የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “ልብህን ጠብቅ!”
    መጠበቂያ ግንብ—2012 | ግንቦት 1
    • “ልብህን ጠብቅ!”

      የይሖዋ ምሥክሮች የአውራጃ ስብሰባ

      የዓርብ ዕለት ጭብጥ

      ‘ይሖዋ ልብን ያያል’​—1 ሳሙኤል 16:7

      የቅዳሜ ዕለት ጭብጥ

      “አንደበት የሚናገረው በልብ ውስጥ የሞላውን ነው”​—ማቴዎስ 12:34

      የእሁድ ዕለት ጭብጥ

      ‘ይሖዋን በፍጹም ልብ አገልግለው’​—1 ዜና መዋዕል 28:9

      ልብ የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ ሺህ ጊዜ ያህል ይገኛል። በአብዛኞቹ ቦታዎች ቃሉ የተሠራበት ቃል በቃል ሳይሆን ምሳሌያዊ በሆነ መንገድ ነው። ታዲያ ምሳሌያዊው ልብ ምን ያመለክታል? ምሳሌያዊው ልብ የአንድን ሰው ውስጣዊ ማንነት ይኸውም ሐሳቡን፣ ስሜቱንና ፍላጎቱን ሊያመለክት ይችላል።

      ምሳሌያዊውን ልባችንን መጠበቅ ያለብን ለምንድን ነው? ንጉሥ ሰለሞን በአምላክ መንፈስ መሪነት እንዲህ ሲል ጽፏል፦ “ከሁሉም በላይ ልብህን ጠብቅ፤ የሕይወት ምንጭ ነውና።” (ምሳሌ 4:23) ምሳሌያዊው ልባችን ያለበት ሁኔታ በአሁኑ ጊዜ በምንመራው ሕይወትም ሆነ በወደፊቱ ሕይወታችን ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል። እንዲህ የምንለው ለምንድን ነው? አምላክ የሚያየው ልባችንን ስለሆነ ነው። (1 ሳሙኤል 16:7) አምላክ ለእኛ ያለው አመለካከት የሚወሰነው በውስጣዊ ማንነታችን ይኸውም ‘በተሰወረው የልብ ሰው’ ነው።​—1 ጴጥሮስ 3:4

      ልባችንን መጠበቅ የምንችለው እንዴት ነው? የዚህ ጥያቄ መልስ የይሖዋ ምሥክሮች በሚያደርጉት የአውራጃ ስብሰባ ላይ በጥልቀት ይብራራል፤ በዓለም ዙሪያ የሚደረገው ይህ ስብሰባ በዚህ ወር ይጀምራል። በሦስቱም ቀናት በስብሰባው ላይ እንዲገኙ በአክብሮት ተጋብዘዋል።a በስብሰባው ላይ የሚቀርበው ትምህርት የይሖዋ አምላክን ልብ ደስ በሚያሰኝ መንገድ ሕይወትዎን ለመምራት ያስችልዎታል።​—ምሳሌ 27:11

  • መጥተን እንድናነጋግርዎ ይፈልጋሉ?
    መጠበቂያ ግንብ—2012 | ግንቦት 1
    • መጥተን እንድናነጋግርዎ ይፈልጋሉ?

      በዚህ በመከራ በተሞላ ዓለምም እንኳ ስለ አምላክ፣ ስለ መንግሥቱና ለሰው ልጆች ስላለው አስደናቂ ዓላማ ትክክለኛ የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት በማግኘት ደስተኛ መሆን ይችላሉ። ተጨማሪ መረጃ ማግኘት አሊያም ከአንድ የይሖዋ ምሥክር ጋር መጽሐፍ ቅዱስን ያለ ክፍያ መማር የሚፈልጉ ከሆነ www.pr2711.com. በተባለው ድረ ገጽ አማካኝነት ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር መገናኘት ይችላሉ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ