የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • hf ክፍል 2 ገጽ 6-8
  • አንዳችሁ ለሌላው ታማኝ ሁኑ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አንዳችሁ ለሌላው ታማኝ ሁኑ
  • ደስተኛ ቤተሰብ ሊኖርህ ይችላል
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • 1 ለትዳራችሁ ቅድሚያ ስጡ
  • 2 ልባችሁን ጠብቁ
  • ትዳራችሁ አስደሳች እንዲሆን የአምላክን መመሪያ ተከተሉ
    ደስተኛ ቤተሰብ ሊኖርህ ይችላል
  • ከሠርጋችሁ ቀን በኋላ
    ከአምላክ ፍቅር ሳትወጡ ኑሩ
  • የጋብቻ ቃል ኪዳንን አክብሮ መኖር
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • የትዳር ጓደኛችሁን በአክብሮት መያዝ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
ለተጨማሪ መረጃ
ደስተኛ ቤተሰብ ሊኖርህ ይችላል
hf ክፍል 2 ገጽ 6-8
አንድ ባል ለሚስቱ ጃንጥላ ይዞላት የመኪና በር ከፍቶ ሲያስገባት

ክፍል 2

አንዳችሁ ለሌላው ታማኝ ሁኑ

“አምላክ ያጣመረውን ማንም ሰው አይለያየው።”—ማርቆስ 10:9

ይሖዋ ‘ታማኝነትን እንድንወድ’ ይጠብቅብናል። (ሚክያስ 6:8) በተለይ በትዳራችሁ ውስጥ ታማኝነት እጅግ አስፈላጊ ነው፤ ምክንያቱም ታማኝነት ከሌለ መተማመን አይኖርም። ፍቅራችሁ እያደገ እንዲሄድ ደግሞ መተማመን መኖሩ የግድ አስፈላጊ ነው።

በዛሬው ጊዜ በትዳር ውስጥ ታማኝነትን ማጉደል የተለመደ ነገር እየሆነ መጥቷል። ትዳራችሁን እንዲህ ካለው አደጋ መጠበቅ እንድትችሉ ሁለት ነገሮችን ለማድረግ መቁረጥ አለባችሁ።

1 ለትዳራችሁ ቅድሚያ ስጡ

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “ይበልጥ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ለይታችሁ [እወቁ]።” (ፊልጵስዩስ 1:10) በሕይወታችሁ ውስጥ ይበልጥ አስፈላጊ ከሆኑት ነገሮች አንዱ ትዳራችሁ ነው። ትዳራችሁ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል።

ይሖዋ ለትዳር ጓደኛችሁ ትኩረት እንድትሰጡና ‘ተደስታችሁ እንድትኖሩ’ ይፈልጋል። (መክብብ 9:9) ይሖዋ የትዳር ጓደኛችሁን ፈጽሞ ችላ ማለት እንደሌለባችሁ ይልቁንም አንዳችሁ ሌላውን ማስደሰት የምትችሉባቸውን መንገዶች መፈለግ እንዳለባችሁ በግልጽ ተናግሯል። (1 ቆሮንቶስ 10:24) የትዳር ጓደኛህ ተፈላጊ እንደሆነችና እንደምታደንቃት እንዲሰማት አድርግ።

አንድ ባል ለሚስቱ ትኩስ መጠጥ ሲያቀርብላት፤ ባል ወደ ቤት ሲመለስ ሚስቱ ምግብ እያዘጋጀች ሳለ

ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

  • ከትዳር ጓደኛችሁ ጋር ዘወትር አብራችሁ ጊዜ አሳልፉ፤ እንዲሁም ለትዳር ጓደኛችሁ ሙሉ ትኩረታችሁን ስጡ

  • “እኔ” ከማለት ይልቅ “እኛ” እያላችሁ አስቡ

አንድ ባልና ሚስት ሽርሽር ላይ

2 ልባችሁን ጠብቁ

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “አንዲትን ሴት በፍትወት ስሜት የሚመለከት ሁሉ በዚያን ጊዜ በልቡ ከእሷ ጋር አመንዝሯል።” (ማቴዎስ 5:28) አንድ ሰው ስለ ፆታ ብልግና የሚያውጠነጥን ከሆነ ለትዳር ጓደኛው ያለውን ታማኝነት እያጓደለ ነው ሊባል ይችላል።

ይሖዋ ‘ልባችሁን መጠበቅ’ እንደሚያስፈልጋችሁ ይናገራል። (ምሳሌ 4:23፤ ኤርምያስ 17:9) ይህን ለማድረግ ደግሞ ዓይናችሁን መጠበቅ አለባችሁ። (ማቴዎስ 5:29, 30) ሌላዋን ሴት ፈጽሞ በምኞት ላለመመልከት ከዓይኑ ጋር ቃል ኪዳን የገባውን የኢዮብን ምሳሌ ተከተሉ። (ኢዮብ 31:1) የብልግና ምስሎችንና ጽሑፎችን ፈጽሞ ላለመመልከትና ላለማንበብ ቁርጥ ውሳኔ አድርጉ። እንዲሁም ከትዳር ጓደኛችሁ ሌላ ለማንም ሰው ምንም ዓይነት የፍቅር ስሜት እንዳይኖራችሁ ተጠንቀቁ።

አንድ ባል በሥራ ቦታ የሚስቱን ፎቶ ግራፍ ጠረጴዛ ላይ አድርጎ

ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

  • ለትዳር ጓደኛህ ሙሉ በሙሉ ታማኝ መሆንህ ለሌሎች በግልጽ እንዲታይ አድርግ

  • የትዳር ጓደኛህን ስሜት ግምት ውስጥ አስገባ፤ ከሌላ ሴት ጋር ያለህ ቅርርብ እሷን ቅር የሚያሰኛት ከሆነ ግንኙነቱን ወዲያውኑ አቋርጥ

የበኩልህን አድርግ

ለራስህ ሐቀኛ በመሆን ድክመቶችህን ለይተህ እወቅ። (መዝሙር 15:2) ድክመትህን ማሸነፍ እንድትችል እርዳታ ለመጠየቅ ኀፍረት አይሰማህ። (ምሳሌ 1:5) የብልግና ሐሳቦች ወደ አእምሮህ ከመጡ እነዚህን ለማስወገድ ታገል። በዚህ ረገድ ቶሎ ተስፋ አትቁረጥ። (ምሳሌ 24:16) ይሖዋ ለትዳር ጓደኛህ ታማኝ ለመሆን የምታደርገውን ጥረት ይባርከዋል።

ራስህን እንዲህ እያልክ ጠይቅ፦

  • ለትዳር ጓደኛዬ ይበልጥ ጊዜ ልሰጣት የምችለው እንዴት ነው?

  • የትዳር ጓደኛዬ የልብ ጓደኛዬ ናት?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ