የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 9/07 ገጽ 32
  • “ምናለ ሁሉም ሰው ቢያነበው!”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ምናለ ሁሉም ሰው ቢያነበው!”
  • ንቁ!—2007
ንቁ!—2007
g 9/07 ገጽ 32

“ምናለ ሁሉም ሰው ቢያነበው!”

ጸሐፊዋ ይህን ያለችው ወደ ይሖዋ ቅረብ የተባለውን መጽሐፍ አስመልክታ ነበር። አክላም “አሁን የይሖዋ ፍቅር ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ ግልጽ ስለሆነልኝ ሌሎችን ይበልጥ ለመውደድ ተነሳስቻለሁ” ብላለች። አንዲት ሌላ ሴት ደግሞ እንዲህ በማለት አድናቆቷን ገልጻለች:- “በዚህ መጽሐፍ ምን ያህል እንደተደሰትኩና መጽሐፉ ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ ለመግለጽ ቃላት ያጥረኛል። . . . ብዙ ባነበብኩ መጠን የዚያኑ ያህል ተበረታትቻለሁ።”

ወደ ይሖዋ ቅረብ የተባለው መጽሐፍ በአራት ክፍሎች ሥር ስለ አምላክ ዋና ዋና ባሕርያት ማለትም ስለ ኃይሉ፣ ፍትሑ፣ ጥበቡና ፍቅሩ በሰፊው ያብራራል። ይህን መጽሐፍ ያነበበች አንዲት ሴት እንዲህ ብላለች:- “መጽሐፉ በሰማይ የሚኖረው አባቴ ያሉትን ግሩም ባሕርያት እንዳስተውል ረድቶኛል። መንፈስ ቅዱስ በሕይወቴ ውስጥ እንዲሠራ ከፈቀድኩ እኔም የእሱን ባሕርያት ማንጸባረቅ እንደምችል አስገንዝቦኛል።”

በፖላንድ የምትኖር ዮአና የተባለች ወጣት “‘ይቅር ባይ’ አምላክ” የሚል ርዕስ ያለውን ምዕራፍ 26ን ካጠናች በኋላ “በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የሚገኙትን ትምህርቶች እንደ ውድ ሀብት አድርጌ እመለከታቸዋለሁ፤ ይህን ሀብት ማግኘት ደግሞ ለሕይወቴ በጣም አስፈላጊ ነው” ብላለች።

እርስዎም 320 ገጽ ካለው ከዚህ መጽሐፍ ከፍተኛ እርዳታና ማጽናኛ እንደሚያገኙ እናምናለን። ይህን መጽሐፍ ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

□ እዚህ ላይ የሚታየውን መጽሐፍ ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ