የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • fg ትምህርት 5 ጥያቄ 1-5
  • አምላክ ለምድር ያለው ዓላማ ምንድን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አምላክ ለምድር ያለው ዓላማ ምንድን ነው?
  • ከአምላክ የተላከ ምሥራች!
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አምላክ ለምድር ያለው ዓላማ ምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • አምላክ ለምድር ያለው ዓላማ ምንድን ነው?
    አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?
  • በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰችው ገነት የምትገኘው የት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • “ገነት ውስጥ እንገናኝ!”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2018
ለተጨማሪ መረጃ
ከአምላክ የተላከ ምሥራች!
fg ትምህርት 5 ጥያቄ 1-5

ትምህርት 5

አምላክ ለምድር ያለው ዓላማ ምንድን ነው?

1. አምላክ ምድርን የፈጠራት ለምንድን ነው?

አዳም እና ሔዋን በኤደን ገነት ውስጥ፤ ከጊዜ በኋላ ደግሞ ከገነት ሲባረሩ

ይሖዋ ምድርን የፈጠራት ለሰው ልጆች መኖሪያ እንድትሆን ነው። አምላክ የመጀመሪያዎቹን ባልና ሚስት ይኸውም አዳምና ሔዋንን የፈጠራቸው በሰማይ እየኖሩ ልጆች ወልደው እንዲባዙ አልነበረም፤ ምክንያቱም እነሱን ከመፍጠሩ በፊት መላእክትን በሰማይ እንዲኖሩ ፈጥሯል። (ኢዮብ 38:4, 7) አምላክ የመጀመሪያውን ሰው፣ ኤደን ገነት በምትባል ውብ የሆነች ቦታ አስቀመጠው። (ዘፍጥረት 2:15-17) ከዚያም ለአዳምና ወደፊት ለሚወልዳቸው ልጆች በምድር ላይ ለዘላለም የመኖር ተስፋ ሰጣቸው።​—መዝሙር 37:29ን እና 115:16ን አንብብ።

መጀመሪያ ላይ ገነት የነበረው የኤደን የአትክልት ቦታ ብቻ ነበር። የመጀመሪያዎቹ ባልና ሚስት ልጆች ወልደው ምድርን እንዲሞሉ ተነግሯቸው ነበር። ውሎ አድሮ መላዋን ምድር መግዛትና ገነት ማድረግ ይጠበቅባቸው ነበር። (ዘፍጥረት 1:28) ምድር ፈጽሞ አትጠፋም። ምንጊዜም የሰው ዘር መኖሪያ ሆና ትቀጥላለች።​—መዝሙር 104:5ን አንብብ።

አምላክ ምድርን የፈጠረው ለምንድን ነው? የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት

2. በአሁኑ ጊዜ ምድር ገነት ያልሆነችው ለምንድን ነው?

አዳምና ሔዋን አምላክን ለመታዘዝ አሻፈረኝ በማለታቸው ይሖዋ ከገነት አባረራቸው። በዚህ ምክንያት ገነት የጠፋች ሲሆን ማንም ሰው መልሶ ሊያቋቁማት አልቻለም። መጽሐፍ ቅዱስ “ምድር ለክፉዎች ተሰጥታለች” ይላል።—ኢዮብ 9:24​—ዘፍጥረት 3:23, 24ን አንብብ።

በምድር ላይ እንደገና በምትቋቋመው ገነት ላይ ሰዎች ቤት ሲሠሩ

ታዲያ ይሖዋ ለሰው ልጆች የነበረውን የመጀመሪያ ዓላማ ትቶት ይሆን? በፍጹም! እሱ ሁሉን ቻይ አምላክ ነው። ምንጊዜም ዓላማውን ማሳካት ይችላል። (ኢሳይያስ 45:18) አምላክ፣ የሰው ልጆች መጀመሪያ ላይ ያሰበላቸውን ዓይነት ሕይወት እንዲያገኙ ያደርጋል።​—መዝሙር 37:11, 34ን አንብብ።

3. አምላክ ምድርን እንደገና ገነት የሚያደርጋት እንዴት ነው?

አምላክ የሾመው ንጉሥ ማለትም ኢየሱስ ምድርን በሚያስተዳድርበት ወቅት ወደ ገነትነት እንድትለወጥ ያደርጋል። አርማጌዶን ተብሎ በሚጠራው ጦርነት ወቅት ኢየሱስ የአምላክን መላእክት በመምራት የአምላክን ተቃዋሚዎች በሙሉ ጠራርጎ ያጠፋቸዋል። ከዚያም ሰይጣንን ለ1,000 ዓመት ያስረዋል። የአምላክ ሕዝቦች ግን ኢየሱስ ስለሚመራቸውና ጥበቃ ስለሚያደርግላቸው ከዚህ ጥፋት ይተርፋሉ። ከዚያም ገነት በሆነች ምድር ላይ የዘላለም ሕይወት ያገኛሉ።​—ራእይ 20:1-3ን እና 21:3, 4ን አንብብ።

4. መከራና ሥቃይ የሚወገደው መቼ ነው?

አምላክ ክፋትን ከምድር ላይ የሚያስወግደው መቼ ነው? ኢየሱስ ክፋት የሚወገድበት ጊዜ መቅረቡን የሚጠቁም “ምልክት” ሰጥቷል። በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ ያሉት ሁኔታዎች ለሰው ልጆች ሕልውና የሚያሰጉ ናቸው፤ እነዚህ ሁኔታዎች የምንኖረው ‘በዚህ ሥርዓት መደምደሚያ’ ውስጥ መሆኑን ይጠቁማሉ።​—ማቴዎስ 24:3, 7-14, 21, 22ን አንብብ።

ኢየሱስ ከሰማይ ሆኖ ለ1,000 ዓመት ምድርን በሚያስተዳድርበት ወቅት መከራና ሥቃይ በሙሉ እንዲወገድ ያደርጋል። (ኢሳይያስ 9:6, 7፤ 11:9) ኢየሱስ ንጉሥ ብቻ ሳይሆን ሊቀ ካህናትም ሆኖ ስለሚያገለግል አምላክን የሚወዱ ሰዎችን ኃጢአት ያስተሰርያል። በዚህ መንገድ አምላክ በኢየሱስ አማካኝነት በሽታን፣ እርጅናንና ሞትን ያስቀራል።​—ኢሳይያስ 25:8ን እና 33:24ን አንብብ።

5. ገነት በምትሆነው ምድር ላይ የሚኖሩት እነማን ናቸው?

በምድር ላይ እንደገና በምትቋቋመው ገነት ላይ ሰዎች ቤት ሲሠሩ

ወደ ስብሰባ አዳራሽ ስትሄድ አምላክን የሚወዱና እሱን እንዴት ማስደሰት እንደሚችሉ መማር የሚፈልጉ ሰዎችን ታገኛለህ

አምላክን የሚታዘዙ ሰዎች በገነት ውስጥ ይኖራሉ። (1 ዮሐንስ 2:17) ኢየሱስ፣ ቅን የሆኑ ሰዎችን እንዲፈልጉና በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ማግኘት የሚችሉበትን መንገድ እንዲያስተምሯቸው ተከታዮቹን ልኳቸው ነበር። በዛሬው ጊዜ ይሖዋ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ገነት በምትሆነው ምድር ላይ ለመኖር ዝግጁ እንዲሆኑ እየረዳቸው ነው። (ሶፎንያስ 2:3) በይሖዋ ምሥክሮች የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ሰዎች፣ ጥሩ ባልና አባት እንዲሁም ጥሩ ሚስትና እናት መሆን የሚቻለው እንዴት እንደሆነ እየተማሩ ነው። ልጆችና ወላጆች በአንድ ላይ ሆነው ይሖዋን የሚያመልኩ ሲሆን ከምሥራቹ እንዴት ጥቅም ማግኘት እንደሚችሉም ይማራሉ።​—ሚክያስ 4:1-4ን አንብብ።

ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል? የተባለውን መጽሐፍ ምዕራፍ 3 ተመልከት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ