ልጆች መጽሐፉን በጣም ወደውታል!
◼ ከታላቁ አስተማሪ ተማር የተባለው መጽሐፍ በሁሉም ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ልጆችን ይማርካቸዋል። አንዲት ልጅ እንዲህ በማለት ጽፋለች፦ “በመጽሐፉ ውስጥ ያሉት የተለያዩ ነገሮች መጽሐፉን እንድወደው አድርጎኛል። ለምሳሌ ያህል፣ ሁሉንም ሥዕሎች ወድጃቸዋለሁ። ሥዕሎቹ ደማቅ መሆናቸው ትኩረት ይስባል። መጽሐፉን ሳነብ፣ ሥዕሎቹን በጥንቃቄ በመመልከት ከታሪኩ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለመረዳት እሞክራለሁ!
“ሌላው የወደድኩት ነገር ደግሞ መጽሐፉ የተጻፈበትን መንገድ ነው። በመጽሐፉ ላይ ያሉትን ቃላት መረዳት ቀላል ነው፤ ይህ ደግሞ መጽሐፉን ማንበብ ይበልጥ አስደሳች እንዲሆን ያደርጋል።
“ይህ መጽሐፍ፣ በዛሬው ጊዜ ያሉትን አንዳንድ ችግሮች እንዲሁም ችግሮቹን እንዴት መወጣት እንደምንችል ያብራራበት መንገድ ትኩረቴን ስቦታል። የሚከተሉትን ምዕራፎች በጣም ወድጃቸዋለሁ፦ ‘የሚያጋጥሙንን ፈተናዎች መቋቋም ያስፈልገናል፣’ ‘ደግ ስለመሆን የተሰጠ ትምህርት’ እንዲሁም ‘ሁልጊዜ ቅድሚያ ማግኘት ትፈልጋለህ?’”
እርስዎም ውብ ሥዕሎችን የያዘውና ከዚህ መጽሔት ጋር ተመሳሳይ መጠን ያለው ይህን ባለ 256 ገጽ መጽሐፍ እንዲላክልዎት መጠየቅ ይችላሉ። ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።
□ ከታላቁ አስተማሪ ተማር የተባለውን መጽሐፍ ላኩልኝ።
□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።