የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lmd ትምህርት 4
  • ትሕትና

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ትሕትና
  • ሰዎችን ውደዱ—ደቀ መዛሙርት አድርጉ
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጳውሎስ ምን አድርጓል?
  • ከጳውሎስ ምን እንማራለን?
  • ጳውሎስን ምሰል
  • ትሕትናን መልበስ ያለብን ለምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ይሖዋ ትሑት አገልጋዮቹን ከፍ አድርጎ ይመለከታል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2019
  • ልንመስላቸው የሚገቡ የትሕትና ምሳሌዎች
    መጠበቂያ ግንብ—1993
  • እውነተኛ ትሕትናን አዳብሩ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
ለተጨማሪ መረጃ
ሰዎችን ውደዱ—ደቀ መዛሙርት አድርጉ
lmd ትምህርት 4

ውይይት መጀመር

ሐዋርያው ጳውሎስ ንጉሥ አግሪጳ፣ አገረ ገዢ ፊስጦስ እና በርኒቄ ፊት ቀርቦ በአክብሮት ሲናገር፤ እጁ ከአንድ ወታደር ጋር በሰንሰለት ታስሯል።

ሥራ 26:2, 3

ምዕራፍ 4

ትሕትና

መሠረታዊ ሥርዓት፦ “ሌሎች ከእናንተ እንደሚበልጡ በትሕትና አስቡ።”—ፊልጵ. 2:3

ጳውሎስ ምን አድርጓል?

ሐዋርያው ጳውሎስ ንጉሥ አግሪጳ፣ አገረ ገዢ ፊስጦስ እና በርኒቄ ፊት ቀርቦ በአክብሮት ሲናገር፤ እጁ ከአንድ ወታደር ጋር በሰንሰለት ታስሯል።

ቪዲዮ፦ ጳውሎስ ለንጉሥ አግሪጳ ሰበከ

1. ቪዲዮውን ተመልከት፤ ወይም የሐዋርያት ሥራ 26:2, 3ን አንብብ። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች አስብባቸው፦

  1. ሀ. ጳውሎስ ንጉሥ አግሪጳን ሲያነጋግር ትሕትና ያሳየው እንዴት ነው?

  2. ለ. ጳውሎስ ወደ ራሱ ትኩረት ከመሳብ ይልቅ የአድማጮቹን ትኩረት ወደ ይሖዋና ወደ ቅዱሳን መጻሕፍት ያዞረው እንዴት ነው?—የሐዋርያት ሥራ 26:22ን ተመልከት።

ከጳውሎስ ምን እንማራለን?

2. መልእክታችንን በትሕትናና በአክብሮት መናገራችን የሰዎችን ልብ የመማረክ ኃይል አለው።

ጳውሎስን ምሰል

3. ራስህን እንዳታመጻድቅ ተጠንቀቅ። አንተ ሁሉን አዋቂ እንደሆንክ፣ የምታነጋግረው ሰው ደግሞ ምንም እንደማያውቅ በሚያስመስል መንገድ አትናገር። ግለሰቡን እንደምታከብረው በሚያሳይ መንገድ ተናገር።

4. የምታስተምረው ትምህርት መሠረቱ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሆነ ግልጽ አድርግ። በአምላክ ቃል ውስጥ የሚገኙት ሐሳቦች የሰዎችን ልብ ይነካሉ። ሰዎችን ስናነጋግር የአምላክን ቃል መጠቀማችን እምነታቸው በትክክለኛው መሠረት ላይ እንዲገነባ ያደርጋል።

5. ምንጊዜም ገር ሁን። ‘እኔ ያልኩትን ካልተቀበልክ’ ብለህ ድርቅ አትበል። እኛ የመከራከር ፍላጎት የለንም። በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ስሜትህን በመቆጣጠርና ተገቢ በሚሆንበት ጊዜ ግለሰቡን ትተህ በመሄድ ትሕትና አሳይ። (ምሳሌ 17:14፤ ቲቶ 3:2) በገርነት መልስ መስጠትህ ግለሰቡ ሌላ ጊዜ ለመልእክቱ ጆሮ እንዲሰጥ ሊያደርግ ይችላል።

ተጨማሪ ጥቅሶች

ሮም 12:16-18፤ 1 ቆሮ. 8:1፤ 2 ቆሮ. 3:5

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ