የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መላእክትን በተመለከተ እውነታው ምንድን ነው?
    መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2017 | ቁጥር 5
    • መላእክት የተደራጁት እንዴት ነው?

      የመላእክት አለቃ የሆነው ሚካኤል በኃይልም ሆነ በሥልጣን ከሁሉም መላእክት ይበልጣል። ሚካኤል፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ሌላ ስም እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ይጠቁማል።—1 ተሰሎንቄ 4:16፤ ይሁዳ 9

      ሱራፌል የተባሉት መላእክት ከፍተኛ መብትና ክብር ያላቸው ሲሆን እነዚህ መላእክት የሚያገለግሉት በአምላክ ዙፋን ዙሪያ ነው።—ኢሳይያስ 6:1-3

      ኪሩቤል የተባሉት መላእክትም ከፍተኛ ሥልጣን ያላቸው ሲሆን ሁሉን ቻይ የሆነውን ታላቅ አምላክ በቅርበት ያገለግላሉ። ኪሩቦች ብዙውን ጊዜ አምላክ በሚገኝበት ቦታ እንደሚገኙ ተገልጿል።—ዘፍጥረት 3:24፤ ሕዝቅኤል 9:3፤ 11:22

      መልእክተኞች የሆኑ አእላፋት መላእክት የልዑሉ አምላክ ወኪሎች ሆነው የአምላክን ፈቃድ ያስፈጽማሉ።b—ዕብራውያን 1:7, 14

  • ጠባቂ መልአክ አለህ?
    መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2017 | ቁጥር 5
    • የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ | መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መላእክት ምን ይላል?

      ጠባቂ መልአክ አለህ?

      መጽሐፍ ቅዱስ እያንዳንዱ ግለሰብ የራሱ ጠባቂ መልአክ አለው ብሎ አያስተምርም። እርግጥ ነው፣ ኢየሱስ በአንድ ወቅት “በሰማይ ያሉት መልአኮቻቸው በሰማይ ባለው አባቴ ፊት ዘወትር ስለሚቀርቡ ከእነዚህ ከትናንሾቹ [የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት] መካከል አንዱንም እንዳትንቁ ተጠንቀቁ” ብሏል። (ማቴዎስ 18:10) ይሁን እንጂ ኢየሱስ ይህን የተናገረው፣ መላእክት የእሱን ደቀ መዛሙርት በግለሰብ ደረጃ ትኩረት ሰጥተው እንደሚከታተሏቸው ለማመልከት እንጂ እያንዳንዱ ሰው የራሱ ጠባቂ መልአክ አለው ለማለት አይደለም። በመሆኑም እውነተኛ የአምላክ አገልጋዮች መላእክት እንደሚጠብቋቸው በማሰብ ሕይወታቸውን ለአደጋ የሚያጋልጥ የሞኝነት ወይም የግድየለሽነት ድርጊት አይፈጽሙም።

      ታዲያ መላእክት ሰዎችን አይረዱም ማለት ነው? በፍጹም። (መዝሙር 91:11) አንዳንዶች አምላክ በመላእክት አማካኝነት ጥበቃ እንዳደረገላቸውና አመራር እንደሰጣቸው በእርግጠኝነት ያምናሉ። በመጀመሪያው ርዕስ ላይ የተጠቀሰው ኬነት እንዲህ ከሚሰማቸው ሰዎች አንዱ ነው። በእርግጠኝነት መናገር ባንችልም ኬነት ልክ ሊሆን ይችላል። የይሖዋ ምሥክሮች በስብከት ሥራቸው ሲካፈሉ የመላእክት እገዛ መኖሩን የሚያሳዩ ማስረጃዎችን በተደጋጋሚ ይመለከታሉ። ይሁን እንጂ መላእክት በዓይን ስለማይታዩ አምላክ ሰዎችን ለመርዳት ምን ያህል እንደሚጠቀምባቸው በእርግጠኝነት መናገር አንችልም። ያም ሆኖ ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ለሚያደርግልን ማንኛውም ዓይነት ድጋፍ ብናመሰግነው ስህተት አይሆንም።—ቆላስይስ 3:15፤ ያዕቆብ 1:17, 18

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ