የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 7/06 ገጽ 32
  • ደስተኛ ቤተሰብ ማግኘት ይቻላል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ደስተኛ ቤተሰብ ማግኘት ይቻላል?
  • ንቁ!—2006
ንቁ!—2006
g 7/06 ገጽ 32

ደስተኛ ቤተሰብ ማግኘት ይቻላል?

ባለፈው ዓመት፣ በወጣትነት ዕድሜ ላይ ያለች አንዲት እናት በሜክሲኮ ወደሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮ ደብዳቤ በመጻፍ አስደሳች የቤተሰብ ሕይወት ለማግኘት የሚያስችላትን እርዳታ ጠይቃ ነበር። ንቁ! መጽሔትን አንብባ እንደተደሰተች ከገለጸች በኋላ እንዲህ ብላለች:-

“ትዳር ከያዝኩ ሦስት ዓመታት ያለፉ ሲሆን ደስተኛ ቤተሰብ ለመገንባት የሚረዱ ምክሮችንና ሐሳቦችን ማግኘት ብችል ደስ ይለኛል። እኔና ባለቤቴ የዛሬ ሁለት ዓመት ቆንጅዬ ልጅ ወልደናል። ልጃችንን ደግሞ ጥሩ አድርጌ ላሳድገው እፈልጋለሁ።”

ይህች እናት ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? ስለተባለው መጽሐፍ ሰምታ ስለነበር አንድ ቅጂ እንዲላክላት ጠይቃለች። በሺህ የሚቆጠሩ ሌሎች ሰዎችም መጽሐፉ እንዲላክላቸው ጠይቀዋል። ብዙዎች ካነበቡት በኋላ ምን ያህል ጠቃሚ ሆኖ እንዳገኙት ሪፖርት አድርገዋል። ትምህርት ሰጪ ከሆኑት ምዕራፎች መካከል “ልጆቻችሁን ከሕፃንነታቸው ጀምሮ አሠልጥኗቸው፣” “ቤተሰባችሁን ጎጂ ከሆኑ ተጽዕኖዎች ጠብቁ” እና “በቤተሰባችሁ ውስጥ ሰላም እንዲሰፍን አድርጉ” የሚሉት ይገኙበታል።

ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ማግኘት ከፈለጉ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች ውስጥ አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

□ ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ አንድ ቅጂ ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ