የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • th ጥናት 6 ገጽ 9
  • የጥቅሱን ዓላማ ግልጽ ማድረግ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የጥቅሱን ዓላማ ግልጽ ማድረግ
  • ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጥቅሶችን ጥሩ አድርጎ ማስተዋወቅ
    ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
  • ጥቅሶችን ከነጥቡ ጋር ማገናዘብ
    በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም
  • ግቡን የሚመታ መደምደሚያ
    ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
  • የትምህርቱን ጥቅም ግልጽ ማድረግ
    ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
ለተጨማሪ መረጃ
ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
th ጥናት 6 ገጽ 9

ጥናት 6

የጥቅሱን ዓላማ ግልጽ ማድረግ

ጥቅስ

ዮሐንስ 10:33-36

ፍሬ ሐሳብ፦ አንድን ጥቅስ ካነበብክ በኋላ ሳታብራራው ወደ ሌላ ነጥብ አትለፍ። አድማጮችህ ባነበብከው ጥቅስና እያብራራኸው ባለው ነጥብ መካከል ያለውን ዝምድና እንዲያስተውሉ እርዳቸው።

ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

  • ቁልፍ ቃላትን ለይተህ አውጣ። ጥቅስ ካነበብክ በኋላ ከዋናው ነጥብ ጋር በቀጥታ የሚዛመዱትን ቃላት አጉላ። እነዚህን ቃላት በመድገም ወይም ደግሞ አድማጮች ቁልፍ የሆኑትን ቃላት እንዲለዩ የሚረዳ ጥያቄ በማንሳት ይህን ማድረግ ትችላለህ።

    ጠቃሚ ሐሳብ

    በጥቅሱ ላይ ያለውን ሐሳብ በሌላ አባባል በምትገልጽበት ጊዜም እንኳ አድማጮችህ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ባሉት ቃላትና በምታብራራው ዋና ነጥብ መካከል ያለውን ዝምድና ማስተዋል እንዲችሉ እርዳቸው።

  • ዋናውን ነጥብ ጎላ አድርገህ ግለጽ። አንድን ጥቅስ የምታነብበትን ዓላማ ተናግረህ ከነበረ ጥቅሱን ካነበብክ በኋላ ቁልፍ የሆኑት ቃላት፣ ጥቅሱ የተጠቀሰበትን ዓላማ የሚደግፉት እንዴት እንደሆነ አብራራ።

    ጠቃሚ ሐሳብ

    አንድን ጥቅስ ካነበብክ በኋላ ጥቅሱን ስታብራራ መጽሐፍ ቅዱስህን አትክደነው። እንዲህ ማድረግህ አድማጮችህ የምትናገረውን ሐሳብ ካነበብከው ጥቅስ ጋር ማዛመድ እንዲችሉ ይረዳቸዋል።

  • ጥቅሱ እንዴት ተግባራዊ እንደሚሆን ባልተወሳሰበ መንገድ አስረዳ። ከዋናው ነጥብ ጋር ብዙም ተያያዥነት የሌላቸውን ነጥቦች አታብራራ። አድማጮችህ ስለ ርዕሰ ጉዳዩ የሚያውቁትን ነገር ከግምት አስገባ፤ ከዚያም ጥቅሱ እንዴት ተግባራዊ እንደሚሆን ለማስረዳት ምን ያህል ማብራሪያ መስጠት እንዳለብህ ወስን።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ