ጥናት 11
በጋለ ስሜት መናገር
ሮም 12:11
ፍሬ ሐሳብ፦ ግለት በሚንጸባረቅበት መንገድ በመናገር የአድማጮችህን ስሜት ለመቀስቀስና ለተግባር ለማነሳሳት ጥረት አድርግ።
ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?
ትምህርቱ ልብህን ሊነካው ይገባል። ንግግርህን በምትዘጋጅበት ጊዜ፣ ትምህርቱ ስላለው ጥቅም ቆም ብለህ አስብ። ከልብ በመነጨ ስሜት መናገር እንድትችል ትምህርቱን በደንብ እስኪዋሃድህ ድረስ አጥናው።
ስለ አድማጮችህ አስብ። የምታነበው ወይም የምትናገረው ነገር አድማጮችህን እንዴት እንደሚጠቅማቸው ለማሰብ ሞክር። አድማጮችህ ከትምህርቱ የሚያገኙት ጥቅም ቁልጭ ብሎ እንዲታያቸው በሚያደርግ መንገድ ንግግርህን ተዘጋጅ።
ንግግርህን ሕያው በሆነ መንገድ አቅርብ። ሞቅ ባለ ስሜት ተናገር። ተስማሚ የሆኑ አካላዊ መግለጫዎችን ተጠቀም፤ ፊትህ ላይ የሚነበበው ነገርም የልብህን ስሜት የሚገልጽ ሊሆን ይገባል።