‘በዓለም ላይ ስላሉ ሃይማኖቶች የሚያብራራ እንዲህ ያለ መጽሐፍ የለም’
◼ በካናዳ የምትኖር አንዲት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር በአካባቢዋ የሚገኙ የተለያዩ ሃይማኖቶች ስለሚያምኑባቸው ነገሮች ለተማሪዎቿ ለማስረዳት ተቸግራ ነበር። ማንካይንድስ ሰርች ፎር ጎድ የተባለውን መጽሐፍ ካነበበች በኋላ “በዓለም ላይ ስላሉ ሃይማኖቶች የሚያብራራ እንዲህ ያለ መጽሐፍ አንብቤ አላውቅም!” በማለት ገልጻለች። መጽሐፉን በጣም ስለወደደችው በክፍል ውስጥ እንድታስተምርበት ፈቃድ እንዲሰጧት የትምህርት ቤቱን ኃላፊዎች የጠየቀቻቸው ሲሆን እነሱም ጥያቄዋን ተቀበሉ።
መምህሯ በካናዳ ከሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮ የዚህን መጽሐፍ 40 ቅጂ ለመውሰድ ስትል ከ500 ኪሎ ሜትር በላይ ለመጓዝ ፈቃደኛ መሆኗን ገልጻለች። ይሁንና በአካባቢዋ የሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮች መጻሕፍቱን ያለችበት ድረስ ሊያመጡላት እንደሚችሉ ገለጹላት። ከተማሪዎቿ መካከል አብዛኞቹ መጽሐፉን በጣም ስለወደዱት የራሳቸው ቅጂ ማግኘት እንዲችሉ ጥያቄ አቅርበዋል።
እርስዎም በአካባቢዎ የሚኖሩ ሰዎች ስለሚያምኑባቸው ነገሮች ለማወቅ ከፈለጉ ይህ መጽሐፍ ጠቃሚ ሆኖ ያገኙት ይሆናል። መጽሐፉ እንደ ሂንዱይዝም፣ ቡዲዝም፣ ታኦይዝም፣ ኮንፊሺያኒዝም፣ ሺንቶ፣ ጁዳይዝም፣ እስልምና እንዲሁም ክርስትና ያሉትን በዓለም ላይ የሚገኙ ታላላቅ ሃይማኖቶች አመጣጥና ታሪክ እንዲሁም ስለሚያምኑባቸው ነገሮች ያብራራል።
እርስዎም፣ ማንካይንድስ ሰርች ፎር ጎድ የተባለው ማራኪ የሆኑ ሥዕሎች የያዘው ባለ 384 ገጽ መጽሐፍ እንዲላክልዎት መጠየቅ ይችላሉ። የዚህን መጽሐፍ አንድ ቅጂ ማግኘት ከፈለጉ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ከሞሉ በኋላ በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ አለዚያም በገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።
□ ማንካይንድስ ሰርች ፎር ጎድ የተባለውን መጽሐፍ ላኩልኝ።
□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።