንኳን እንዲገቡ ከተጋበዙ ተገቢውን እንክብካቤና አክብሮት እንደሚያገኙ መተማመን ይችሉ ነበር። በመሆኑም ራእይ 7:15 ስለ እጅግ ብዙ ሕዝብ ሲናገር “[አምላክ] ድንኳኑን በላያቸው ይዘረጋል” ማለቱ ጥበቃ፣ እንክብካቤና ከለላ እንደሚያገኙ ይጠቁማል። (መዝ 61:3, 4) ኢሳይያስ የአምላክ ሚስት የሆነችው ጽዮን ለምትወልዳቸው ልጆች ስለምታደርገው ዝግጅት ተናግሯል። ጽዮን “የድንኳንሽን ቦታ አስፊ” ተብላለች። (ኢሳ 54:2) ይህም ሲባል ልጆቿ ጥበቃ የሚያገኙበትን ቦታ ታሰፋለች ማለት ነው።
መለኮታዊ ሕጎች የተሰጡን ለጥቅማችን ነው
14 የአምላክ ሕግ ፈጽሞ አይለዋወጥም። በዚህ በምንኖርበት ተነዋዋጭ ዘመን ውስጥ ይሖዋ ምንጊዜም የማይለወጥ ከዘላለም እስከ ዘላለም የሚኖር አምላክ ነው። (መዝሙር 90:2) ስለ ራሱ ሲናገር “እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም” ብሏል። (ሚልክያስ 3:6) መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ተመዝግበው የሚገኙት የአምላክ መሥፈርቶች እንደ እንቧይ ካብ ዕድሜ ከሌለውና ምንጊዜም ተለዋዋጭ ከሆነው የሰው ሐሳብ በተለየ ፍጹም አስተማማኝ ናቸው። (ያዕቆብ 1:17) ለምሳሌ ያህል የሥነ ልቦና ጠበብት ልጆችን ለቀቅ አድርጎ ማሳደግን ለበርካታ ዓመታት ሲያበረታቱ ቢቆዩም ከጊዜ በኋላ አንዳንዶቹ አስተሳሰባቸውን የለወጡ ሲሆን ምክራቸው የተሳሳተ እንደነበረም አምነዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ የወጡ ዓለማዊ መሥፈርቶችና መመሪያዎች በነፋስ የተመቱ ያህል ወዲያ ወዲህ ይዋልላሉ። የይሖዋ ቃል ግን አይለዋወጥም። መጽሐፍ ቅዱስ ልጆችን እንዴት በፍቅር ማሳደግ እንደሚቻል ለበርካታ መቶ ዓመታት ምክር ሲሰጥ ቆይቷል። ሐዋርያው ጳውሎስ “አባቶች ሆይ፣ ልጆቻችሁን በጌታ ምክርና በተግሣጽ አሳድጉአቸው እንጂ አታስቈጡአቸው” ሲል ጽፏል። (ኤፌሶን 6:4) ፈጽሞ በማይለዋወጡት የይሖዋ መሥፈርቶች ላይ ትምክህት መጣል እንደምንችል ማወቁ ምንኛ ያበረታታል!
መንፈሳዊ ዕንቁዎች
የመዝሙር ሁለተኛ መጽሐፍ ጎላ ያሉ ነጥቦች
62:11፦ አምላክ የየትኛውም ኃይል እገዛ አያስፈልገውም። የብርታት ሁሉ ምንጭ እርሱ ነው። ‘ኃይል የእርሱ ነው።’
ከሐምሌ 15-21
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | መዝሙር 63–65
‘ታማኝ ፍቅርህ ከሕይወት ይሻላል’
ከአምላክ ፍቅር ማን ይለየናል?
17 የአምላክን ፍቅር ምን ያህል ከፍ አድርገህ ትመለከተዋለህ? ዳዊት “ምሕረትህ [“ፍቅራዊ ደግነትህ፣” NW] ከሕይወት ይሻላልና ከንፈሮቼ ያመሰግኑሃል። እንዲህ በሕይወቴ ዘመን አመሰግንሃለሁ፣ በአንተም ስም እጆቼን አነሣለሁ” ብሎ እንደጻፈው ይሰማሃል? (መዝሙር 63:3, 4) ከአምላክ ፍቅርና ታማኝ ወዳጅነት ጋር የሚወዳደር ይህ ዓለም ሊሰጥ የሚችለው ነገር ይኖራልን? ለምሳሌ ያህል ጥሩ ገቢ የሚያስገኝ ሰብዓዊ ሥራ መሥራት ከአምላክ ጋር የቀረበ ዝምድና በመመሥረት ከሚገኘው የአእምሮ ሰላምና ደስታ ይሻላልን? (ሉቃስ 12:15) አንዳንድ ክርስቲያኖች ይሖዋን ከመካድ ወይም ከመሞት አንዱን እንዲመርጡ የሚያደርግ ፈተና ገጥሟቸዋል። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በናዚ ማጎሪያ ካምፕ የነበሩ በርካታ የይሖዋ ምሥክሮች እንዲህ ያለ ሁኔታ ደርሶባቸው ነበር። በጣት ከሚቆጠሩት በስተቀር አብዛኞቹ ክርስቲያን ወንድሞቻችን ሞት የሚያስከትልባቸው ቢሆን እንኳ በአምላክ ፍቅር ውስጥ ለመኖር መርጠዋል። በአምላክ ፍቅር ውስጥ በታማኝነት ለመኖር የመረጡ ሁሉ ወደፊት አምላክ ይህ ዓለም ፈጽሞ ሊሰጥ የማይችለውን የዘላለም ሕይወት እንደሚሰጣቸው በእርግጠኝነት ሊጠባበቁ ይችላሉ። (ማርቆስ 8:34-36) ሆኖም የዘላለም ሕይወት ማግኘት ብቻ አይደለም።
18 ምንም እንኳ ከይሖዋ መመሪያ ርቆ ለዘላለም መኖር የማይቻል ቢሆንም ያለ ፈጣሪ ረዥም ዕድሜ መኖር ምን ሊመስል እንደሚችል ለማሰብ ሞክር። ሕይወታችን ባዶና ዓላማ ቢስ ይሆን ነበር። ይሖዋ በዚህ የመጨረሻ ዘመን ሕዝቦቹ የሚሠሩት አርኪ የሆነ ሥራ ሰጥቷቸዋል። ታላቁ የዓላማ አምላክ ይሖዋ የዘላለም ሕይወት ሲሰጠን ልንማራቸውና ልንሠራቸው የምንችላቸው ቁጥር ስፍር የሌላቸው ማራኪና ጠቃሚ የሆኑ ነገሮችንም እንደሚሰጠን እርግጠኞች ልንሆን እንችላለን። (መክብብ 3:11) ከፊታችን በሚጠብቀን ሺህ ዓመት ‘ጥልቅ የሆኑትን የእግዚአብሔርን ባለ ጠግነት፣ ጥበብና እውቀት’ መርምረን መጨረስ እንደማንችል የታወቀ ነው።—ሮሜ 11:33
“ለሁሉም ነገር አመስግኑ”
በተለይ ደግሞ አምላክን ማመስገናችን ተገቢ ነው። ይሖዋ በመንፈሳዊም ሆነ በሥጋዊ እስከ ዛሬ ስላደረጋቸውና ወደፊት ስለሚያደርጋቸው ብዙ መልካም ነገሮች አልፎ አልፎ ማሰብህ አይቀርም። (ዘዳ. 8:17, 18፤ ሥራ 14:17) ሆኖም ስለ አምላክ ጥሩነት ለአፍታ ያህል ከማሰብ ባለፈ አምላክ ለአንተም ሆነ ለቤተሰብህ ስለሰጠህ የተትረፈረፈ በረከት ለማሰላሰል ለምን ጊዜ አትመድብም? ፈጣሪህ ባሳየህ ልግስና ላይ ማሰላሰልህ ለእሱ ያለህ አድናቆት እንዲጨምር እንዲሁም ምን ያህል እንደሚወድህና ከፍ አድርጎ እንደሚመለከትህ ይበልጥ እንድትገነዘብ ያደርጋል።—1 ዮሐ. 4:9
ዘወትር በመንፈሳዊ ነገሮች ላይ አሰላስሉ
7 ማንበብ ብዙ ጥረት የሚጠይቅ ባይሆንም ማሰላሰል ግን ትኩረትን ማሰባሰብ ይጠይቃል። ፍጽምና የሚጎድለው የሰው አእምሮ ብዙ ማሰብ በማይጠይቁና እምብዛም አድካሚ ባልሆኑ ሥራዎች በቀላሉ የመወሰድ አዝማሚያ ያለው ከዚህ የተነሳ ነው። በመሆኑም ለማሰላሰል ይበልጥ አመቺ የሆነው ጊዜ ዘና የምትልበት እንዲሁም ትኩረትህን የሚሰርቁና የሚያስጨንቁ ነገሮች የሌሉበት ወቅት ነው። መዝሙራዊው ሌሊት ከእንቅልፉ የሚነቃበት ጊዜ ለማሰላሰል ጥሩ ሰዓት እንደሆነ ተረድቷል። (መዝ. 63:6) ፍጹም አእምሮ የነበረው ኢየሱስ ጸጥ ባለ ቦታ ማሰላሰልና መጸለይ ምን ያህል ጥቅም እንዳለው ተገንዝቦ ነበር።—ሉቃስ 6:12
በፍቅር በማስተማር ኢየሱስን ምሰሉ
6 ስለምንወዳቸው ነገሮች ማውራት ያስደስተናል። በጣም ስለምንወደው ነገር ስናወራ ንግግራችን ግለትና ሞቅ ያለ ስሜት የሚንጸባረቅበት ከመሆኑም ሌላ በፊታችን ላይ ደስታ ይነበባል። በተለይ ደግሞ ስለምንወደው ሰው ስንናገር እንደዚህ ዓይነት ስሜት ይታይብናል። አብዛኛውን ጊዜ ስለ ግለሰቡ የምናውቀውን ነገር ለሌሎች ለመናገር እንጓጓለን። ግለሰቡን እናሞግሰዋለን፣ እናከብረዋለን እንዲሁም ጥብቅና እንቆምለታለን። እንዲህ የምናደርገው እኛ ግለሰቡንና ባሕርይውን እንደምንወደው ሁሉ ሌሎችም ለግለሰቡ እንዲህ ዓይነት ስሜት እንዲኖራቸው ስለምንፈልግ ነው።
መንፈሳዊ ዕንቁዎች
የሌሎችን መንፈስ የምታድስ ነህ?
አንድን ሕንጻ ከመገንባት ይልቅ ማፍረስ በጣም ቀላል ነው። ንግግርን በተመለከተም ሁኔታው ተመሳሳይ ነው። ፍጽምና የጎደለን እንደመሆናችን መጠን ሁላችንም ድክመቶችና ጉድለቶች አሉብን። ንጉሥ ሰሎሞን “ትክክለኛውን ነገር የሚያደርግና ፈጽሞ ኀጢአት የማይሠራ፣ ጻድቅ ሰው በምድር ላይ የለም” ብሏል። (መክብብ 7:20) የአንድን ሰው ጉድለት ለይቶ ማወቅና ጎጂ በሆኑ ቃላት ስሜቱን ማቁሰል ቀላል ነው። (መዝሙር 64:2-4) በሌላ በኩል፣ የሚያንጽ ንግግር መናገር ጥረት ይጠይቃል።
ከሐምሌ 22-28
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | መዝሙር 66–68
ይሖዋ ሸክማችንን በየዕለቱ ይሸከምልናል
ይሖዋ ጸሎታችንን የሚመልስልን እንዴት ነው?
15 የምናቀርበው ጸሎት ብዙውን ጊዜ የሚመለሰው ተአምራዊ በሚመስል መንገድ አይደለም። ሆኖም ለሰማዩ አባታችን ታማኝ ለመሆን የሚረዳንን መልስ እናገኛለን። ስለዚህ ይሖዋ ለጸሎትህ የሚሰጥህን መልስ ለማስተዋል ጥረት አድርግ። ዮኮ የተባለች እህት ይሖዋ ጸሎቷን እንደማይመልስላት ተሰምቷት ነበር። በኋላ ግን ይሖዋን የጠየቀቻቸውን ነገሮች በዝርዝር መጻፍ ጀመረች። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የማስታወሻ ደብተሯን መለስ ብላ ስትመለከት ይሖዋ አብዛኞቹን ጸሎቶቿን እንደመለሰላት ተገነዘበች፤ እንዲያውም ከተመለሱላት ነገሮች መካከል አንዳንዶቹን መጠየቋን እንኳ ረስታ ነበር። እኛም አልፎ አልፎ ቆም ብለን ይሖዋ ጸሎታችንን እየመለሰልን ያለው እንዴት እንደሆነ ማስተዋል ይኖርብናል።—መዝ. 66:19, 20
ለነጠላ ወላጆች አሳቢነት አሳይ
ይሖዋ፣ እስራኤላውያን በአምልኳቸው ላይ የሚዘምሯቸውን ቅዱስ መዝሙራት በመንፈስ መሪነት አስጽፎ ነበር። በእስራኤል የሚኖሩ መበለቶችና አባት የሌላቸው ልጆች ይሖዋ ‘አባታቸው’ እና ‘ተሟጋቻቸው’ እንደሆነ እንዲሁም የሚያስፈልጋቸውን እርዳታ እንደሚያቀርብላቸው የሚያስታውሷቸውን በመለኮታዊ መንፈስ መሪነት የተጻፉትን ሐሳቦች ሲዘምሩ እንዴት ሊበረታቱ እንደሚችሉ መገመት ትችላለህ። (መዝሙር 68:5፤ 146:9) እኛም፣ ነጠላ ወላጆች ለረጅም ጊዜ ሊያስታውሱት የሚችሉት የሚያበረታታ ሐሳብ መናገር እንችላለን። ሩት የተባለች አንዲት ነጠላ ወላጅ ተሞክሮ ያለው አንድ አባት “ሁለቱን ወንዶች ልጆችሽን ጥሩ አድርገሽ እያሳደግሻቸው ነው። በዚሁ ቀጥይ” በማለት የተናገረበትን ጊዜ ከ20 ዓመታት በኋላም ታስታውሰዋለች። ሩት “እነዚያን ቃላት ከእሱ መስማቴ በእኔ ላይ ትልቅ ለውጥ አምጥቷል” በማለት ተናግራለች። በእርግጥም “በደግነት የተነገሩ ቃላት ጥሩ መድኃኒት” ስለሆኑ ከምናስበው በላይ ነጠላ ወላጆችን ሊያበረታቱ ይችላሉ። (ምሳሌ 15:4 ኮንቴምፖራሪ ኢንግሊሽ ቨርሽን) አንዲትን ነጠላ ወላጅ ከልብ እንድታመሰግናት የሚያደርግህን አንድ ነገር ማሰብ ትችላለህ?
አባት ለሌላቸው ልጆች አባት
“በተቀደሰ መኖሪያው ያለ አምላክ፣ አባት ለሌላቸው ልጆች አባት ነው።” (መዝሙር 68:5 የ1980 ትርጉም) በመንፈስ መሪነት የተጻፈው ይህ ሐሳብ ስለ ይሖዋ አምላክ ልብ የሚነካ ትምህርት ይሰጠናል፤ ይሖዋ እርዳታ ለሚያሻቸው ሰዎች ያስባል። አምላክ ከወላጆቻቸው አንዱን በሞት ላጡ ልጆች እንደሚያስብላቸው ለእስራኤላውያን ከተሰጠው ሕግ በግልጽ መመልከት ይቻላል። ‘አባትና እናት ስለሌለው ልጅ’ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀሰበትን በዘፀአት 22:22-24 ላይ ያለውን ሐሳብ እስቲ እንመርምር።
ይሖዋ ስኬታማ እንድትሆኑ ይረዳችኋል
17 መዝሙር 40:5ን አንብብ። ተራራ የሚወጣ ሰው ዋነኛ ግቡ የተራራው ጫፍ ላይ መድረስ ነው። ይሁንና በመንገዱ ላይ ቆም እያለ የአካባቢውን መልክዓ ምድር ማድነቅ የሚችልበት ብዙ አጋጣሚ ይኖረዋል። አንተም በተመሳሳይ በመከራ ውስጥ ብትሆንም እንኳ ይሖዋ ስኬታማ እንድትሆን እየረዳህ ያለው እንዴት እንደሆነ አልፎ አልፎ ቆም እያልክ አስብ። በእያንዳንዱ ቀን መጨረሻ ላይ እንዲህ እያልክ ራስህን ጠይቅ፦ ‘ዛሬ የይሖዋን በረከት ያየሁት በምን መንገድ ነው? የደረሰብኝ ፈተና ገና ባያበቃም ይሖዋ ለመጽናት እየረዳኝ ያለው እንዴት ነው?’ ይሖዋ ስኬታማ እንድትሆን ለመርዳት ያደረገልህን ቢያንስ አንድ ነገር ለማስተዋል ሞክር።
መንፈሳዊ ዕንቁዎች
የመዝሙር ሁለተኛ መጽሐፍ ጎላ ያሉ ነጥቦች
68:18 NW—‘ስጦታ ሆነው የተሰጡት ወንዶች’ እነማን ነበሩ? እነዚህ ወንዶች እስራኤላውያን ተስፋይቱን ምድር በወረሩበት ወቅት ከማረኳቸው ሰዎች መካከል ነበሩ። በኋላ ላይም እነዚህ ሰዎች ሌዋውያንን በሥራ እንዲያግዙ ተመድበዋል።—ዕዝራ 8:20
ከሐምሌ 29–ነሐሴ 4
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | መዝሙር 69
መዝሙር 69 ስለ ኢየሱስ ሕይወት ምን ትንቢት ይዟል?
የመሲሑን መምጣት ይጠባበቁ ነበር
17 መሲሑ ያለ ምክንያት ይጠላል። (መዝ. 69:4) ሐዋርያው ዮሐንስ፣ ኢየሱስ እንደሚከተለው ብሎ እንደተናገረ ጽፏል፦ “ሌላ ማንም ያላደረገውን ነገር [በሕዝቡ መካከል] ባላደርግ ኖሮ ኃጢአት ባልሆነባቸው ነበር፤ አሁን ግን አይተዋል፤ እንዲሁም እኔንም ሆነ አባቴን ጠልተዋል። ይሁን እንጂ ይህ የሆነው ‘ያለ ምክንያት ጠሉኝ’ ተብሎ በሕጋቸው የተጻፈው ቃል እንዲፈጸም ነው።” (ዮሐ. 15:24, 25) ብዙውን ጊዜ ‘ሕግ’ የሚለው ቃል ቅዱሳን መጻሕፍትን በሙሉ ያመለክታል። (ዮሐ. 10:34፤ 12:34) የወንጌል ዘገባዎች ኢየሱስ በተለይ በአይሁድ ሃይማኖታዊ መሪዎች ይጠላ እንደነበር ያሳያሉ። ከዚህም በተጨማሪ ክርስቶስ እንዲህ ብሎ ነበር፦ “ዓለም እናንተን የሚጠላበት ምንም ምክንያት የለውም፤ እኔ ግን ሥራው ክፉ እንደሆነ ስለምመሠክርበት ይጠላኛል።”—ዮሐ. 7:7
ለእውነተኛው አምልኮ ቅንዓት ይኑራችሁ
7 በኢየሱስ ሕይወት ውስጥ የተፈጸመ አንድ ክንውን ምን ያህል ቅንዓት እንደነበረው በግልጽ ያሳያል። ሁኔታው የተፈጸመው አገልግሎቱን በጀመረበት አካባቢ ይኸውም በ30 ዓ.ም. በዋለው የፋሲካ በዓል ወቅት ነበር። ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጡ በቤተ መቅደሱ ውስጥ “ከብቶችን፣ በጎችንና ርግቦችን የሚሸጡ ሰዎችን እንዲሁም በዚያ የተቀመጡ ገንዘብ መንዛሪዎችን” ተመለከቱ። በዚህ ጊዜ ኢየሱስ ምን አደረገ? ደቀ መዛሙርቱስ የወሰደውን እርምጃ ሲመለከቱ ምን ተሰማቸው?—ዮሐንስ 2:13-17ን አንብብ።
8 ኢየሱስ በዚህ ወቅት ያደረገውና የተናገረው ነገር ደቀ መዛሙርቱ፣ በዳዊት መዝሙሮች ውስጥ የሚገኘውን “የቤትህ ቅናት በላችኝ” የሚለውን ትንቢት እንዲያስታውሱ አደረጋቸው። (መዝ. 69:9) ደቀ መዛሙርቱ ይህን ትንቢት ያስታወሱት ለምን ነበር? ምክንያቱም ኢየሱስ ያከናወነው ነገር ለአደጋ የሚያጋልጠው በመሆኑ ነው። በቤተ መቅደሱ በሚካሄደው ስግብግብነት የሚንጸባረቅበት ንግድ ላይ የቤተ መቅደሱ ባለሥልጣናት ይኸውም የካህናቱ፣ የጸሐፍቱና የሌሎች ሰዎች እጅ ነበረበት። በመሆኑም ኢየሱስ፣ ምግባረ ብልሹነት የሚንጸባረቅበትን ይህን ሥራቸውን በማጋለጡና በማስተጓጎሉ በወቅቱ ከነበሩት ሃይማኖታዊ መሪዎች ጋር ጠላትነት ፈጥሯል። በእርግጥም ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስ ያደረገውን ነገር ሲመለከቱ ‘ለአምላክ ቤት’ ወይም ለእውነተኛው አምልኮ ‘ቅንዓት’ እንዳለው የሚናገረውን ጥቅስ ማስታወሳቸው ትክክል ነበር። ይሁንና ቅንዓት ምንድን ነው? ከጥድፊያ ስሜት ይለያል?
g95 10/22 31 አን. 4
የልብ ስብራት ይገድላል?
አንዳንዶች ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲሞት ካደረጉት ነገሮች አንዱ የልብ ስብራት እንደሆነ ይናገራሉ፤ ስለ ኢየሱስ “የተሰነዘረብኝ ነቀፋ ልቤን ሰብሮታል፤ ቁስሉም የሚድን ዓይነት አይደለም” የሚል ትንቢት ተነግሯል። (መዝሙር 69:20) ይህ ሐሳብ ቃል በቃል ሊወሰድ ይገባል? ሊሆን ይችላል፤ ምክንያቱም ኢየሱስ ከመሞቱ በፊት በነበሩት ሰዓታት አካላዊ ብቻ ሳይሆን ስሜታዊ ሥቃይም ደርሶበታል። (ማቴዎስ 27:46፤ ሉቃስ 22:44፤ ዕብራውያን 5:7) ከዚህም ሌላ ኢየሱስ ልክ ከሞተ በኋላ በጦር ሲወጋ “ደምና ውኃ” የወጣው በልብ ስብራት የተነሳ ሊሆን ይችላል። የልብ ወይም የትልቅ የደም ቧንቧ መፈንዳት፣ ደም ወደ ደረት ወይም በልብ ዙሪያ ወዳለው ፈሳሽ የያዘ ልባስ እንዲገባ ሊያደርግ ይችላል። ሁለቱም ቦታዎች ቢሆኑ ከተወጉ “ደምና ውኃ” የሚመስል ነገር ሊወጣ ይችላል።—ዮሐንስ 19:34
it-2 650
መርዛማ ተክል
መሲሑ “መርዛማ ተክል” እንዲበላ እንደሚሰጠው ትንቢት ተነግሮ ነበር። (መዝ 69:21 ግርጌ) ይህ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ከመሰቀሉ በፊት ሐሞት የተቀላቀለበት የወይን ጠጅ ሲሰጡት ከቀመሰው በኋላ ለመጠጣት ፈቃደኛ አለመሆኑን በገለጸበት ወቅት ነው፤ ይህ አደንዛዥ መጠጥ የተሰጠው ሥቃዩን ለማቅለል ሊሆን ይችላል። ማቴዎስ የዚህን ትንቢት ፍጻሜ ሲዘግብ (27:34) የተጠቀመበት ኮሌ (ሐሞት) የሚለው የግሪክኛ ቃል በግሪክኛው የሰብዓ ሊቃናት ትርጉም ላይ በመዝሙር 69:21 ላይ ይገኛል። የማርቆስ ወንጌል ግን ከርቤን ይጠቅሳል (ማር 15:23)፤ በመሆኑም አንዳንዶች እዚህ ላይ የተጠቀሰው “መርዛማ ተክል” ወይም “ሐሞት” “ከርቤ” እንደሆነ ይናገራሉ። በሌላ በኩል ደግሞ አደንዛዡ መጠጥ ሐሞትም ከርቤም ሊኖረው ይችላል።
መንፈሳዊ ዕንቁዎች
ታማኝ እጆችን እያነሣችሁ ጸልዩ
11 ብዙ ሰዎች የሚጸልዩት የሆነ ነገር ለመለመን ብቻ ነው፤ ሆኖም ለይሖዋ አምላክ ያለን ፍቅር በግልም ሆነ በሕዝብ ፊት በምንጸልይበት ጊዜ እንድናመሰግነውና እንድናወድሰው ሊገፋፋን ይገባል። ጳውሎስ “በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ። አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል” ሲል ጽፏል። (ፊልጵስዩስ 4:6, 7) አዎን፣ ከምልጃና ከልመና በተጨማሪ ለመንፈሳዊና ለሥጋዊ በረከቱ ይሖዋን ማመስገን አለብን። (ምሳሌ 10:22) መዝሙራዊው “ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ሠዋ፣ ለልዑልም ስእለትህን ስጥ” ሲል ዘምሯል። (መዝሙር 50:14) በተጨማሪም በዜማ የቀረበው የዳዊት ጸሎት የሚከተሉትን ልብ የሚነኩ ቃላት የያዘ ነው፦ “የእግዚአብሔርን ስም በዝማሬ አመሰግናለሁ፣ በምስጋናም ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ።” (መዝሙር 69:30) በሕዝብ ፊትም ሆነ በግል በምንጸልይበት ጊዜ እንዲህ ማድረግ አይኖርብንምን?
ከነሐሴ 5-11
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | መዝሙር 70–72
“ለቀጣዩ ትውልድ” ስለ አምላክ ኃይል ተናገሩ
ወጣቶች—የማስተዋል ችሎታችሁን አዳብሩ!
17 ከሰይጣን ወጥመዶች ለመሸሽ በበኩላችን የማያቋርጥ ትጋት አንዳንድ ጊዜም ትልቅ ድፍረት ማሳየት ይፈለግብናል። እንዲያውም አንዳንድ ጊዜ ከእኩዮቻችሁ ጋር ብቻ ሳይሆን ከመላው ዓለም ጋር እንዳልተጣጣማችሁ ሆኖ ይሰማችሁ ይሆናል። መዝሙራዊው ዳዊት እንዲህ ሲል ጸልዮአል፦ “አቤቱ፣ አንተ ተስፋዬ ነህና፣ እግዚአብሔር ሆይ፣ ከታናሽነቴ ጀምረህ መታመኛዬ ነህና። አምላኬ፣ ከታናሽነቴ ጀምረህ አስተማርኸኝ፤ እስከ ዛሬም ተአምራትህን እነግራለሁ።” (መዝሙር 71:5, 17) ዳዊት በድፍረቱ የሚታወቅ ሰው ነበር። ይሁን እንጂ ይህን ድፍረት ያዳበረው መቼ ነው? ገና ወጣት ሳለ ነበር! ዳዊት በሰፊው የሚታወቀውን ጎልያድን በመጋፈጥ ከፈጸመው ገድል በፊትም እንኳ የአባቱን መንጋ ይጠብቅ በነበረበት ጊዜ አንበሳና ድብ በመግደል የሚያስገርም ድፍረት አሳይቷል። (1 ሳሙኤል 17:34-37) ይሁን እንጂ ዳዊት “ከታናሽነቴ ጀምረህ መታመኛዬ ነህ” በማለት ላሳየው ጀግንነት ሁሉ ያመሰገነው ይሖዋን ነበር። ዳዊት በይሖዋ ላይ መደገፍ መቻሉ የገጠሙትን ፈተናዎች ሁሉ በብቃት ለመቋቋም አስችሎታል። እናንተም በይሖዋ ላይ ከተደገፋችሁ እርሱ ‘ዓለምን ለማሸነፍ’ የሚያስችል ድፍረትና ጥንካሬ ይሰጣችኋል።—1 ዮሐንስ 5:4
g 11/04 23 አን. 3
ለአረጋውያን ምን ዓይነት አመለካከት ሊኖረን ይገባል?
መዝሙራዊው “በእርጅናዬ ዘመን አትጣለኝ፤ ጉልበቴም ባለቀበት ጊዜ አትተወኝ” በማለት ጸልዮአል። (መዝሙር 71:9) አምላክ ታማኝ አገልጋዮቹ በዕድሜ መግፋት ምክንያት ዋጋ እንደሌላቸው ቢሰማቸውም እንኳን እሱ ግን ‘አይጥላቸውም።’ መዝሙራዊው ይሖዋ እንደጣለው ሆኖ አልተሰማውም፤ ከዚህ ይልቅ እያረጀ በሄደ መጠን በፈጣሪው ላይ መታመን እንደሚያስፈልገው ተገንዝቧል። ይሖዋ በእሱ ለሚታመን ሰው በዕድሜ ዘመኑ በሙሉ ድጋፍ በመስጠት ወሮታ ይከፍላል። (መዝሙር 18:25) ብዙውን ጊዜ እንዲህ ያለው ድጋፍ የሚመጣው በመሰል ክርስቲያኖች አማካኝነት ነው።
የጭንቀት ጊዜ ከመምጣቱ በፊት ይሖዋን ማገልገል
4 የብዙ ዓመት ተሞክሮ ያለህ ሰው ከሆንክ ‘አሁን ያለኝን ጉልበትና ጥንካሬ እንዴት ብጠቀምበት ይሻላል?’ ብለህ ራስህን መጠየቅህ በጣም አስፈላጊ ነው። ተሞክሮ ያካበትክ ክርስቲያን እንደመሆንህ መጠን ሌሎች የሌሏቸው አጋጣሚዎች አሉህ። ከይሖዋ የተማርከውን ነገር ለወጣቶች ማካፈል ትችላለህ። አምላክን ስታገለግል ያገኘሃቸውን ተሞክሮዎች በመናገር ሌሎችን ማበረታታት ትችላለህ። ንጉሥ ዳዊት፣ አምላክ እንዲህ ለማድረግ የሚያስችል አጋጣሚ እንዲሰጠው ጸልዮአል። “አምላክ ሆይ፤ አንተ ከልጅነቴ ጀምረህ አስተማርኸኝ፤ . . . አምላክ ሆይ፤ ሳረጅና ስሸብትም አትተወኝ፤ ክንድህን ለመጭው ትውልድ፣ ኀይልህን ኋላ ለሚነሣ ሕዝብ ሁሉ፣ እስከምገልጽ ድረስ” ሲል ጽፏል።—መዝ. 71:17, 18
5 በረጅም ዓመታት ውስጥ ያካበትከውን ጥበብ ለሌሎች ማካፈል የምትችለው እንዴት ነው? አምላክን የሚያገለግሉ ወጣቶችን ቤትህ በመጋበዝ የሚያንጽ ጊዜ ማሳለፍ ትችል ይሆን? ከእነሱ ጋር አገልግሎት በመውጣት ይሖዋን ማገልገል ምን ያህል እንደሚያስደስትህ እንዲያዩ ማድረግ ትችላለህ? ከበርካታ ዘመናት በፊት የኖረው ኤሊሁ “ዕድሜ ይናገራል፤ ረጅም ዘመን ጥበብን ያስተምራል” ብሏል። (ኢዮብ 32:7) ሐዋርያው ጳውሎስ ተሞክሮ ያካበቱ ክርስቲያን ሴቶች በቃልም ሆነ በተግባር ሌሎችን እንዲያበረታቱ አሳስቧቸዋል። “አረጋውያን ሴቶች . . . ጥሩ የሆነውን ነገር የሚያስተምሩ ይሁኑ” በማለት ጽፏል።—ቲቶ 2:3
መንፈሳዊ ዕንቁዎች
it-1 768
ኤፍራጥስ
ለእስራኤል የተመደበው ክልል ድንበር። አምላክ አብርሃምን ባነጋገረው ወቅት “ከግብፅ ወንዝ አንስቶ እስከ ታላቁ የኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ያለውን” ምድር ለአብርሃም ዘር እንደሚሰጥ ቃል ኪዳን ገብቶ ነበር። (ዘፍ 15:18) ይሖዋ ይህን ተስፋ ለእስራኤል ብሔርም ደግሞላቸዋል። (ዘፀ 23:31፤ ዘዳ 1:7, 8፤ 11:24፤ ኢያሱ 1:4) አንደኛ ዜና መዋዕል 5:9 አንዳንድ የሮቤል ዘሮች ከዳዊት ግዛት በፊት መኖሪያቸውን “በኤፍራጥስ ወንዝ በኩል እስካለው፣ ምድረ በዳው እስከሚጀምርበት ቦታ ድረስ” አስፋፍተው እንደነበረ ይናገራል። ይሁንና የኤፍራጥስ ወንዝ “ከጊልያድ በስተ ምሥራቅ” (1ዜና 5:10) 800 ኪሎ ሜትር ገደማ ስለሚርቅ ይህ ሐሳብ ሮቤላውያን ክልላቸውን ከጊልያድ በስተ ምሥራቅ እስከ ሶርያ ምድረ በዳ ጫፍ ድረስ እንዳሰፉ የሚጠቁም ሊሆን ይችላል፤ ይህ ምድረ በዳ እስከ ኤፍራጥስ ድረስ ይዘልቃል። (አ.መ.ት. “ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ እስከ ምድረ በዳው ዳርቻ ድረስ” ይላል።) ከዚህ አንጻር፣ ይሖዋ የገባው ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉ በሙሉ የተፈጸመው በዳዊትና በሰለሞን የግዛት ዘመን ይመስላል፤ በዚያ ወቅት የእስራኤል ግዛት የአራማውያን መንግሥት እስከሆነው እስከ ጾባህ ድረስ በመስፋፋቱ የኤፍራጥስ ወንዝ ዳርቻ ጋ ደርሷል፤ ይህም ከሰሜናዊ ሶርያ ጋር የሚዋሰነው የወንዙ ክፍል ሳይሆን አይቀርም። (2ሳሙ 8:3፤ 1ነገ 4:21፤ 1ዜና 18:3-8፤ 2ዜና 9:26) ኤፍራጥስ በጣም ትልቅ ወንዝ ከመሆኑ አንጻር ብዙውን ጊዜ “ወንዙ” በመባል ይጠራል።—ኢያሱ 24:2, 15፤ መዝ 72:8
ከነሐሴ 12-18
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | መዝሙር 73–74
አምላክን በማያገለግሉ ሰዎች መቅናት ብንጀምርስ?
‘ይሖዋ ተስፋ የቆረጡትን ያድናል’
14 የመዝሙር 73 ጸሐፊ ሌዋዊ ነበር። በመሆኑም በይሖዋ የአምልኮ ቦታ የማገልገል ልዩ መብት ነበረው። ያም ቢሆን እሱም እንኳ ተስፋ የቆረጠበት ጊዜ ነበር። ለምን? በክፉዎችና በእብሪተኞች መቅናት ጀምሮ ነበር፤ የቀናው በክፋታቸው ሳይሆን የተሻለ ሕይወት ያላቸው ስለመሰለው ነው። (መዝ. 73:2-9, 11-14) ሀብትና ጥሩ ሕይወት ያላቸው እንዲሁም ምንም ጭንቀት የሌለባቸው፣ በአጭር አነጋገር ሁሉ ነገር የተሳካላቸው ይመስላሉ። መዝሙራዊው ይህን ሲያይ ተስፋ ከመቁረጡ የተነሳ “በእርግጥም ልቤን ያነጻሁት፣ ንጹሕ መሆኔንም ለማሳየት እጄን የታጠብኩት በከንቱ ነው” ብሏል። ይህ ሌዋዊ፣ ከባድ መንፈሳዊ አደጋ ተጋርጦበት እንደነበር በግልጽ ማየት ይቻላል።
‘ይሖዋ ተስፋ የቆረጡትን ያድናል’
15 መዝሙር 73:16-19, 22-25ን አንብብ። ሌዋዊው “ወደ ታላቁ የአምላክ መቅደስ [ገባ]።” ከሌሎች የእምነት ባልንጀሮቹ ጋር መገናኘት በሚችልበት በአምላክ መቅደስ ውስጥ በእርጋታ ማሰብ፣ ሁኔታውን አጥርቶ ማየትና ስለ ጉዳዩ መጸለይ ችሏል። በዚህም የተነሳ፣ ማስተዋል እንደጎደለውና ከይሖዋ ሊያርቀው በሚችል አደገኛ ጎዳና ላይ እየተጓዘ እንዳለ ተገነዘበ። በተጨማሪም ክፉዎች “በሚያዳልጥ መሬት ላይ” እንዳሉና ቅጽበታዊ “ጥፋት” እንደሚደርስባቸው አስተዋለ። መዝሙራዊው ያደረበትን ቅናትና የተስፋ መቁረጥ ስሜት ለማስወገድ ጉዳዩን ከይሖዋ አመለካከት አንጻር ማየት ነበረበት። እንዲህ ሲያደርግ ውስጣዊ ሰላሙንና ደስታውን መልሶ ማግኘት ችሏል። ‘በምድር ላይ ከይሖዋ ሌላ የምሻው የለም’ በማለት ተናግሯል።
16 ምን ትምህርት እናገኛለን? የተሳካላቸው በሚመስሉ ክፉ ሰዎች ፈጽሞ መቅናት አይኖርብንም። ደስታቸው ዘላቂና እውነተኛ አይደለም፤ እንዲሁም የዘላለም ሕይወት አያገኙም። (መክ. 8:12, 13) በእነሱ መቅናት፣ ተስፋ እንድንቆርጥና ለመንፈሳዊ አደጋ እንድንዳረግ ያደርገናል። በመሆኑም ክፉዎች ስኬታማ በመምሰላቸው ምክንያት መቅናት ከጀመርን ሌዋዊው የወሰደውን ዓይነት እርምጃ መውሰድ ይኖርብናል። ፍቅር የሚንጸባረቅበትን የአምላክን ምክር መታዘዝና የይሖዋን ፈቃድ ከሚያደርጉ ሰዎች ጋር መቀራረብ አለብን። ከምንም ነገር በላይ ይሖዋን የምንወደው ከሆነ እውነተኛ ደስታ እናገኛለን። እንዲሁም “እውነተኛ የሆነውን ሕይወት” በሚያስገኝልን ጎዳና ላይ መጓዛችንን እንቀጥላለን።—1 ጢሞ. 6:19
እምነት በማሳየት ረገድ ሙሴን ምሰሉ
5 ‘በኃጢአት በሚገኝ ጊዜያዊ ደስታ’ እንዳትሸነፍ ምን ሊረዳህ ይችላል? በኃጢአት የሚገኝ ደስታ ቅጽበታዊ መሆኑን አትርሳ። “ዓለምም ሆነ ምኞቱ በማለፍ ላይ” እንደሆኑ በእምነት ዓይንህ ይታይህ። (1 ዮሐ. 2:15-17) ንስሐ ያልገቡ ኃጢአተኞች የወደፊት ዕጣቸው ምን እንደሆነ አሰላስል። “በሚያዳልጥ ስፍራ” የቆሙ ያህል ነው፤ ‘ፈጽመው ይወድማሉ!’ (መዝ. 73:18, 19) ኃጢአት ለመፈጸም ስትፈተን ‘ወደፊት ምን እንዲያጋጥመኝ ነው የምፈልገው?’ በማለት ራስህን ጠይቅ።
የአምላክን ክብር እንዳታገኙ ምንም ነገር እንቅፋት አይሁንባችሁ
3 መዝሙራዊው፣ ይሖዋ ቀኝ እጁን ይዞ እንደሚመራውና ወደ ክብር እንደሚያስገባው ያለውን እምነት ገልጿል። (መዝሙር 73:23, 24ን አንብብ።) ይሖዋ ይህን የሚያደርገው እንዴት ነው? ይሖዋ ትሑት አገልጋዮቹን ወደ ክብር የሚያስገባቸው በተለያዩ መንገዶች ነው። ፈቃዱን እንዲገነዘቡ በማድረግ ይባርካቸዋል። (1 ቆሮ. 2:7) እንዲሁም ቃሉን የሚሰሙና እሱን የሚታዘዙ ሰዎችን ከእሱ ጋር የቅርብ ዝምድና እንዲመሠርቱ በመፍቀድ ያከብራቸዋል።—ያዕ. 4:8
4 ከዚህም ሌላ ይሖዋ፣ እጅግ ውድ ሀብት የሆነውን ክርስቲያናዊ አገልግሎት ለአገልጋዮቹ በአደራ ሰጥቷቸዋል። (2 ቆሮ. 4:1, 7) ይህ አገልግሎት ደግሞ ክብር እንዲያገኙ ያደርጋቸዋል። ይሖዋ፣ በዚህ የአገልግሎት መብት ተጠቅመው እሱን ለሚያወድሱና ሌሎችን ለሚረዱ ሁሉ “የሚያከብሩኝን አከብራለሁ” የሚል ቃል ገብቷል። (1 ሳሙ. 2:30) እንዲህ ያሉ ሰዎች በይሖዋም ሆነ በሌሎች የአምላክ አገልጋዮች ዘንድ ጥሩ ስም ስለሚያተርፉ ክብር ያገኛሉ።—ምሳሌ 11:16፤ 22:1
5 ‘ይሖዋን ደጅ የሚጠኑና መንገዱን የሚጠብቁ’ ሰዎች ወደፊት ምን ያገኛሉ? እነዚህ ሰዎች “ምድሪቱን ትወርስ ዘንድ [ይሖዋ] ከፍ ከፍ ያደርግሃል፤ ክፉዎችም ሲጠፉ ታያለህ” የሚል ቃል ተገብቶላቸዋል። (መዝ. 37:34) እነዚህ ሰዎች የዘላለም ሕይወት በማግኘት ወደር የሌለው ክብር የመጎናጸፍ ተስፋ አላቸው።—መዝ. 37:29
መንፈሳዊ ዕንቁዎች
it-2 240
ሌዋታን
መዝሙር 74 አምላክ ሕዝቡን ያዳነበትን ታሪክ ይተርካል፤ ቁጥር 13 እና 14 ደግሞ እስራኤላውያንን ከግብፅ ነፃ ያወጣበትን መንገድ በምሳሌያዊ ሁኔታ ይገልጻሉ። እዚህ ላይ “ግዙፍ የባሕር ፍጥረታት [ዕብ. ታኒኒም፣ ታኒን የሚለው ቃል በብዙ ቁጥር ሲገለጽ]” የሚለው አገላለጽ “ሌዋታንን” ያመለክታል፤ የሌዋታን ራሶች መድቀቅ ደግሞ እስራኤላውያን ከግብፅ ነፃ በወጡበት ወቅት በፈርዖንና በሠራዊቱ ላይ የደረሰውን አሳፋሪ ሽንፈት የሚያመለክት ሊሆን ይችላል። አረማይክ ታርገም “የሌዋታንን ራሶች” በሚለው ቦታ “የፈርዖንን ኃያላን” የሚለውን አገላለጽ ይጠቀማል። (ከሕዝ 29:3-5 ጋር አወዳድር፤ እዚህ ላይ ፈርዖን በአባይ ጅረቶች መካከል ካለ “ግዙፍ የባሕር ፍጥረት” ጋር ተመሳስሏል፤ ሕዝ 32:2ንም ተመልከት።) ኢሳይያስ 27:1 ሌዋታን (ሰብዓ ሊቃናት ትርጉም “ዘንዶ”) የሚለውን ቃል የሚጠቀምበት ዓለም አቀፋዊ ይዘት ያለውን እንዲሁም “እባብ” እና “ዘንዶ” ተብሎ የተጠራው አካል የሚቆጣጠረውን ግዛት ለማመልከት ሳይሆን አይቀርም። (ራእይ 12:9) ይህ ትንቢት ስለ እስራኤል መልሶ መቋቋም የሚገልጽ ትንቢት ስለሆነ ይሖዋ ሌዋታንን ይቀጣዋል ሲባል ባቢሎንንም የሚያካትት መሆን አለበት። ይሁንና ቁጥር 12 እና 13 ስለ አሦርና ስለ ግብፅም ይናገራሉ። በመሆኑም እዚህ ላይ የተጠቀሰው ሌዋታን ይሖዋንና አገልጋዮቹን የሚቃወምን ዓለም አቀፋዊ ድርጅት ወይም ግዛት የሚያመለክት ሊሆን ይችላል።
ከነሐሴ 19-25
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | መዝሙር 75–77
ጉራ አትንዙ—ለምን?
አምላክን በሚያገለግለውና በማያገለግለው መካከል ያለውን ልዩነት አስተውሉ
4 ጳውሎስ በመጨረሻው ዘመን የሚኖሩ ሰዎች ራሳቸውንና ገንዘብን የሚወዱ እንደሚሆኑ ከገለጸ በኋላ ብዙዎች ጉረኞች፣ ትዕቢተኞች እና በኩራት የተወጠሩ እንደሚሆኑ ተናግሯል፤ አንድ ሰው እነዚህን ባሕርያት የሚያሳየው በችሎታው፣ በመልኩ፣ በሀብቱ አሊያም በማኅበረሰቡ ውስጥ ባለው ቦታ የተነሳ ከሌሎች እንደሚበልጥ አድርጎ የሚያስብ ከሆነ ነው። እንዲህ ዓይነት ሰዎች፣ ሁልጊዜ ሌሎች እንዲያደንቋቸውና ከፍ ያለ ቦታ እንዲሰጧቸው ይፈልጋሉ። አንድ ምሁር፣ እብሪተኛ ስለሆነ ሰው ሲናገሩ “በልቡ ውስጥ ትንሽ መሠዊያ ሠርቶ ለራሱ ተንበርክኮ ይሰግዳል” ብለዋል። ከልክ ያለፈ ኩራት በጣም የሚጠላ ባሕርይ በመሆኑ፣ ኩሩ የሆኑ ሰዎችም እንኳ እንዲህ ያለ ባሕርይ ያላቸውን ሰዎች እንደማይወዱ አንዳንዶች ሲናገሩ ይሰማል።
5 ይሖዋ ኩራትን እንደሚጸየፍ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ይናገራል። በተጨማሪም ‘ትዕቢተኛ ዓይንን’ እንደሚጠላ ተገልጿል። (ምሳሌ 6:16, 17) ኩራት ወደ አምላክ እንዳንቀርብ እንቅፋት ይሆናል። (መዝ. 10:4) ይህ ባሕርይ የዲያብሎስ መገለጫ ነው። (1 ጢሞ. 3:6) የሚያሳዝነው ግን ታማኝ ከሆኑ የይሖዋ አገልጋዮች መካከል አንዳንዶቹም በኩራት ወጥመድ ወድቀዋል። የይሁዳ ንጉሥ የነበረው ዖዝያ ለዓመታት ይሖዋን በታማኝነት አገልግሏል። “ይሁን እንጂ ዖዝያ በበረታ ጊዜ ለጥፋት እስኪዳረግ ድረስ ልቡ ታበየ፤ በዕጣን መሠዊያው ላይ ዕጣን ለማጠን ወደ ይሖዋ ቤተ መቅደስ በመግባት በአምላኩ በይሖዋ ላይ ታማኝነት የጎደለው ድርጊት ፈጸመ።” ንጉሥ ሕዝቅያስም በአንድ ወቅት ልቡ ታብዮ ነበር።—2 ዜና 26:16፤ 32:25, 26
የመዝሙር ሦስተኛና አራተኛ መጻሕፍት ጎላ ያሉ ነጥቦች
75:4, 5, 10—“ቀንድ” የሚለው አባባል ምን ያመለክታል? እንስሳት ቀንዳቸውን እንደ ኃይለኛ መሣሪያ ይጠቀሙበታል። በመሆኑም “ቀንድ” የሚለው ቃል ምሳሌያዊ በሆነ መንገድ ኃይልን ወይም ጥንካሬን ለማመልከት ተሠርቶበታል። ይሖዋ የሕዝቡን ቀንድ ከፍ ከፍ በማድረግ እንዲደሰቱ ሲያደርግ ‘የክፉዎችን ቀንድ ግን ይሰብራል።’ የኩራትና የትዕቢት መንፈስ እንዳይጠናወተን “ቀንድህን ከፍ አታድርግ” የሚል ምክር ተሰጥቶናል። ከፍ ከፍ ያደረገን ይሖዋ በመሆኑ በጉባኤ ውስጥ የሚሰጡንን ኃላፊነቶች ከእርሱ እንደተቀበልናቸው አድርገን መመልከት ይኖርብናል።—መዝሙር 75:7
መንፈሳዊ ዕንቁዎች
የመዝሙር ሦስተኛና አራተኛ መጻሕፍት ጎላ ያሉ ነጥቦች
76:10—“የሰዎች ቊጣ” (የ1980 ትርጉም) ለይሖዋ ምስጋና የሚያመጣው እንዴት ነው? ይሖዋ፣ አገልጋዮቹ በመሆናችን ምክንያት ሰዎች በእኛ ላይ እንዲቆጡ መፍቀዱ መልካም ውጤት ሊያስገኝ ይችላል። አገልጋዮቹ በመሆናችን ምክንያት የሚደርስብን ማንኛውም መከራ አንድ ዓይነት ሥልጠና ይሰጠናል። ይሖዋ መከራ እንዲደርስብን የሚፈቅደው እንዲህ ያለውን ሥልጠና እስክናገኝ ብቻ ነው። (1 ጴጥሮስ 5:10) ከዚህ ‘የተረፈውን ቊጣ ራሱ ይገታዋል።’ ለሞት የሚዳርግ ሥቃይ ቢደርስብንስ? የእኛን በታማኝነት መቆም የሚመለከቱ ሰዎች ይሖዋን ለማወደስ እንዲገፋፉ ሊያደርግ ስለሚችል ይህም ቢሆን እርሱን ያስከብራል።
ከነሐሴ 26–መስከረም 1
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | መዝሙር 78
የእስራኤላውያን ታማኝነት ማጉደል—የማስጠንቀቂያ ምሳሌ
“የቀድሞዎቹን ቀኖች አስታውሱ”—ለምን?
የሚያሳዝነው ግን እስራኤላውያን በተደጋጋሚ ጊዜ የመርሳት ኃጢአት ይፈጽሙ ነበር። ውጤቱስ ምን ሆነ? “ተመለሱ፣ እግዚአብሔርንም ፈተኑት፣ የእስራኤልንም ቅዱስ አሳዘኑት። እነርሱም እጁን አላሰቡም፣ ከጠላቶቻቸው እጅ ያዳነበትን ቀን።” (መዝሙር 78:41, 42) በመጨረሻም የይሖዋን ትእዛዛት መዘንጋታቸው በእሱ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያጡ አድርጓቸዋል።—ማቴዎስ 21:42, 43
“ያህ ያደረጋቸውን ነገሮች አስታውሳለሁ፤ ከረጅም ጊዜ በፊት ያከናወንካቸውን አስደናቂ ሥራዎች አስታውሳለሁ። ባደረግሃቸው ነገሮች ሁሉ ላይ አሰላስላለሁ፣ እንዲሁም ድርጊቶችህን አስብባቸዋለሁ” ሲል የጻፈው መዝሙራዊ ጥሩ ምሳሌ ትቷል። (መዝሙር 77:11, 12 አዓት) ያለፈውን የታማኝነት አገልግሎትና የይሖዋን ፍቅራዊ ተግባራት በማሰላሰል ማስታወስ አስፈላጊውን ማነቃቂያና ማበረታቻ እንድናገኝ እንዲሁም አድናቆታችን እንዲጨምር ያደርጋል። በተጨማሪም ‘የቀድሞዎቹን ቀኖች ማስታወስ’ ድካምን ለማስወገድ የሚረዳ ከመሆኑም በላይ በታማኝነት ለመጽናት የተቻለንን ሁሉ እንድናደርግ ሊቀሰቅሰን ይችላል።
‘አታጉረምርሙ’
16 ማጉረምረም ስለ ራሳችንና ስለ ችግሮቻችን ብቻ እንድናስብ ሊያደርገን እንዲሁም የይሖዋ ምሥክር በመሆናችን ምክንያት ያገኘናቸው በርካታ በረከቶች ፈጽሞ እንዳይታዩን ሊያደርገን ይችላል። የማማረር ዝንባሌ ኖሮብን ልናሸንፈው የምንፈልግ ከሆነ የይሖዋ አገልጋዮች በመሆናችን ምክንያት ያገኘናቸውን በረከቶች ማስታወስ ይገባናል። ለምሳሌ ያህል፣ እያንዳንዳችን የይሖዋን የግል ስም የመሸከም ድንቅ መብት አለን። (ኢሳይያስ 43:10) ከአምላክ ጋር የተቀራረበ ዝምድና መመሥረት እንችላለን፤ በተጨማሪም ‘ጸሎትን የሚሰማውን’ ይሖዋን በማንኛውም ጊዜ ማነጋገር እንችላለን። (መዝሙር 65:2፤ ያዕቆብ 4:8) ጽንፈ ዓለማዊ ሉዓላዊነትን በተመለከተ የተነሳውን ጉዳይ ስለምናውቅና ለአምላክ ታማኝ ሆኖ የመቆም መብት ስላለን ሕይወታችን እውነተኛ ትርጉም አለው። (ምሳሌ 27:11) አዘውትረን የመንግሥቱን ምሥራች መስበክ እንችላለን። (ማቴዎስ 24:14) በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛዊ መሥዋዕት ላይ ያለን እምነት ንጹሕ ሕሊና እንዲኖረን ያስችለናል። (ዮሐንስ 3:16) ምንም ዓይነት ችግር ቢኖርብን እነዚህን በረከቶች እያገኘን ነው።
ይሖዋ ስሜት አለው?
መዝሙራዊው “በምድረ በዳ ስንት ጊዜ ዐመፁበት!” በማለት ተናግሯል። (ቁጥር 40) በሚቀጥለው ቁጥር ላይ ደግሞ “ደግመው ደጋግመው እግዚአብሔርን ተፈታተኑት” የሚል ሐሳብ ይገኛል። (ቁጥር 41) ጸሐፊው እስራኤላውያን በተደጋጋሚ ጊዜ ያምፁ እንደነበር መግለጹን ልብ በል። እንዲህ ያለው መጥፎ ዝንባሌ የጀመረው ከግብፅ ከወጡ ብዙም ሳይቆዩ ገና በምድረ በዳ በነበሩበት ጊዜ ነው። ሕዝቡ፣ አምላክ እነሱን ለመንከባከብ ያለውን አቅምና ፍላጎት በመጠራጠር በእሱ ላይ ማመፅ ጀመረ። (ዘኍልቍ 14:1-4) ለመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚዎች የተዘጋጀ አንድ የማመሳከሪያ ጽሑፍ “ዐመፁበት” የሚለው ቃል “‘በአምላክ ላይ ልባቸውን አደነደኑ’ ወይም ‘አምላክን “እንቢ” አሉ’ ተብሎ ሊተረጎም” እንደሚችል ገልጿል። እንደዚያም ሆኖ ይሖዋ ንስሐ ሲገቡ በምሕረት ተነሳስቶ ይቅር ይላቸው ነበር። ይሁንና ወደ ቀድሞ ሕይወታቸው በመመለስ እንደገና ዓመፁ፤ እንዲህ ዓይነቱ ሁኔታ በተደጋጋሚ ጊዜ ይከሰት ነበር።—መዝሙር 78:10-19, 38
ይሖዋ ወጥ አቋም የሌለው ይህ ሕዝብ በሚያምፅበት ጊዜ ምን ተሰምቶት ነበር? ቁጥር 40 “አሳዘኑት” ይላል። ሌላ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ደግሞ “ለመሪር ሐዘን ዳረጉት” በማለት ይገልጻል። አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ የማመሳከሪያ ጽሑፍ ይህን ጉዳይ ሲያብራራ “ይህ ሐረግ የማይታዘዝና ዓመፀኛ የሆነ አንድ ልጅ የሚያደርገው ነገር ሥቃይ እንደሚያስከትል ሁሉ የዕብራውያኑ ድርጊትም ለሥቃይ ምክንያት እንደሆነ የሚገልጽ ትርጉም አለው” ብሏል። በጥባጭ የሆነ ልጅ ወላጆቹን እንደሚያበሳጭ ሁሉ ዓመፀኛ የሆኑት እነዚህ እስራኤላውያንም ‘የእስራኤልን ቅዱስ አስቈጥተውታል።’—ቁጥር 41
መንፈሳዊ ዕንቁዎች
የመዝሙር ሦስተኛና አራተኛ መጻሕፍት ጎላ ያሉ ነጥቦች
78:24, 25—መና ‘የሰማይ መብል’ እና ‘የመላእክት እንጀራ’ ተብሎ የተጠራው ለምንድን ነው? ሁለቱም አገላለጾች መና የመላእክት ምግብ መሆኑን አያመለክቱም። መና የተገኘው ከሰማይ በመሆኑ ‘የሰማይ እንጀራ’ ተብሏል። (መዝሙር 105:40) መላእክት ደግሞ የሚኖሩት በሰማይ ነው፤ በመሆኑም ‘የመላእክት እንጀራ’ የሚለው አገላለጽ በሰማይ ከሚኖረው አምላክ የተሰጠ መሆኑን የሚያመለክት ሊሆን ይችላል። (መዝሙር 11:4) በሌላ በኩል፣ ይሖዋ ለእስራኤላውያን መና ለመስጠት በመላእክት ተጠቅሞም ይሆናል።