የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 7/09 ገጽ 10
  • ኃይል ቆጣቢው ቦክስፊሽ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ኃይል ቆጣቢው ቦክስፊሽ
  • ንቁ!—2009
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የርዕስ ማውጫ
    ንቁ!—2009
  • የመጀመሪያውን ንድፍ ያወጣው ማን ነው?
    ሕይወት የተገኘው በፍጥረት ነው?
  • ተፈጥሮ ምን ያስተምረናል?
    ንቁ!—2006
  • እጅብ ብለው የሚዋኙ ዓሦች
    ንቁ!—2012
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2009
g 7/09 ገጽ 10

ንድፍ አውጪ አለው?

ኃይል ቆጣቢው ቦክስፊሽ

የመኪና ንድፍ አውጪዎች ጠንካራ፣ ይበልጥ ኃይል የሚቆጥብና አካባቢን የማይበክል መኪና ለማምረት የሚያስችል ሞዴል ለማግኘት ያልተጠበቀ ቦታ ይኸውም ባሕር ውስጥ ገብተው ምርምር እያደረጉ ነው! በሐሩር ክልል ውቅያኖሶች ውስጥ ባሉ ኮራል ሪፎች አጠገብ የሚገኘው ቦክስፊሽ የተባለው የዓሣ ዝርያ ክብደቱ ቀላል የሆነና አየርን ሰንጥቆ የማለፍ አስገራሚ ችሎታ ያለው ተሽከርካሪ ለመሥራት ግሩም ሞዴል ይሆናል።

እስቲ የሚከተለውን አስብ፦ ቦክስፊሽ በእያንዳንዱ ሴኮንድ የቁመቱን ስድስት እጥፍ የሚሆን ርቀት እየተወረወረ በፍጥነት መዋኘት ይችላል። ይሁን እንጂ ዓሣው በዚህ ፍጥነት ሊጓዝ የቻለው ጠንካራ ስለሆነ ብቻ አይደለም። ይህ ዓሣ ከሌሎች ፍጹም በተለየ መንገድ እኩል መጠን ያለው ባለ ስድስት ጎን ቅርጽ ያለው መሆኑ አየር ሰንጥቆ የማለፍ ችሎታውን ይጨምርለታል። እንዲያውም መሐንዲሶች በቦክስፊሽ ሞዴል የተሠራ መኪና ለሙከራ ንፋስ በታመቀበት መሿለኪያ ውስጥ እንዲያልፍ በማድረግ መኪናው አነስተኛ መጠን ካላቸው ሌሎች መኪናዎች በተሻለ ሁኔታ አየሩን እየሰነጠቀ የማለፍ ብቃት እንዳለው አረጋግጠዋል።

ቦክስፊሽ አጥንት የበዛበት የቆዳ ሽፋን አለው፤ ይህ ደግሞ ክብደቱ አነስተኛ ቢሆንም ከፍተኛ ጥንካሬ እንዲኖረው አስችሎታል። ባሕሩ በሚናወጥበት ጊዜ በዓሣው ዙሪያ የሚፈጠሩት እሽክርክሪቶች ዓሣው አንድ ቦታ ላይ ተረጋግቶ እንዲቆይ ይረዱታል። ይህም ቦክስፊሽ አስደናቂ ቅልጥፍና እንዲኖረውና ከጉዳት እንዲጠበቅ ያደርገዋል።

መሐንዲሶች የቦክስፊሽን ሞዴል በመከተል በቀላሉ ለአደጋ የማይጋለጥ፣ ይበልጥ ኃይል የሚቆጥብ ሆኖም ክብደቱ ቀላል የሆነ ተሽከርካሪ መሥራት እንደሚችሉ እምነት አላቸው። የምርምርና የልማት ተቋም ኃላፊ የሆኑት ዶክተር ቶማስ ዌበር “ግልጹን ለመናገር፣ አየርን ሰንጥቆ የማለፍ አስገራሚ ችሎታ ያለውና ነዳጅ ቆጣቢ የሆነ መኪና ለመሥራት ቀርፋፋ የሚመስለው ይህ ዓሣ ሞዴል ሊሆነን እንደሚችል ስናውቅ በጣም ተገርመናል።”

ታዲያ ምን ይመስልሃል? ኃይል ቆጣቢው ቦክስፊሽ ዓሣ እንዲሁ በአጋጣሚ የተገኘ ነው? ወይስ ንድፍ አውጪ አለው?

[በገጽ 10 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

ቦክስፊሽ፦ © Hal Beral/V&W/SeaPics.com; መኪና፦ Mercedes-Benz USA

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ