-
በሆንግ ኮንግ እውነተኛውን ሀብት ፈልጎ ማግኘትመጠበቂያ ግንብ—1993 | ግንቦት 15
-
-
ናቸው። ስለዚህ የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች ከቤት ወደ ቤት ከሚያደርጉት ምስክርነት በተጨማሪ በመንገድ ላይ በሚደረግ ምስክርነትም ብዙ የተሳካ ውጤት አግኝተዋል። በተጨማሪም ሥራ ቦታቸው ድረስ በመሄድ የቢሮ ሠራተኞችን፣ ባለሱቆችን፣ ገበሬዎችንና በደቡባዊ ቻይና ከሚገኘው ባህር ዓሣ አጥምደው የሚመለሱትን ሰዎች ያነጋግራሉ።
በእውነትም በሆንግ ኮንግ “መከሩስ ብዙ ነው፣ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው” ሊባል ይቻላል። (ማቴዎስ 9:37) በአሁኑ ጊዜ ከ2,300 ሰዎች ውስጥ 1ዱ የይሖዋ ምስክር ነው። የመከሩን ሥራ አጣዳፊነት በመገንዘብ እዚያ ካሉት 2,600 የመንግሥት አስፋፊዎች መካከል ወደ 600 የሚጠጉት አቅኚዎች ወይም የምሥራቹ የሙሉ ጊዜ ሰባኪዎች ናቸው። በሌላ ቦታ እንደሚገኙት ሁሉ በሆንግ ኮንግ ያሉት የይሖዋ ምስክሮችም ‘የይሖዋ በረከት ባለ ጠጋ እንደምታደርግ’ ተገንዝበዋል። (ምሳሌ 10:22) ስለዚህ በዚህ በበለጸገ ማኅበረሰብ ውስጥ ሌሎች ብዙ ሰዎችም እውነተኛውን ሀብት እንዲያገኙ ለመርዳት ጠንክረው በመሥራት ላይ ይገኛሉ።
-
-
ይሖዋን ሙሉ በሙሉ ትከተላለህን?መጠበቂያ ግንብ—1993 | ግንቦት 15
-
-
ይሖዋን ሙሉ በሙሉ ትከተላለህን?
“ጻድቃን . . . እንደ አንበሳ ያለ ፍርሃት ይኖራሉ።” (ምሳሌ 28:1) ምንም ዓይነት አደጋ ከፊታቸው ቢደቀንም በይሖዋ አገልግሎት በድፍረት ወደፊት ይገፋሉ፤ እምነት አላቸው፤ በአምላክ ቃል ላይም ትምክህት ጥለው ይመሩበታል።
እስራኤላውያን በ16ኛው መቶ ዘመን ከዘአበ ከግብፅ ባርነት ነጻ ከወጡ በኋላ በሲና በነበሩበት ወቅት በተለይ ሁለት ሰዎች ልክ እንደ አንበሳ ልበ ሙሉነትን አሳይተዋል። በተጨማሪም በአስቸጋሪ ሁኔታዎችም ሥር እያሉ ለይሖዋ ያላቸውን ታማኝነት አሳይተዋል። ከእነዚህ ሰዎች አንዱ
-