የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • sjj መዝ. 159
  • ለይሖዋ ክብር ስጡ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ለይሖዋ ክብር ስጡ
  • ለይሖዋ ‘በደስታ ዘምሩ’
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የመንግሥቱን መዝሙር ዘምሩ!
    ለይሖዋ ‘በደስታ ዘምሩ’
  • የመንግሥቱን መዝሙር ዘምሩ!
    ለይሖዋ ዘምሩ
  • አዲሱ መዝሙር
    ለይሖዋ ‘በደስታ ዘምሩ’
  • አዲሱ መዝሙር
    ለይሖዋ ዘምሩ
ለተጨማሪ መረጃ
ለይሖዋ ‘በደስታ ዘምሩ’
sjj መዝ. 159

መዝሙር 159

ለይሖዋ ክብር ስጡ

በወረቀት የሚታተመው

(መዝሙር 96:8)

  1. 1. ማን አለ ’ንዳንተ ይሖዋ?

    አቻ የለህ አምሳያ።

    ማን አለ ’ንዳንተ ገናና?

    የግርማ ሞገስ ማደሪያ።

    የሚያስደምም ነው ዙፋንህ፤

    በክብርህ የሞላኸው።

    ታስበው ዘንድ ሰው ምንድን ነው?

    እንዲህ ቦታ የሰጠኸው?

    (አዝማች)

    ይሖዋ ሆይ፣ አምላኬ፣ ንጉሤ፣

    ልቀኝልህ ምስጋና።

    ያስደስትህ የባሪያህ ዝማሬ፤

    ላወድስህ በዜማ።

    ክብር ያንተ ነውና!

  2. 2. ደግ አባት ነህ፣ እጅግ መልካም፤

    እኔ የ’ጅህ ባለ’ዳ።

    ላውራ ’ንጂ ልናገርልህ፤

    አልከፍለው ያንተን ውለታ።

    ሕይወቴን ሰጥቼሃለሁ፤

    የለም የምሰስተው።

    ባሪያህ ልሁን፣ ላገልግልህ፤

    ክብሬ ነው መሆኔ ያንተው።

    (አዝማች)

    ይሖዋ ሆይ፣ አምላኬ፣ ንጉሤ፣

    ልቀኝልህ ምስጋና።

    ያስደስትህ የባሪያህ ዝማሬ፤

    ላወድስህ በዜማ።

    ክብር ያንተ ነውና!

  3. 3. አቤቱ የ’ጆችህ ሥራ!

    ፀሐይ፣ ምድር፣ ጨረቃ።

    ምሥክር ናቸው ለፍቅርህ፤

    ያወድሱሃል ያለቃል።

    ድንቅ ዕፁብ ውበት ለበሱ፤

    ጥበብህ እንከን አልባ።

    ሁሉን የፈጠርከው ጌታ፣

    ክብርህ ይላቅ፣ ያስተጋባ።

    (አዝማች)

    ይሖዋ ሆይ፣ አምላኬ፣ ንጉሤ፣

    ልቀኝልህ ምስጋና።

    ያስደስትህ የባሪያህ ዝማሬ፤

    ላወድስህ በዜማ።

    ክብር ያንተ ነውና!

(በተጨማሪም መዝ. 96:1-10፤ 148:3, 7⁠ን ተመልከት።)

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ