የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 11/06 ገጽ 32
  • “ድንቅ መጽሐፍ ነው”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ድንቅ መጽሐፍ ነው”
  • ንቁ!—2006
ንቁ!—2006
g 11/06 ገጽ 32

“ድንቅ መጽሐፍ ነው”

በ2005 ታትሞ የወጣውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለ መጽሐፍ አስመልክተው ከላይ ያለውን ሐሳብ የጻፉት በጆርጂያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ የሚገኙ አንድ ባልና ሚስት ናቸው። መጽሐፉ 224 ገጾች ያሉት ሲሆን ውብ ሥዕሎችንም ይዟል። ባልና ሚስቱ እንዲህ በማለት ተናግረዋል:- “ቀላል በሆነ ሁኔታ በመዘጋጀቱ ማንኛውም ሰው በመጽሐፉ መጠቀም ይችላል። እንደዚያም ሆኖ ከፍተኛ የትምህርት ደረጃ ያላቸውን ሰዎችም መንፈሳዊ ፍላጎት የሚያረካ ጥልቀት ያለው ትምህርት የያዘ መጽሐፍ ነው።”

በኒው ጀርሲ፣ ዩናይትድ ስቴትስ የሚገኙ አንድ ባልና ሚስት የገጠማቸው ሁኔታ ርዕሱ ብቻ እንኳ የሰዎችን ትኩረት እንደሚስብ ያሳያል። እነዚህ ባልና ሚስት በፍሎሪዳ በተካሄደው የይሖዋ ምሥክሮች የአውራጃ ስብሰባ ላይ ይህን መጽሐፍ ካገኙ በኋላ ለእረፍት ወደ ባሃማስ ሄዱ። አንዲት የጉምሩክ ሠራተኛ ሻንጣቸውን በምትፈትሽበት ጊዜ መጽሐፉን ተመለከተች፤ የመጽሐፉን ርዕስ ካነበበችው በኋላ “ለዚህ ጥያቄ መልስ ለማግኘት እፈልግ ነበር” አለቻቸው። የይሖዋ ምሥክሮቹ መጽሐፉን ሲሰጧት ሴትየዋ በጣም ተደሰተች።

በማግሥቱ እነዚህ ባልና ሚስት በባሕሩ ዳርቻ ላይ ሆነው ይህንን መጽሐፍ ሲያነቡ፣ ለጎብኚዎች ዕቃ የምትሸጥ በአካባቢው የምትኖር አንዲት ሴት ተመለከተቻቸው። በዚያው ዕለት ትንሽ ቀደም ብላ፣ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምን እንደሆነ ለማወቅ እንዲረዳት ወደ አምላክ ጸልያ እንደነበር ነገረቻቸው። ከዚያም እነዚህን ባልና ሚስት መጽሐፉን እንዴት ማግኘት እንደምትችል ጠየቀቻቸው፤ እነርሱም ትርፍ የነበራቸውን የመጨረሻ መጽሐፍ ሲሰጧት በጣም ተደሰተች።

ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለው መጽሐፍ በአሁኑ ጊዜ ከ145 በሚበልጡ ቋንቋዎች የሚገኝ ሲሆን ከ40 ሚሊዮን በላይ ቅጂዎች ታትመዋል። ይህን መጽሐፍ ማግኘት ከፈለጉ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች ውስጥ አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

□ እዚህ ላይ የሚታየውን መጽሐፍ ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ